ኢዩኤል 1:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሻዎች ባዶአቸውን ቀርተዋል፤ እህል ጠፍቶአል፤ የወይን ተክሎች ደርቀዋል፤ ዘይትም ጠፍቶአል፤ ስለዚህ ምድር ታለቅሳለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዕርሻዎች ባዷቸውን ቀርተዋል፤ ምድሩም ደርቋል፤ እህሉ ጠፍቷል፤ አዲሱ የወይን ጠጅ ዐልቋል፤ ዘይቱም ተሟጧል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እህሉ ጠፍቶአልና፥ ወይኑም ደርቆአልና፥ ዘይቱም ጐድሎአልና እርሻው ምድረ በዳ ሆኖአል፥ ምድሪቱም አልቅሳለች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሻው ምድረ በዳ ሆኖአል፤ ምድሪቱም ታልቅስ፤ እህሉ ጠፍቶአልና፥ ወይኑም ደርቆአልና፥ ዘይቱም ጐድሎአልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እህሉ ጠፍቶአልና፥ ወይኑም ደርቆአልና፥ ዘይቱም ጐድሎአልና እርሻው ምድረ በዳ ሆኖአል፥ ምድሪቱም አልቅሳለች። |
“እኛ የምናደርገውን ሁሉ እግዚአብሔር አያይም” ከሚሉት ሕዝባችን ክፋት የተነሣ፥ ምድራችንን ድርቅ የሚያጠቃውና በየመስኩ ያለውስ ሣር እንደ ደረቀ የሚቀረው እስከ መቼ ነው? በዚህም ምክንያት እንስሶችና ወፎች ሁሉ ተጠራርገው ጠፍተዋል።
ደስታና ሐሴት ለምለም ከሆነችው ከሞአብ ምድር ተወስደዋል፤ ከወይን መጭመቂያዎች ሁሉ የወይን ጠጅ እንዳይፈስስ አድርጌአለሁ፤ የደስታ ድምፅ እያሰማ የሚጨምቅ የለም፤ ድምፅ የሚሰማ ቢሆንም የሚሰማው ድምፅ ግን የደስታ ድምፅ አይደለም።
የወይን ተክሎችና የበለስ ዛፎች ጠውልገዋል፤ ሮማኑ፥ ተምሩና እንኰዩ፥ ሌሎችም የፍራፍሬ ዛፎች ሁሉ ደርቀዋል፤ በዚህም ምክንያት በእርግጥ ደስታ ከሰው ልጆች ርቆአል።
ከእንግዲህ ወዲህ አዲስ የወይን ጠጅ በአፋችሁ ስለማትቀምሱ፥ እናንተ ሰካራሞች ከእንቅልፋችሁ ነቅታችሁ አልቅሱ፤ እናንተም የወይን ጠጅ መጠጣት የምታዘወትሩ ምርር ብላችሁ አልቅሱ።
ስለዚህም እንዲህ አላቸው፦ “እነሆ እህል፥ የወይን ጠጅና የወይራ ዘይት እስክትጠግቡ ድረስ እሰጣችኋለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲያ አሕዛብ መዘባበቻ እንዲያደርጉአችሁ አልፈቅድም።
ምንም እንኳ የበለስ ዛፍ ባያብብ፥ በወይን ተክል ላይም ፍሬ ባይገኝ፥ የወይራ ዛፍም ምንም ፍሬ ባይሰጥ፥ በእርሻዎች ላይ ሰብል ቢጠፋ፥ የበግ መንጋዎች ሁሉ ቢያልቁ፥ በበረት ውስጥ ምንም ከብት ባይገኝ፥
እነሆ በዚህ ምክንያት በተራሮች ላይ በእህል፥ በወይን፥ በዘይት፥ ምድር በምታበቅለው ሁሉ ላይ፥ በሰዎችና በእንስሶች፥ በሥራቸውም ውጤት ሁሉ ላይ ድርቅን አመጣለሁ።”