Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ጴጥሮስ 4:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 የሚያስተምር፥ የእግዚአብሔርን ቃል እንደሚያስተምር ያስተምር፤ የሚያገለግልም እግዚአብሔር በሚሰጠው ኀይል ያገልግል፤ በዚህም ዐይነት እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በሁሉ ነገር ይመሰገናል፤ ክብርና ሥልጣን ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ለእርሱ ይሁን፤ አሜን።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ከእናንተ ማንም የሚናገር ቢኖር እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር፤ የሚያገለግልም ቢኖር እግዚአብሔር በሚሰጠው ብርታት ያገልግል፤ ይኸውም እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት እንዲከብር ነው። ክብርና ኀይል ለርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ይሁን። አሜን።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ማንም ሰው የሚናገር ቢሆን፥ እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር፤ የሚያገለግልም ቢሆን፥ እግዚአብሔር በሚሰጠው ኃይል ያገልግል፤ በዚህም ዓይነት በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብራል፤ ክብርና ሥልጣን ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ለእርሱ ይሁን፤ አሜን።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ማንም ሰው የሚናገር ቢሆን፥ እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር፤ የሚያገለግልም ቢሆን፥ “እግዚአብሔር በሚሰጠኝ ኀይል ነው” ብሎ ያገልግል፤ ክብርና ሥልጣን እስከ ዘላለም ድረስ ለእርሱ በሚሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ማንም ሰው የሚናገር ቢሆን፥ እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር የሚያገለግልም ቢሆን፥ እግዚአብሔር በሚሰጠኝ ኃይል ነው ብሎ ያገልግል፤ ክብርና ሥልጣን እስከ ዘላለም ድረስ ለእርሱ በሚሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።

Ver Capítulo Copiar




1 ጴጥሮስ 4:11
47 Referencias Cruzadas  

እንግዲህ ስትበሉም ሆነ ስትጠጡ ወይም ማናቸውንም ነገር ስታደርጉ ሁሉንም ነገር ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉ።


በቀረውስ በጌታና በእርሱም ታላቅ ኀይል በርቱ፤


የተለያዩትን የእግዚአብሔርን የጸጋ ስጦታዎች በታማኝነት በማስተዳደር ከእናንተ እያንዳንዱ በተሰጠው የጸጋ ስጦታ ሌላውን ያገልግል።


በበረሓ ተሰብስቦ ከነበረው ሕዝብ ጋርና ከሲና ተራራ ላይ ከተናገረው መልአክ ጋር እንዲሁም ከአባቶቻችን ጋር የነበረው እርሱ ነው። የእግዚአብሔርን የሕይወት ቃል ለእኛ ያስተላለፈልንም ይኸው ሙሴ ነው።


ከቶ ከአፋችሁ ክፉ ቃል አይውጣ፤ ነገር ግን ለሚሰሙት ደስ የሚያሰኝና ለማነጽ የሚጠቅም ለሰዎችም አስፈላጊ የሆነውን ቃል ተናገሩ።


በእርግጥ አይሁዳዊ መሆን በብዙ መንገድ ብልጫ አለው፤ ዋናው ነገር እግዚአብሔር ቃሉን ለአይሁድ ዐደራ መስጠቱ ነው።


የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ይህን አትርሱ፤ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ፥ ለመናገርና ለቊጣም የዘገየ ይሁን።


ለእያንዳንዱ ሰው ተገቢውን መልስ መስጠት እንድታውቁ ዘወትር ንግግራችሁ ለዛና ጣዕም ያለው ይሁን።


ልዩ ልዩ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች አሉ፤ መንፈስ ቅዱስ ግን አንድ ነው።


ወደ ጌታ ኢየሱስ የምትቀርቡትም እንደ ሕያዋን ድንጋዮች መንፈሳዊ ቤት ሆናችሁ ለመታነጽ ነው፤ በዚህ ዐይነት በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ለእግዚአብሔር ለማቅረብ ቅዱሳን ካህናት ትሆናላችሁ።


