Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤርምያስ 17:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 እንዲህ ዐይነቱ ሰው ማንም ሊኖርበት በማይችል በጨው ምድርና በበረሓ እንደሚበቅል ቊጥቋጦ ነው፤ በሕይወቱ ሙሉ ምንም መልካም ነገርን አያገኝም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 በምድረ በዳ እንዳለ ቍጥቋጦ ይሆናል፤ መልካም ነገር ሲመጣ አያይም፤ ሰው በሌለበት በጨው ምድር፣ በምድረ በዳ በደረቅ ስፍራ ይቀመጣል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 እርሱ በምድረ በዳ እንዳለ ቁጥቋጦ ነው፥ መልካምም በመጣ ጊዜ አያይም፤ ሰውም በማይቀመጥበት፥ ጨው ባለበት ምድር፥ በምድረ በዳ በደርቅ ስፍራ ይቀመጣል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 በም​ድረ በዳ እንደ አለ ቍጥ​ቋጦ ይሆ​ናል፤ መል​ካ​ምም በመጣ ጊዜ አያ​ይም፤ ሰውም በማ​ይ​ኖ​ር​በት፥ ጨው ባለ​በት ምድር በም​ድረ በዳ በደ​ረቅ ስፍራ ይቀ​መ​ጣል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 በምድረ በዳ እንዳለ ቍጥቋጦ ይሆናል፥ መልካምም በመጣ ጊዜ አያይም፥ ሰውም በሌለበት፥ ጨው ባለበት ምድር በምድረ በዳ በደርቅ ስፍራ ይቀመጣል።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 17:6
17 Referencias Cruzadas  

የወይራ ዘይት እንደ ጐርፍ ሲወርድ፥ ማርና ወተት እንደ ጅረት ውሃ ሲፈስ ሳያይ ይሞታል።


ክፉዎች ግን እንደዚህ አይደሉም፤ እነርሱ ነፋስ ጠርጎ እንደሚወስደው ገለባ ናቸው።


ምድሪቱም ሁሉ በዲንና በጨው ትሸፈናለች፤ ምንም ነገር አይተከልባትም፤ ምንም ነገር አታበቅልም፤ እግዚአብሔር በኀይለኛ ቊጣው እንደ ደመሰሳቸው እንደ ሰዶምና ገሞራ፥ እንደ አዳማና እንደ ጺባዮ ትሆናለች።


እርስ በርሳቸውም ‘ሕይወታችሁን ለማትረፍ በፍጥነት ሩጡ! በበረሓም እንደሚኖር የሜዳ አህያ ብረሩ!’ ይባባላሉ።


በረሓን ለእነርሱ መሰማሪያ አድርጌ ሰጥቼአለሁ፤ ጨው ባለበት ሜዳም እንዲኖሩ አድርጌአቸዋለሁ።


እኔ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሕያው እንደ መሆኔ፥ ሞአብ እንደ ሰዶም አሞንም እንደ ገሞራ ይሆናሉ፤ ምድሪቱም በዳዋና በጨው ጒድጓድ ተወራ ለዘለቄታ ባድማ ትሆናለች፤ ከሞት የተረፈው ሕዝቤ ይበዘብዛቸዋል ንብረታቸውንም ይወርሳል።”


ውጊያውም ቀኑን ሙሉ ቀጥሎ ዋለ፤ አቤሜሌክ ከተማይቱን ይዞ ሕዝብዋን ