“አሁንም ልዑል እግዚአብሔር ሆይ፥ አንተ አምላክ ነህ፤ ቃልህ ታማኝ ነው፤ እነሆ፥ አሁንም ይህን መልካም የተስፋ ቃል ለአገልጋይህ ሰጥተሃል።
ዮሐንስ 17:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእውነትህ ቀድሳቸው፤ ቃልህ እውነት ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቃልህ እውነት ነው፤ በእውነትህ ቀድሳቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእውነትህ ቀድሳቸው፤ ቃልህ እውነት ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእውነትህ ቀድሳቸው፤ ቃልህ እውነት ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእውነትህ ቀድሳቸው፤ ቃልህ እውነት ነው። |
“አሁንም ልዑል እግዚአብሔር ሆይ፥ አንተ አምላክ ነህ፤ ቃልህ ታማኝ ነው፤ እነሆ፥ አሁንም ይህን መልካም የተስፋ ቃል ለአገልጋይህ ሰጥተሃል።
በመልካም መሬት ላይ የወደቀው ዘር የሚያመለክተው ግን በመልካምና በቅን ልብ ቃሉን ሰምተው የሚጠብቁትን ነው፤ እነርሱ በቃሉ ጸንተው ፍሬ የሚያፈሩ ናቸው።”
እኛ ሁላችን ባልተሸፈነ ፊት ሆነን በመስታዋት እንደሚታይ ዐይነት የጌታን ክብር እናንጸባርቃለን፤ እኛም መንፈስ የሆነውን የጌታን መልክ ለመምሰል ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን።
በጌታ የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ! እኛ ግን በእናንተ ምክንያት እግዚአብሔርን ሁልጊዜ ማመስገን ይገባናል፤ የምናመሰግነውም እናንተ በመንፈስ ቅዱስ በመቀደሳችሁና እውነትን በማመናችሁ እንድትድኑ እግዚአብሔር በመጀመሪያ ስለ መረጣችሁ ነው።
ስለዚህ ርኲሰትንና የክፋትንም ብዛት ሁሉ አስወግዳችሁ እግዚአብሔር በልባችሁ የተከለውንና ነፍሳችሁን ማዳን የሚችለውን ቃል በትሕትና ተቀበሉ።