እርሱ ብቻ መድኃኒታችን ለሆነው አምላክ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ከጥንት ጀምሮ፥ አሁንም፥ ለዘለዓለምም ክብርና ግርማ፥ ኀይልና ሥልጣንም ይሁን! አሜን።


እስከ አሁን በነበረው ጊዜ እናንተ አስተማሪዎች መሆን በተገባችሁ ነበር፤ ነገር ግን የእግዚአብሔርን ቃል የመጀመሪያውን ትምህርት ሌላ ሰው እንደገና እንዲያስተምራችሁ ያስፈልጋል፤ በዚህ ዐይነት የሚያስፈልጋችሁ ወተት ነው እንጂ ጠንካራ ምግብ አይደለም።


እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ እርሱን ከቶ ማንም አላየውም፤ ማንም ሊያየውም አይችልም፤ ክብርና ዘለዓለማዊ ኀይል ለእርሱ ይሁን፤ አሜን።


ስለዚህ ለዘለዓለማዊው ንጉሥ፥ ለማይሞተው፥ ለማይታየው፥ ለአንዱ አምላክ ክብርና ምስጋና ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ይሁን! አሜን።


እግዚአብሔር በሰጠኝ ጸጋ መጠን እንደ ብልኅ ግንበኛ መሠረትን ጣልኩ፤ ሌላውም እኔ በጣልኩት መሠረት ላይ ይገነባል፤ ነገር ግን እያንዳንዱ በዚያ ላይ እንዴት እንደሚገነባ መጠንቀቅ አለበት።


ከክፉ አድነን እንጂ፥ ወደ ፈተና አታግባን፤ [መንግሥት፥ ኀይልና ክብር ለዘለዓለም ያንተ ነው፤ አሜን።’]


በልዩ ልዩ አገር የሚኖሩ ሕዝቦችና ልዩ ልዩ ቋንቋ የሚናገሩ ነገዶች ያገለግሉት ዘንድ ሥልጣን፥ ክብርና ንጉሥነት ተሰጠው፤ ግዛቱም የማይጠፋ ዘለዓለማዊ ነው፤ ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም።


ይህን ቃል ባይናገሩ በእርግጥ የንጋት ብርሃን አይበራላቸውም።


ግዛትህም ከትውልድ ወደ ትውልድ ይተላለፋል። መንግሥትህም ዘለዓለማዊ ነው። እግዚአብሔር በቃል ኪዳኑ የታመነ ነው፤ እርሱ የሚያደርገው ሁሉ መልካም ነው።


ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ክብርና ኀይል ለእርሱ ይሁን! አሜን።


አንደበቱን ሳይቈጣጠር እግዚአብሔርን አመልካለሁ የሚል ሰው ራሱን ያታልላል፤ የእርሱም አምልኮ ከንቱ ነው።


በአንደበታቸውም “ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ ነው” ብለው በመመስከር ለእግዚአብሔር አብ ክብር ይሰጣሉ።


በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ስለ ሁሉ ነገር እግዚአብሔር አብን ዘወትር አመስግኑ።


እርሱ በዋጋ ገዝቶአችኋል፤ ስለዚህ በሰውነታችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ።


ሁሉም ነገር የተገኘው ከእርሱ፥ በእርሱና ለእርሱ ነው፤ ለዘለዓለም ክብር ለእርሱ ይሁን! አሜን!


ንጉሡ ናቡከደነፆር እንዲህ አለ፦ “ሰባቱ ዓመቶች ካለፉ በኋላ ቀና ብዬ ወደ ሰማይ ተመለከትኩ፤ አእምሮዬም ተመለሰልኝ፤ ልዑል እግዚአብሔርን አመሰገንኩ፤ ለዘለዓለማዊው አምላክ ክብርና ውዳሴ አቀረብኩ፤ “ግዛቱ ዘለዓለማዊ ነው፤ ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም፤


“እግዚአብሔር የሚያሳየው ተአምር እንዴት ታላቅ ነው! እርሱ የሚፈጽመው ድንቅ ሥራ እንዴት ብርቱ ነው! እግዚአብሔር ለዘለዓለም ንጉሥ ነው፤ ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም።


