ካወጡአቸውም በኋላ ከመላእክቱ አንዱ “ሕይወታችሁን አድኑ! ወደ ኋላ አትመልከቱ! በሸለቆው ውስጥ አትዘግዩ፤ እንዳትሞቱ ወደ ተራራው ሽሹ!” አላቸው።
ኤርምያስ 48:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስ በርሳቸውም ‘ሕይወታችሁን ለማትረፍ በፍጥነት ሩጡ! በበረሓም እንደሚኖር የሜዳ አህያ ብረሩ!’ ይባባላሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሽሹ፤ ሕይወታችሁንም አትርፉ! በምድረ በዳ እንዳለ ቍጥቋጦ ሁኑ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሸሽታችሁ ራሳችሁን አድኑ፤ በምድረ በዳ እንዳለ ቁጥቋጦ ሁኑ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ሸሽታችሁ ራሳችሁን አድኑ፤ እንደ ሜዳ አህያ በምድረ በዳ ተቀመጡ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሸሽታችሁ ራሳችሁን አድኑ፥ በምድረ በዳ እንዳለ ቍጥቋጦ ሁኑ። |
ካወጡአቸውም በኋላ ከመላእክቱ አንዱ “ሕይወታችሁን አድኑ! ወደ ኋላ አትመልከቱ! በሸለቆው ውስጥ አትዘግዩ፤ እንዳትሞቱ ወደ ተራራው ሽሹ!” አላቸው።
እንዲህ ዐይነቱ ሰው ማንም ሊኖርበት በማይችል በጨው ምድርና በበረሓ እንደሚበቅል ቊጥቋጦ ነው፤ በሕይወቱ ሙሉ ምንም መልካም ነገርን አያገኝም።
ከባቢሎን ሽሹ! ሕይወታችሁንም ለማትረፍ አምልጡ! ባቢሎን በሠራችው ኃጢአት ምክንያት በከንቱ አትለቁ! እኔ ለእርስዋ የሚገባትን ቅጣት በመስጠት የምበቀልበት ጊዜ ነው።
ሊጠመቁ ወደ እርሱ የመጡትን ብዙ ሕዝብ ዮሐንስ እንዲህ ይላቸው ነበር፦ “እናንተ የመርዘኛ እባብ ልጆች! ከሚመጣው ከእግዚአብሔር ቊጣ እንድታመልጡ ማን አስጠነቀቃችሁ?
በዚሁ ዐይነት እግዚአብሔር የማይለወጡትንና የማይዋሽባቸውን ሁለቱን ነገሮች፥ ማለትም ተስፋውንና መሐላውን ሰጥቶናል፤ በእነዚህም በሁለቱ ነገሮች አማካይነት በፊታችን ያለውን ተስፋ አጥብቀን መያዝ እንድንችል መጠጊያ ለማግኘት ወደ እርሱ የሸሸን እኛ ታላቅ መጽናናትን እናገኛለን።