በንግድ የምታገኘውም ገንዘብ ሁሉ ለእግዚአብሔር የተለየ ይሆናል፤ ለራስዋ ተቀማጭ ሳታደርግ የእግዚአብሔር አገልጋዮች በሚያስፈልጋቸው ምግብና በጥሩ ልብስ ያውሉታል።
ኤርምያስ 49:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ከጊዜ በኋላ የአሞናውያንን ንብረት እመልሳለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከዚያ በኋላ ግን፣ የአሞናውያንን ምርኮ እመልሳለሁ” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ነገር ግን ከዚያ በኋላ የአሞንን ልጆች ምርኮ እመልሳለሁ፥ ይላል ጌታ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ከዚያ በኋላ የአሞንን ልጆች ምርኮ እመልሳለሁ ይላል እግዚአብሔር።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ከዚያ በኋላ የአሞንን ልጆች ምርኮ እመልሳለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር። |
በንግድ የምታገኘውም ገንዘብ ሁሉ ለእግዚአብሔር የተለየ ይሆናል፤ ለራስዋ ተቀማጭ ሳታደርግ የእግዚአብሔር አገልጋዮች በሚያስፈልጋቸው ምግብና በጥሩ ልብስ ያውሉታል።
ነገር ግን ከአገራቸው ካወጣኋቸው በኋላ እንደገና ምሕረት አደርግላቸዋለሁ፤ እያንዳንዱንም ሕዝብ ወደ ገዛ ምድሩና ወደ ገዛ አገሩ መልሼ አመጣዋለሁ።
ሊገድሉአቸው ለሚፈልጉ ለባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆርና ለሠራዊቱ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ ሆኖም ዘግየት ብሎ ከዚህ በፊት እንደሆነው ሁሉ ግብጽ እንደገና የሰዎች መኖሪያ ትሆናለች፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”
እግዚአብሔር ስለ ኢየሩሳሌም እንዲህ አለ፦ “ለሰዶምና ለመንደሮችዋ፥ ለሰማርያና መንደሮችዋ የቀድሞ ሀብታቸውን እንደምመልስ የአንቺንም ሀብት እመልስልሻለሁ።
ውብ የሆነችውንም የተስፋይቱን ምድር ይወራል፤ ብዙ አገሮችም በእርሱ እጅ ይወድቃሉ፤ ነገር ግን የኤዶም፤ የሞአብና የዐሞን አገሮች ከወረራው ያመልጣሉ።