ስለ ሞአብ ከልቤ አለቅሳለሁ፤ ሕዝቡ ወደ ጾዓርና ወደ ዔግላት ሸሊሺያ ኰበለሉ፤ ጥቂቶችም ወደ ሉሒት አቀበት ወጡ፤ በሚወጡበትም ጊዜ ያለቅሱ ነበር፤ ሌሎች ደግሞ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ስለ ጥፋታቸው እያለቀሱ ወደ ሖሮናይም ለማምለጥ ይሞክራሉ።
ኤርምያስ 51:54 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ከባቢሎን ጩኸት፥ ከከለዳውያን ምድርም የታላቅ ጥፋት ድምፅ ይሰማል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከባቢሎን ጩኸት፣ ከባቢሎናውያንም ምድር፣ የታላቅ ጥፋት ድምፅ ይሰማል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከባቢሎን ጩኸት፥ ከከለዳውያንም ምድር የታላቅ ጥፋት ድምፅ ተሰምቶአል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ከባቢሎን የጩኸት ድምፅ፥ ከከለዳውያንም ምድር የታላቅ ጥፋት ድምፅ ተሰምቶአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከባቢሎን ጩኸት፥ ከከለዳውያንም ምድር የታላቅ ጥፋት ድምፅ ተሰምቶአል። |
ስለ ሞአብ ከልቤ አለቅሳለሁ፤ ሕዝቡ ወደ ጾዓርና ወደ ዔግላት ሸሊሺያ ኰበለሉ፤ ጥቂቶችም ወደ ሉሒት አቀበት ወጡ፤ በሚወጡበትም ጊዜ ያለቅሱ ነበር፤ ሌሎች ደግሞ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ስለ ጥፋታቸው እያለቀሱ ወደ ሖሮናይም ለማምለጥ ይሞክራሉ።
እነርሱ በደረቅ ቦታ ላይ እንዳለ ሙቀት ሕዝብን ይጐዳሉ፤ አምላክ ሆይ! አንተ ግን የባዕዳንን ድንፋታ ዝም አሰኘህ፤ የደመና ጥላ ቃጠሎን እንደሚያበርድ የጋጠወጦችን ዘፈን ጸጥ አደረግህ።
ወታደሮቻቸውን፥ ወደ ማረጃ ቦታ ወርደው እንደሚታረዱ የዕርድ ኰርማዎች ወስዳችሁ ግደሉ፤ የሚቀጡበት ጊዜ ስለ ደረሰ ለባቢሎን ሕዝብ ወዮላቸው!
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በዚያን ቀን ከኢየሩሳሌም ቅጽር በዓሣ በር በኩል ኡኡታ ይሰማል፤ ከአዲሱም አደባባይ የዋይታ ድምፅ ያስተጋባል፤ በኰረብቶችም አካባቢ ከፍተኛ ሽብር ይሰማል።