በእኔ ጉባኤ ፊት ቆመው ቢሆንማ ኖሮ ቃሌን ለሕዝቡ ባወጁ ነበር፤ ጠማማ መንገዳቸውንና ክፉ አኗኗራቸውንም ትተው ወደ እኔ እንዲመለሱ ማድረግ በቻሉ ነበር።”


በዚህም ዐይነት ሕይወታችሁ ከኢየሱስ ክርስቶስ በሚገኘው የጽድቅ ፍሬ የተሞላ ሆኖ ለእግዚአብሔር ክብርና ምስጋና የምታስገኙ ትሆናላችሁ።


ይህ የእናንተ የልግሥና አገልግሎት እናንተ የክርስቶስን ወንጌል ተቀብላችሁ ታማኞች መሆናችሁንና ለእነርሱና ለሌሎችም መለገሣችሁን የሚያረጋግጥ ስለ ሆነ ሁሉም እግዚአብሔርን ያመሰግናሉ።


እርሱ ብቻ ጥበብ ላለው ለአንድ አምላክ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለዘለዓለም ምስጋና ይሁን! አሜን።


ይሁዳ ወጥቶ ከሄደ በኋላ ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “አሁን የሰው ልጅ ከብሮአል፤ በእርሱም አማካይነት እግዚአብሔር ከብሮአል፤


ደግሞም እያንዳንዳችሁ እግዚአብሔር በሰጣችሁ እምነት መጠን በትሕትና አስቡ እንጂ ከሚገባችሁ በላይ ስለ ራሳችሁ በትዕቢት አታስቡ ብዬ በተሰጠኝ ጸጋ እነግራችኋለሁ።


እኛ የእግዚአብሔርን ቃል እንደ ንግድ ዕቃ እንደሚቸረችሩት እንደ ብዙዎቹ አይደለንም፤ ነገር ግን ከእግዚአብሔር እንደ ተላኩ ቅን መልእክተኞች በክርስቶስ ሆነን በእግዚአብሔር ፊት እንናገራለን።


የማይለካው ታላቅ ኀይሉ ለእኛ ለምናምነው ምን ያኽል ታላቅ መሆኑን ታውቁ ዘንድ እጸልያለሁ፤ ይህንንም ታላቅ ኀይሉን በተግባር ያሳየው ከሞት አስነሥቶ በሰማይ በቀኙ ባስቀመጠው በክርስቶስ አማካይነት ነው።


ይልቅስ እግዚአብሔር ወንጌሉን ለእኛ በዐደራ የሰጠን በእኛ ተማምኖ ስለ ሆነ እንናገራለን፤ ይህንንም የምናደርገው ልባችንን የሚመረምረውን እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት ብለን ነው እንጂ ሰውን ለማስደሰት ብለን አይደለም።


አንተ ግን ሕይወት የሚገኝበትን ትምህርት አስተምር፤


እንግዲህ እነዚህን ነገሮች አስተምር፤ በሙሉ ሥልጣንም ምከር፤ ገሥጽም፤ ማንም አይናቅህ።


የእግዚአብሔርን ቃል በመጀመሪያ የነገሩአችሁን መሪዎቻችሁን አትርሱ፤ የአኗኗራቸውንና የሥራቸውን ውጤት በማስታወስ እምነታቸውን ተከተሉ።


ምናልባት “ክፉ አድራጊዎች ናቸው” ብለው ቢያሙአችሁም እንኳ እግዚአብሔር እኛን ለመጐብኘት በሚመጣበት ቀን አሕዛብ መልካም ሥራችሁን አይተው እግዚአብሔርን እንዲያመሰግኑ በእነርሱ መካከል ስትኖሩ መልካም ጠባይ ይኑራችሁ።


ክርስቲያን በመሆኑ መከራ የሚደርስበት ቢኖር ግን ስለ ክርስቶስ ስም እግዚአብሔርን ያመስግን እንጂ አይፈር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios