Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዮሐንስ 7:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰ፦ “የእኔ ትምህርት ከላከኝ ከአብ የተገኘ ነው እንጂ ከእኔ አይደለም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፤ “የማስተምረው ትምህርት ከራሴ ሳይሆን፣ ከላከኝ የመጣ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ስለዚህም ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ትምህርቴስ የላከኝ ነው እንጂ የእኔ አይደለም፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ስለ​ዚ​ህም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ትም​ህ​ርቴ የላ​ከኝ ናት እንጂ የእኔ አይ​ደ​ለ​ችም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ስለዚህ ኢየሱስ መለሰ እንዲህም አላቸው፦ “ትምህርቴስ ከላከኝ ነው እንጂ ከእኔ አይደለም፤

Ver Capítulo Copiar




ዮሐንስ 7:16
14 Referencias Cruzadas  

እኔ በአብ እንዳለሁ፥ አብም በእኔ እንዳለ አታምንምን? ለእናንተ የምናገረውን ቃል የምናገረው በራሴ ሥልጣን አይደለም፤ ነገር ግን ሥራውን ሁሉ የሚሠራው፥ በእኔ የሚኖረው አብ ነው።


የማይወደኝ ቃሌን አይጠብቅም፤ ይህ የምትሰሙት ቃል የላከኝ የአብ ነው እንጂ የእኔ አይደለም።


እኔ ቃልህን ሰጥቻቸዋለሁ፤ እኔ ከዓለም እንዳይደለሁ እነርሱም ከዓለም አይደሉም፤ ስለዚህ ዓለም ጠላቸው።


የሰጠኸኝን ቃል ሰጥቻቸዋለሁ፤ እነርሱም ተቀብለውታል፤ ከአንተ ዘንድ መጥቼ መምጣቴንም በእውነት ዐውቀዋል፤ አንተ እንደ ላክኸኝም አምነዋል።


እውነት፥ እውነት እልሃለሁ፤ የምናውቀውን እንናገራለን፤ ያየነውንም እንመሰክራለን፤ እናንተ ግን ምስክርነታችንን አትቀበሉትም።


ከላይ የሚመጣው ከሁሉ በላይ ነው፤ ከምድር የሆነ ምድራዊ ነው፤ የምድርንም ነገር ይናገራል፤ ከሰማይ የሚመጣው ከሁሉ በላይ ነው።


“እኔ በራሴ ሥልጣን ምንም ማድረግ አልችልም፤ ነገር ግን ከአብ የሰማሁትን እፈርዳለሁ፤ የላከኝን ፈቃድ እንጂ የራሴን ፈቃድ ስለማላደርግ ፍርዴ ትክክል ነው።


የላከኝ አብ የሳበው ካልሆነ በቀር ወደ እኔ መምጣት የሚችል ማንም የለም፤ ወደ እኔ የሚመጣውንም በመጨረሻ ቀን ከሞት አስነሣዋለሁ።


ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “የሰውን ልጅ ከፍ አድርጋችሁ በምትሰቅሉት ጊዜ እኔ እርሱ እንደ ሆንኩ ታውቃላችሁ፤ እንዲሁም አብ ያስተማረኝን እንደምናገር እንጂ በራሴ ሥልጣን ብቻ ምንም እንደማላደርግ ያን ጊዜ ታስተውላላችሁ።


በክርስቶስ ትምህርት ጸንቶ የማይኖርና ከእርሱም ርቆ የሚሄድ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር የለም፤ በክርስቶስ ትምህርት ጸንቶ የሚኖር ሰው ግን አብና ወልድ ከእርሱ ጋር አሉ።


ይህ ራእይ በቅርብ ጊዜ ውስጥ የሚሆነውን ነገር ለአገልጋዮቹ እንዲያሳያቸው እግዚአብሔር ለኢየሱስ ክርስቶስ የሰጠው ነው፤ ኢየሱስ ክርስቶስም መልአኩን ልኮ ለአገልጋዩ ለዮሐንስ ይህን ራእይ ገለጠለት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos