ኢየሱስም “ቀበሮዎች ጒድጓድ አላቸው፤ በአየር ላይ የሚበሩ ወፎችም የሚሰፍሩበት ጎጆ አላቸው፤ የሰው ልጅ ግን ራሱን እንኳ የሚያሳርፍበት ስፍራ የለውም” ሲል መለሰለት።
ዮሐንስ 13:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይሁዳ ወጥቶ ከሄደ በኋላ ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “አሁን የሰው ልጅ ከብሮአል፤ በእርሱም አማካይነት እግዚአብሔር ከብሮአል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሁዳ ከወጣ በኋላ፣ ኢየሱስ እንዲህ አለ፤ “አሁን የሰው ልጅ ከበረ፤ በርሱም እግዚአብሔር ከበረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከወጣም በኋላ ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “አሁን የሰው ልጅ ከብሯል፤ በእርሱም እግዚአብሔር ከብሯል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይሁዳም ከወጣ በኋላ ያንጊዜ ጌታችን ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፥ “አሁን የሰው ልጅ ከበረ፤ እግዚአብሔርም በእርሱ ከበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከወጣም በኋላ ኢየሱስ እንዲ አለ፦ “አሁን የሰው ልጅ ከበረ እግዚአብሔርም ሰለ እርሱ ከበረ፤ |
ኢየሱስም “ቀበሮዎች ጒድጓድ አላቸው፤ በአየር ላይ የሚበሩ ወፎችም የሚሰፍሩበት ጎጆ አላቸው፤ የሰው ልጅ ግን ራሱን እንኳ የሚያሳርፍበት ስፍራ የለውም” ሲል መለሰለት።
ኢየሱስም ይህን በሰማ ጊዜ፥ “ይህ ሕመም ለሞት የሚያደርስ አይደለም፤ ነገር ግን ለእግዚአብሔር ክብር እንዲሆንና የእግዚአብሔር ልጅም በዚህ ምክንያት እንዲከበር ነው” አለ።
ይህንንም የተናገረው በእርሱ የሚያምኑ ስለሚቀበሉት ስለ መንፈስ ቅዱስ ነበር፤ ኢየሱስ ገና ወደ ክብር ስላልወጣ መንፈስ ቅዱስ ገና አልተሰጠም ነበር።
የአባቶቻችን የአብርሃም፥ የይስሐቅና፥ የያዕቆብ አምላክ ልጁን ኢየሱስን አከበረው፤ እናንተ ግን እርሱን በጲላጦስ ፊት አሳልፋችሁ ሰጣችሁት፤ ጲላጦስም ሊለቀው ቢፈልግ እንኳ ‘አንፈልግም’ አላችሁ።
እኛ ሁላችን ባልተሸፈነ ፊት ሆነን በመስታዋት እንደሚታይ ዐይነት የጌታን ክብር እናንጸባርቃለን፤ እኛም መንፈስ የሆነውን የጌታን መልክ ለመምሰል ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን።
ይህም የሆነው በአሁኑ ዘመን በቤተ ክርስቲያን አማካይነት በሰማይ ያሉት አለቆችና ባለሥልጣኖች የእግዚአብሔርን ጥበብ በየመልኩ እንዲያውቁ ነው።
እምነታችሁና ተስፋችሁ በእግዚአብሔር ይሆን ዘንድ በኢየሱስ አማካይነት እርሱን ከሞት ባስነሣውና ክብርን በሰጠው በእግዚአብሔር ትተማመናላችሁ።
ምናልባት “ክፉ አድራጊዎች ናቸው” ብለው ቢያሙአችሁም እንኳ እግዚአብሔር እኛን ለመጐብኘት በሚመጣበት ቀን አሕዛብ መልካም ሥራችሁን አይተው እግዚአብሔርን እንዲያመሰግኑ በእነርሱ መካከል ስትኖሩ መልካም ጠባይ ይኑራችሁ።
የሚያስተምር፥ የእግዚአብሔርን ቃል እንደሚያስተምር ያስተምር፤ የሚያገለግልም እግዚአብሔር በሚሰጠው ኀይል ያገልግል፤ በዚህም ዐይነት እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በሁሉ ነገር ይመሰገናል፤ ክብርና ሥልጣን ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ለእርሱ ይሁን፤ አሜን።