Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዮሐንስ 8:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ስለ እናንተ የምናገረው የምፈርደውም ብዙ ነገር አለኝ፤ ዳሩ ግን የላከኝ እውነተኛ ነው፤ እኔም ከእርሱ የሰማሁትን ይህን ለዓለም እናገራለሁ፤” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 በእናንተ ላይ ብዙ የምናገረውና ብዙ የምፈርደው ነገር አለኝ፤ ዳሩ ግን የላከኝ ታማኝ ነው፤ ከርሱም የሰማሁትን ለዓለም እናገራለሁ።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ስለ እናንተ የምናገረውና የምፈርደው ብዙ ነገር አለኝ፤ ይሁን እንጂ የላከኝ እውነተኛ ነው፤ እኔም ለዓለም የምናገረው ከእርሱ የሰማሁትን ነው።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ስለ እና​ንተ የም​ና​ገ​ረ​ውና የም​ፈ​ር​ደው ብዙ አለኝ፤ የላ​ከ​ኝም እው​ነ​ተኛ ነው፤ እኔ በእ​ርሱ ዘንድ የሰ​ማ​ሁ​ትን ለዓ​ለም እና​ገ​ራ​ለሁ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ስለ እናንተ የምናገረው የምፈርደውም ብዙ ነገር አለኝ፤ ዳሩ ግን የላከኝ እውነተኛ ነው እኔም ከእርሱ የሰማሁትን ይህን ለዓለም እናገራለሁ” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar




ዮሐንስ 8:26
17 Referencias Cruzadas  

ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም፤ ባርያ ጌታው የሚያደርገውን አያውቅምና፤ ወዳጆች ግን ብያችኋለሁ፤ ከአባቴ የሰማሁትን ሁሉ ለእናንተ አስታውቄአችኋለሁና።


“ገና ብዙ የምነግራችሁ አለኝ፤ ነገር ግን አሁን ልትሸከሙት አትችሉም።


የሰጠኸኝን ቃል ሰጥቻቸዋለሁና፤ እነርሱም ተቀበሉት፤ ከአንተም ዘንድ እንደ ወጣሁ በእውነት አወቁ፤ አንተም እንደ ላክኸኝ አመኑ።


ኢየሱስም መልሶ “እኔ በግልጥ ለዓለም ተናገርሁ፤ አይሁድ ሁሉ በሚሰበሰቡበት በምኵራብና በመቅደስ ሁልጊዜ አስተማርሁ፤ በስውርም ምንም አልተናገርሁም።


እውነት እውነት እልሃለሁ፥ የምናውቀውን እንናገራለን፤ ያየነውንም እንመሰክራለን፤ የእኛንም ምስክርነት አትቀበሉትም።


ስለዚህም ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ትምህርቴስ የላከኝ ነው እንጂ የእኔ አይደለም፤


እንግዲህ ኢየሱስ በመቅደስ ሲያስተምር “እኔንም ታውቁኛላችሁ፤ ከወዴትም እንደሆንሁ ታውቃላችሁ፤ እኔም በራሴ አልመጣሁም ነገር ግን እናንተ የማታውቁት የላከኝ እውነተኛ ነው፤


እንግዲህ “አንተ ማን ነህ?” አሉት። ኢየሱስም “ከመጀመሪያ ለእናንተ የተናገርሁት ነኝ።


ስለ አብ እንደ ነገራቸው አላስተዋሉም።


ነገር ግን አሁን ከእግዚአብሔር የሰማሁትን እውነት የምነገራችሁን እኔን ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ፤ አብርሃም እንዲህ አላደረገም።


እግዚአብሔር የታመነ የሆነውን ያህል በእርግጥ እኛ ለእናንተ የምንናገረው ቃል “አዎን” እና “አይደለም” አይሆንም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos