Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሚልክያስ 2:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 በእናንተ ምክንያት ልጆቻችሁን እቀጣለሁ፤ ለመሥዋዕት ያመጣችኋቸውን እንስሶች እበት በፊታችሁ ላይ እበትናለሁ፤ ከፊቴም አስወግዳችኋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 “ዘራችሁን እገሥጻለሁ፤ የመሥዋዕታችሁን ፋንድያ በፊታችሁ ላይ እበትናለሁ፤ እናንተም ከርሱ ጋራ ትወገዳላችሁ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 እነሆ፥ ዘራችሁን እገሥጻለሁ፥ በፊታችሁ ላይ ፈርስን እበትናለሁ፥ ይህም ፈርስ ለበዓላችሁ መሥዋዕት ካመጣችኋቸው ነው፤ እናንተንም ከእርሱ ጋር ያነሳችኋል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 እነሆ፥ ክንዳችሁን እገሥጻለሁ፥ የመሥዋዕታችሁንም ፋንድያ በፊታችሁ ላይ እበትናለሁ፣ ከእርሱም ጋር በአንድነት ትወሰዳላችሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 እነሆ፥ ክንዳችሁን እገሥጻለሁ፥ የመሥዋዕታችሁንም ፋንድያ በፊታችሁ ላይ እበትናለሁ፥ ከእርሱም ጋር በአንድነት ትወሰዳላችሁ።

Ver Capítulo Copiar




ሚልክያስ 2:3
16 Referencias Cruzadas  

በዚህ ምክንያት እነሆ፥ በኢዮርብዓም ቤት ላይ ክፉ ነገርን አመጣለሁ፤ ከቤቱም ነጻም ሆነ ባሪያ፥ ወንድ ልጅን ሁሉ ከእስራኤል አጠፋለሁ፤ ፋንድያን አቃጥለው እንደሚጨርሱት የኢዮርብዓምን ቤት አወድማለሁ።


እርሱ እንደ ራሱ ኩስ በፍጹም ይጠረጋል፤ ያዩት የነበሩ ሰዎችም ወዴት ነው? ይላሉ።


እግዚአብሔር በእልልታና በመለከት ድምፅ ዐረገ።


እነርሱን በዔንዶር ድል አደረግሃቸው፤ ሬሳቸውም በሜዳ ላይ በስብሶ ቀረ።


የኰርማውን ሥጋ፥ ቆዳውን፥ አንጀቱን ሁሉ ወስደህ ከሰፈር ውጪ አቃጥለው፤ ይህ የኃጢአት መሥዋዕት ነው።


ዐፅሞቻቸው ተሰብስበው በመቀበር ፈንታ፥ እንደ ጒድፍ የትም ይጣላሉ፤ እነርሱም፥ ሕዝቡ በማምለክና ምክር በመጠየቅ በፍቅር ያገለግሉአቸው በነበሩት በፀሐይ፥ በጨረቃና በከዋክብት ፊት ይበተናሉ።


እርሻዎች ባዶአቸውን ቀርተዋል፤ እህል ጠፍቶአል፤ የወይን ተክሎች ደርቀዋል፤ ዘይትም ጠፍቶአል፤ ስለዚህ ምድር ታለቅሳለች።


የተዘራው እህል ሁሉ በዐፈር ውስጥ በስብሶ ቀርቶአል፤ እህል በመታጣቱ የእህል ማከማቻዎች ሁሉ ባዶ ሆነዋል፤ ጐተራዎችም ፈራርሰዋል።


የሚከተለውን አመጣባችኋለሁ፦ ታላቅ ድንጋጤን፥ ክሳትን፥ ዐይንን የሚያፈዝና ሰውነትን የሚያመነምን የንዳድ በሽታ አመጣባችኋለሁ፤ ጠላቶቻችሁ የሚበሉት ስለ ሆነ ዘራችሁን በከንቱ ትዘራላችሁ።


የቈሻሻ መጣያ አደርግሻለሁ፤ በንቀት እመለከትሻለሁ፤ ሰው ሁሉ እንዲሳለቅብሽ አደርጋለሁ።


የእኔን ሥርዓት ባለመከታተል በሕግ ጉዳይ አድልዎ ስለምትፈጽሙ እኔ ደግሞ በሕዝብ ሁሉ ፊት እንድትናቁና እንድትዋረዱ አደርጋችኋለሁ።”


እንዲህ ዐይነቱ ጨው ለእርሻ መሬትም ሆነ ለማዳበሪያ የማይጠቅም ስለ ሆነ ወዲያ አውጥተው ይጥሉታል፤ ሰሚ ጆሮ ያለው ይስማ!”


ሲሰድቡንና ስማችንን ሲያጠፉ በትሕትና እንመልስላቸዋለን፤ እስከ አሁን ድረስ የዚህ ዓለም ውዳቂና የምድር ጥራጊ ጒድፍ ሆነናል።


“የእህልህን ሰብል አንበጣ ስለሚበላው ብዙ እህል ዘርተህ ጥቂት መከር ብቻ ትሰበስባለህ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos