ኤርምያስ 6:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀስታቸውንና ሰይፋቸውን አንሥተዋል፤ እነርሱም ምሕረት የሌላቸው ጨካኞች ናቸው፤ ተቀምጠው የሚጋልቡአቸው ፈረሶች፥ የኮቴአቸው ድምፅ እንደ ባሕር ሞገድ ነው። እነሆ እነርሱ ኢየሩሳሌምን ለመውጋት ተዘጋጅተዋል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀስትና ጦር ይዘዋል፤ ጨካኞችና ምሕረት የለሽ ናቸው፤ ፈረሶቻቸውን ሲጋልቡ፣ ድምፃቸው እንደ ተናወጠ ባሕር ነው፤ የጽዮን ልጅ ሆይ፤ ለሰልፍ የታጠቁ ሆነው፣ ሊወጉሽ ይመጣሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቀስትንና ጦርን ይይዛሉ፤ ጨካኞች ናቸው፥ ምሕረትንም አያደርጉም፤ ድምፃቸው እንደ ባሕር ሞገድ ይጮኻል፥ በፈረሶችም ላይ ይቀመጣሉ፤ የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ! ለጦርነት እንደ ተዘጋጀ ሰው እያንዳንዳቸው በአንቺ ላይ ተሰለፉ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቀስትንና ጦርን ይይዛሉ፤ ጨካኞች ናቸው፤ ምሕረትም አያደርጉም፤ ድምፃቸው እንደ ባሕር ሞገድ ይተምማል፤ በሰረገላና በፈረሶችም ላይ ይቀመጣሉ፤ የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ! እንደ እሳት ያጠፉሻል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቀስትንና ጦርን ይይዛሉ፥ ጨካኞች ናቸው፥ ምሕረትንም አያደርጉም፥ ድምፃቸው እንደ ባሕር ይተምማል፥ በፈረሶችም ላይ ይቀመጣሉ፥ የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፥ ለሰልፍ እንደ ተዘጋጀ ሰው እያንዳንዳቸው በአንቺ ላይ ተሰለፉ። |
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እነሆ በሕዝቦች ሁሉ ላይ በየተራ ጥፋት ይመጣል፤ በምድር ዳርቻዎች ሁሉ ላይ ታላቅ ዐውሎ ነፋስ ይነሣል።
‘እነሆ በስተሰሜን ወዳሉት ነገዶችና አገልጋዬ ወደ ሆነው ወደ ባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር መልእክተኛ እልካለሁ፤ ይሁዳንና በውስጥዋ የሚኖሩትን፥ እንዲሁም በጐረቤት ያሉትን ሕዝቦች ይወጉ ዘንድ አመጣቸዋለሁ፤ ይህችን አገር ከነጐረቤቶችዋ አጠፋለሁ፤ ለማየት የሚያስፈሩና መሳለቂያ እስኪሆኑ ድረስ ለዘለዓለም ፍርስራሽ ሆነው እንዲቀሩ አደርጋቸዋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።
ወዳጆቻችሁ ሁሉ ረስተዋችኋል፤ እነርሱ እናንተን አይፈልጉአችሁም፤ ኃጢአታችሁ የበዛ፥ ክፋታችሁም እጅግ ከፍ ያለ ስለ ሆነ፥ እንደ ጠላት መታኋችሁ፤ ያለ ርኅራኄም ቀጣኋችሁ።
“እነሆ የጠላት ሠራዊት እንደ ደመና አንዣቦአል፤ የጦር ሠረገሎቹ እንደ ዐውሎ ነፋስ ፈጣኖች ናቸው፤ ፈረሶቹም ከንስር ይበልጥ ይበራሉ፤ ለእኛ ወዮልን! ጠፍተናል!
ከፈረሰኞችና ከቀስት ወርዋሪዎች ድንፋታ የተነሣ፥ የከተማ ሰው ሁሉ ይሸሻል፤ አንዳንዶቹ ወደ ጫካ ይሮጣሉ፤ የቀሩት በየአለቱ ላይ ይወጣሉ፤ እያንዳንዱ ከተማ ሰው የማይኖርበት ወና ይሆናል፤ የሚኖርበትም አያገኝም።
ቀስታቸውንና ሰይፋቸውን ይዘዋል፤ እነርሱ ምሕረት የሌላቸው ጨካኞች ናቸው፤ ፈረሶቻቸውን ሲጋልቡ፥ ድምፃቸው እንደሚተም ባሕር ነው፤ ባቢሎን ሆይ! እነርሱ በአንቺ ላይ አደጋ ለመጣል ለዘመቻ ተዘጋጅተው እንደሚመጡ ሰዎች ወደ አንቺ እየመጡ ነው።
ጠላቶችዋም እንዲህ ይላሉ፦ “ኢየሩሳሌምን ለመውጋት እንዘጋጅ! ተነሡ! በእኩለ ቀን ላይ አደጋ እንጣልባት! እንዲያውም ዘግይተናል፤ ቀኑ ሊመሽ ተቃርቦአል፤ ፀሐይም ልትጠልቅ በመቃረብዋ ጥላው እየረዘመ ሄዶአል፤
ጠላቶቻችን እስከ ዳን ከተማ ደርሰዋል፤ ፈረሶቻቸው ሲያንኮራፉ ድምፃቸው ይሰማል፤ ሰንጋ ፈረሶቻቸውም ሲያሽካኩ ምድር ትናወጣለች፤ ጠላቶቻችን የመጡት ምንም ሳያስቀሩ ሕዝባችንንና ከተሞቻችንን እንዲሁም በውስጡ ያለውን ነገር ሁሉ ለማጥፋት ነው።”