Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 46:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ሊገድሉአቸው ለሚፈልጉ ለባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆርና ለሠራዊቱ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ ሆኖም ዘግየት ብሎ ከዚህ በፊት እንደሆነው ሁሉ ግብጽ እንደገና የሰዎች መኖሪያ ትሆናለች፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ነፍሳቸውን ለሚሹት ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆርና ለጦር መኰንኖቹ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ግን ግብጽ እንደ ቀድሞው ዘመን የሰው መኖሪያ ትሆናለች” ይላል እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ነፍሳቸውንም በሚሽዋት ሰዎች እጅ፥ በባቢሎንም ንጉሥ በናቡከደነፆር እጅ፥ በባርያዎቹም እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ ከዚያም በኋላ አንደ ቀድሞው ዘመን የሰው መኖሪያ ትሆናለች፥ ይላል ጌታ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ነፍ​ሳ​ቸ​ው​ንም በሚ​ፈ​ልጉ ሰዎች እጅ፥ በባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ በና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር እጅ፥ በአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ከዚ​ያም በኋላ እንደ ቀድ​ሞው ዘመን የሰው መኖ​ሪያ ትሆ​ና​ለች፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ነፍሳቸውንም በሚፈልጉ ሰዎች እጅ፥ በባቢሎንም ንጉሥ በናቡከደነፆር እጅ፥ በባሪያዎቹም እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፥ ከዚያም በኋላ አንደ ቀድሞው ዘመን የሰው መኖሪያ ትሆናለች፥ ይላል እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 46:26
7 Referencias Cruzadas  

እነርሱን በጭካኔ ለሚገዛቸው ንጉሥ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ እኔ ጌታ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”


እኔ የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን ቀድሞ ጠላቱ ለነበረና ይገድለው ዘንድ ለሚፈልገው ለባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር አሳልፌ እንደ ሰጠሁት ሁሉ፥ ሖፍራ ተብሎ የሚጠራውን የግብጽ ንጉሥ ሊገድሉት ለሚፈልጉ ጠላቶቹ አሳልፌ እሰጠዋለሁ።”


“ሆኖም የሞአብን ንብረት የምመልስበት ጊዜ ይመጣል፤” ይላል እግዚአብሔር፤ ስለ ሞአብ የተወሰነው ፍርድ እዚህ ላይ ይጠናቀቃል።


ሆኖም የዔላምን ንብረት የምመልስበት ጊዜ ይመጣል፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”


ልዑል እግዚአብሔር ለግብጽ ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ “የባቢሎን ንጉሥ ሰይፍ ይመጣብሃል።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ፈራርሶ እንደ ወደቀ ቤት የነበረውን የዳዊትን ሥርወ መንግሥት መልሼ የማቋቊምበት ጊዜ ይመጣል፤ ቅጽሩን እጠግናለሁ፤ ፍርስራሹንም አድሳለሁ፤ በቀድሞ ዘመን እንደ ነበረውም አድርጌ እሠራዋለሁ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos