Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዮሐንስ 4:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ሴትዮዋም “ጌታ ሆይ! ከእንግዲህ ወዲህ ውሃ እንዳይጠማኝና ወደዚህም ለመቅዳት እንዳልመጣ እባክህ እንዲህ ዐይነቱን ውሃ ስጠኝ!” አለችው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ሴትዮዋም፣ “ጌታዬ፤ እንዳልጠማና ውሃ ለመቅዳት እንዳልመላለስ፣ እባክህ ይህን ውሃ ስጠኝ” አለችው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ሴቲቱ “ጌታ ሆይ! እንዳልጠማ ውሃም ልቀዳ ወደዚህ እንዳልመጣ ይህን ውሃ ስጠኝ፤” አለችው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ሴቲ​ቱም፥ “ጌታዬ ሆይ፥ እን​ዳ​ል​ጠማ፥ ዳግ​መ​ኛም ውኃ ልቀዳ ወደ​ዚህ እን​ዳ​ል​መጣ እባ​ክህ ከዚህ ውኃ ስጠኝ፤” አለ​ችው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ሴቲቱ፦ ጌታ ሆይ፥ እንዳልጠማ ውኃም ልቀዳ ወደዚህ እንዳልመጣ ይህን ውኃ ስጠኝ አለችው።

Ver Capítulo Copiar




ዮሐንስ 4:15
11 Referencias Cruzadas  

“መልካሙን ነገር ማን ያሳየናል?” የሚሉ ብዙዎች ናቸው፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ሆይ! የፊትህ ብርሃን በእኛ ላይ ይብራ!


ኢየሱስም “ሂጂና ባልሽን ጠርተሽ ተመለሺ” አላት።


ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ፤ እናንተ የምትፈልጉኝ እንጀራ ስለ በላችሁና ስለ ጠገባችሁ ነው እንጂ ተአምራት ስላያችሁ አይደለም።


ስለዚህ ሰዎቹ “ጌታ ሆይ! ይህን ዐይነት እንጀራ ዘወትር ስጠን” አሉት።


ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ፤ ወደ እኔ የሚመጣ ፈጽሞ አይራብም፤ በእኔ የሚያምን ፈጽሞ አይጠማም፤


ከኃጢአት የሚገኘው ዋጋ ሞት ነው፤ ከእግዚአብሔር የሚሰጠው ስጦታ ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት የሚገኘው የዘለዓለም ሕይወት ነው።


በሥጋ ፈቃድ የሚኖሩ ሥጋዊ ነገርን፥ በመንፈስ ፈቃድ የሚኖሩ ግን መንፈሳዊ ነገርን ያስባሉ።


የእግዚአብሔር መንፈስ የሌለው ሥጋዊ ሰው ግን ከእግዚአብሔር መንፈስ የሚሰጠውን ስጦታ መቀበል አይችልም፤ የስጦታው ታላቅነት የሚመረመረው በእግዚአብሔር መንፈስ አማካይነት ስለ ሆነ ሊያስተውለው አይችልም፤ እንዲያውም ይህ ለእርሱ ሞኝነት መስሎ ይታየዋል።


ብትጸልዩም የጸሎታችሁን መልስ የማታገኙት የለመናችሁትን ነገር በሥጋዊ ደስታ ላይ ለማዋል በክፉ ሐሳብ ስለምትጸልዩ ነው።


የእግዚአብሔር ልጅ እንደ መጣና እውነተኛውን አምላክ እንድናውቅ አስተዋይ ልቡና እንደ ሰጠን እናውቃለን በልጁም በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ከእርሱ ከእውነተኛው አምላክ ጋር ኅብረት አለን። ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛው አምላክና የዘለዓለም ሕይወት ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos