እግዚአብሔር ሆይ! መንፈሴ ስለ ዛለብኝ ፈጥነህ መልስ ስጠኝ! ፊትህን ከእኔ አትሰውርብኝ! አለበለዚያ ወደ ጥልቁ ጒድጓድ እንደሚወርዱት ሰዎች እሆናለሁ።
ኤርምያስ 8:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መጽናናት የማይገኝለት ብርቱ ሐዘን ደርሶብኛል፤ ልቤም እጅግ ዝሎአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሐዘኔ የምታጽናናኝ ሆይ፤ ልቤ በውስጤ ዝላለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኀዘኔ የማይጽናና ነው፥ ልቤም በውስጤ ደክሞአል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልባችሁን ታምማችሁ ትቅበዘበዛላችሁ። ከሚያቅበዘብዝ የልብ ሕመማችሁ የሚያድናችሁ የለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኀዘኔ የማይጽናና ነው፥ ልቤም በውስጤ ደክሞአል። |
እግዚአብሔር ሆይ! መንፈሴ ስለ ዛለብኝ ፈጥነህ መልስ ስጠኝ! ፊትህን ከእኔ አትሰውርብኝ! አለበለዚያ ወደ ጥልቁ ጒድጓድ እንደሚወርዱት ሰዎች እሆናለሁ።
ስለ ነቢያት በማስብበት ጊዜ ልቤ በሐዘን ይሰበራል፤ አጥንቶቼም ይንቀጠቀጣሉ፤ ከእግዚአብሔር ከቅዱስ ቃሉ የተነሣ፥ በወይን ጠጅ እንደ ተሸነፈ ሰካራም ሆኜአለሁ፤
ወይ ሥቃይ! ይህን ሁሉ ሥቃይ እንዴት መታገሥ እችላለሁ! ወይ ልቤ! የልቤ አመታት እንዴት ፈጠነ? የጥሩምባ ድምፅና የጦርነት ድምፅ እየሰማሁ፥ ዝም ብዬ መታገሥ አልችልም።
ይህን ሁሉ ስሰማ ሰውነቴ ይርበደበዳል፤ ድምፁም ከንፈሮቼን ያንቀጠቅጣል፤ አጥንቶቼ ይበሰብሳሉ፤ እግሮቼ ከታች ይብረከረካሉ፤ በጠላቶቻችን ላይ መከራ የሚደርስበትን ጊዜ በትዕግሥት እጠባበቃለሁ።