እስራኤላውያንን ከሰጠኋቸው ምድር ተነቃቅለው እንዲባረሩ አደርጋለሁ፤ ስሜ እንዲጠራበት የቀደስኩትንም ይህን ቤተ መቅደስ እተወዋለሁ፤ በየአገሩ የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ እስራኤልን መሳለቂያና መዘባበቻ ያደርጓታል።
ኤርምያስ 7:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ‘ይህ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነው! ይህ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነው፤ ይህ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነው! እኛም በሰላም እንኖራለን!’ በምትሉት ከንቱ ቃላችሁ አትታመኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ይህ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ፣ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ፣ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነው” እያላችሁ በሐሰት ቃል አትታመኑ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ‘የጌታ መቅደስ፥ የጌታ መቅደስ፥ የጌታ መቅደስ ይህ ነው’ እያላችሁ በእነዚህ የሐሰት ቃላት አትታመኑ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔር መቅደስ፥ የእግዚአብሔር መቅደስ ይህ ነው እያላችሁ በሐሰት ቃል በራሳችሁ አትታመኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔር መቅደስ፥ የእግዚአብሔር መቅደስ፥ የእግዚአብሔር መቅደስ ይህ ነው እያላችሁ በሐሰት ቃል አትታመኑ። |
እስራኤላውያንን ከሰጠኋቸው ምድር ተነቃቅለው እንዲባረሩ አደርጋለሁ፤ ስሜ እንዲጠራበት የቀደስኩትንም ይህን ቤተ መቅደስ እተወዋለሁ፤ በየአገሩ የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ እስራኤልን መሳለቂያና መዘባበቻ ያደርጓታል።
ማንም ሰው ክስ ሲመሠርት ትክክለኛውን ጉዳይ ይዞ አይመጣም ወደ ፍርድ ሸንጎም ሲቀርብ ለሕግ ታማኝ ሆኖ አይደለም፤ እነርሱ ከንቱ በሆነ አቤቱታ ላይ ተመሥርተው ውሸትን ይናገራሉ፤ ተንኰልን አስበው በደልን ይፈጽማሉ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሰማይ ዙፋኔ ነው፤ ምድርም የእግሬ ማሳረፊያ ናት፤ ታዲያ ለእኔ ምን ዐይነት ቤት ትሠሩልኛላችሁ? የማርፍበትስ ቦታ ምን ዐይነት ነው?
እኔም ይህንኑ ለሐናንያ እንዲህ ብዬ ነገርኩት፦ “ሐናንያ ሆይ! ስማ፤ አንተን እኮ እግዚአብሔር አላከህም፤ ይህንንም ሁሉ ሕዝብ ሐሰት በሆነ ነገር እንዲተማመን አድርገሃል።
ዕድል ፈንታቸውም ይህ የሚሆንበት ምክንያት አሠቃቂ ኃጢአት በመሥራታቸው ነው፤ ይኸውም ከባልንጀሮቻቸው ሚስቶች ጋር አመንዝረዋል፤ እኔም ያላዘዝኳቸውን የሐሰት ቃል በስሜ ተናግረዋል፤ ይህም እኔ ያልፈቀድኩት ነገር ነው፤ ያደረጉትን ሁሉ ስለማውቅባቸው በእነርሱ ላይ እመሰክርባቸዋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።’ ”
“እነሆ ተሰደው በባቢሎን ወደሚኖሩት ሁሉ ስለ ሽማዕያ የተነገረውን ይህን የትንቢት ቃል እንዲህ ብለህ ላክ፥ ‘ሽማዕያ እኔ ሳልከው የትንቢት ቃል በመናገር በውሸት እንድታምኑ አድርጓችኋል፤
ስለዚህ በሴሎ ያደረግኹትን በዚህ በምትታመኑበት በቤተ መቅደሴ አደርጋለሁ፤ ለቀድሞ አባቶቻችሁና ለእናንተ በሰጠሁት በዚህ ቦታ በሴሎ ያደረግኹትን ደግሜ አደርጋለሁ።
እፍኝ ገብስ እና ቊራሽ እንጀራ ለማግኘት ብላችሁ ሐሰትን ለሚያዳምጡ ለሕዝቤ ሐሰትን እየተናገራችሁ መሞት የማይገባቸውን ሰዎች በመግደልና መኖር የማይገባቸውን ሰዎች እንዲኖሩ በማድረግ ስሜ በሕዝቤ ዘንድ እንዲሰደብ አድርጋችኋል።”
የከተማይቱም ሹማምንት የሚፈርዱት በጉቦ ነው፤ ካህናቱ ያለ ዋጋ አያስተምሩም፤ ነቢያቱም ያለ ገንዘብ ትንቢት አይናገሩም፤ ይህም ሁሉ ሆኖ “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ስለ ሆነ ምንም ዐይነት ክፉ ነገር አይመጣብንም” በማለት በእግዚአብሔር ይመካሉ።
ትዕቢተኞችንና ትምክሕተኞችን ከመካከላችሁ ስለማስወግድ በእኔ ላይ ስለ ፈጸማችሁት በደል በዚያን ጊዜ አታፍሩበትም፤ ከእንግዲህ ወዲህ በተቀደሰው ተራራዬ ላይ አትታበዩም።
ይልቁንስ ንስሓ መግባታችሁን የሚያመለክት ሥራ ሥሩ እንጂ እኛ የአብርሃም ልጆች ነን እያላችሁ በልባችሁ አትመኩ። እግዚአብሔር ከእነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆች ሊያስነሣለት እንደሚችል እነግራችኋለሁ።