ኢዮብ 13:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ቢመረምራችሁ አንዳች መልካም ነገር ያገኝባችኋልን? ሰዎችን እንደምታሞኙ እግዚአብሔርንም ማሞኘት የምትችሉ ይመስላችኋልን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ ቢመረምራችሁ መልካም ነገር ይገኝባችኋልን? ሰውን እንደምታታልሉ፣ ልታታልሉት ትችላላችሁን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቢመረምራችሁስ መልካም ይሆንልችኋልን? ወይስ በሰውን እንደምታታልሉ ልታታልሉት ትፈልጋላችሁን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱ ቢመረምራችሁ መልካም ነው፥ ይህን ሁሉ በኀይላችሁ ስታደርጉ ራሳችሁን ከእርሱ ጋር አንድ ታደርጋላችሁና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቢመረምራችሁስ መልካም ይሆንልችኋልን? ወይስ በሰው እንደምትሳለቁ ትሳለቁበታላችሁን? |