ዮሐንስ 6:34 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ሰዎቹ “ጌታ ሆይ! ይህን ዐይነት እንጀራ ዘወትር ስጠን” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም፣ “ጌታ ሆይ፤ እንግዲያውስ ይህን እንጀራ ሁልጊዜ ስጠን” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ “ጌታ ሆይ! ይህን እንጀራ ዘወትር ስጠን፤” አሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም፥ “አቤቱ ከዚያ እንጀራ ሁልጊዜ ስጠን” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ፦ ጌታ ሆይ፥ ይህን እንጀራ ዘወትር ስጠን አሉት። |
ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ፤ እናንተ የምትፈልጉኝ እንጀራ ስለ በላችሁና ስለ ጠገባችሁ ነው እንጂ ተአምራት ስላያችሁ አይደለም።