አገልጋይ ጌታው የሚያደርገውን ስለማያውቅ ከእንግዲህ ወዲህ አገልጋዮች አልላችሁም፤ ነገር ግን ከአባቴ የሰማሁትን ሁሉ ስለ ገለጥኩላችሁ ወዳጆቼ ብያችኋለሁ፤
ዮሐንስ 8:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለ እናንተ የምናገረውና የምፈርደው ብዙ ነገር አለኝ፤ ይሁን እንጂ የላከኝ እውነተኛ ነው፤ እኔም ለዓለም የምናገረው ከእርሱ የሰማሁትን ነው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእናንተ ላይ ብዙ የምናገረውና ብዙ የምፈርደው ነገር አለኝ፤ ዳሩ ግን የላከኝ ታማኝ ነው፤ ከርሱም የሰማሁትን ለዓለም እናገራለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ እናንተ የምናገረው የምፈርደውም ብዙ ነገር አለኝ፤ ዳሩ ግን የላከኝ እውነተኛ ነው፤ እኔም ከእርሱ የሰማሁትን ይህን ለዓለም እናገራለሁ፤” አላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ እናንተ የምናገረውና የምፈርደው ብዙ አለኝ፤ የላከኝም እውነተኛ ነው፤ እኔ በእርሱ ዘንድ የሰማሁትን ለዓለም እናገራለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ እናንተ የምናገረው የምፈርደውም ብዙ ነገር አለኝ፤ ዳሩ ግን የላከኝ እውነተኛ ነው እኔም ከእርሱ የሰማሁትን ይህን ለዓለም እናገራለሁ” አላቸው። |
አገልጋይ ጌታው የሚያደርገውን ስለማያውቅ ከእንግዲህ ወዲህ አገልጋዮች አልላችሁም፤ ነገር ግን ከአባቴ የሰማሁትን ሁሉ ስለ ገለጥኩላችሁ ወዳጆቼ ብያችኋለሁ፤
የሰጠኸኝን ቃል ሰጥቻቸዋለሁ፤ እነርሱም ተቀብለውታል፤ ከአንተ ዘንድ መጥቼ መምጣቴንም በእውነት ዐውቀዋል፤ አንተ እንደ ላክኸኝም አምነዋል።
ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “እኔ ለሰው ሁሉ በግልጥ ተናገርኩ፤ አይሁድ ሁሉ በሚሰበሰቡበት በምኲራብም ሆነ በቤተ መቅደስ፥ ዘወትር አስተማርኩ፤ በስውር የተናገርኩት ምንም ነገር የለም፤
ስለዚህ ኢየሱስ በቤተ መቅደስ ሲያስተምር ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፦ “እኔን ታውቁኛላችሁ፤ ከወዴትም እንደ መጣሁ ታውቃላችሁ፤ ነገር ግን እኔ በራሴ ሥልጣን አልመጣሁም፤ የላከኝ እርሱ እውነተኛ ነው፤ እናንተ ግን አታውቁትም።