ዮሐንስ 5:44 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ እርስ በርሳችሁ ክብርን የምትፈልጉ ከአንዱ ከእግዚአብሔር የሚገኘውን ክብር ግን የማትፈልጉ፥ እንዴት ልታምኑ ትችላላችሁ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ እርስ በርሳችሁ ክብር የምትሰጣጡ፣ ነገር ግን ከአንዱ አምላክ የሚመጣውን ክብር የማትፈልጉ ከሆነ፣ እንዴት ልታምኑ ትችላላችሁ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ እርስ በርሳችሁ ክብር የምትቀባበሉ፥ ከአንዱም ከእግዚአብሔር ብቻ የሚገኘውን ክብር የማትፈልጉ፥ እንዴት ልታምኑ ትችላላችሁ? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከባልንጀራችሁ ክብርን የምትመርጡ፥ ከአንድ እግዚአብሔርም ክብርን የማትሹ እናንተ እንዴት ልታምኑ ትችላላችሁ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ እርስ በርሳችሁ ክብር የምትቀባበሉ ከአንዱም ከእግዚአብሔር ያለውን ክብር የማትፈልጉ፥ እንዴት ልታምኑ ትችላላችሁ? |
ኢትዮጵያዊ መልኩን፥ ነብርም ዝንጒርጒርነቱን መለወጥ አይችልም፤ እንዲሁም እናንተ ክፉ ነገር ማድረግን ስለ ለመዳችሁ ደግ ሥራ መሥራት አይሆንላችሁም።
እውነተኛ አይሁዳዊ በውስጥ አይሁዳዊ የሆነ ነው፤ እውነተኛ መገረዝ በእግዚአብሔር መንፈስ የሚሆን የልብ መገረዝ ነው እንጂ በሕግ በተጻፈው መሠረት የሥጋ መገረዝ አይደለም። እንዲህ ዐይነቱም ሰው ምስጋናን የሚቀበለው ከእግዚአብሔር ነው እንጂ ከሰው አይደለም።
ስለዚህ ጊዜው ሳይደርስ፥ ጌታ ለፍርድ ከመምጣቱ በፊት በማንም ላይ አትፍረዱ፤ እርሱ በሚመጣበት ጊዜ በጨለማ የተሰወረውን ምሥጢር ወደ ብርሃን ያወጣዋል፤ በሰዎች ልብ የተደበቀውን ሐሳብ ይገልጠዋል፤ በዚያን ጊዜ እያንዳንዱ ከእግዚአብሔር ተገቢውን ምስጋና ያገኛል።
በትሕትና ተሞልታችሁ ሌሎች ሰዎች ከእናንተ እንደሚሻሉ አድርጋችሁ ቊጠሩ እንጂ በራስ ወዳድነት ወይም “ያለ እኔ ማን አለ” በሚል ትምክሕት ምንም ነገር አታድርጉ።
ይህ ፈተና የሚደርስባችሁ የእምነታችሁን እውነተኛነት ለማረጋገጥ ነው፤ የሚጠፋ ወርቅ እንኳ በእሳት ይፈተናል፤ ከወርቅ ይልቅ የከበረ እምነታችሁ እንደዚሁ መፈተን አለበት፤ ይህም የተፈተነ እምነታችሁ ኢየሱስ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ ምስጋናን፥ ክብርንና ውዳሴን ያስገኝላችኋል።
እርሱ ብቻ መድኃኒታችን ለሆነው አምላክ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ከጥንት ጀምሮ፥ አሁንም፥ ለዘለዓለምም ክብርና ግርማ፥ ኀይልና ሥልጣንም ይሁን! አሜን።
ሳኦልም “በእርግጥ በደል ሠርቼአለሁ፤ ይሁን እንጂ ሌላው ቢቀር በሕዝቤ መሪዎችና በእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ፊት አክብረኝ፤ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር እሰግድ ዘንድ ከእኔ ጋር አብረህ ሂድ” ሲል ለመነው።
ስለዚህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘የአንተ ቤተሰብና የቀድሞ አባትህ ቤተሰብ ለዘለዓለም ያገለግሉኝ ዘንድ ቃል ገብቼ ነበር፤ አሁን ግን እንዲህ አይሆንም፤ የሚያከብሩኝን አከብራለሁ የሚንቁኝም ይናቃሉ።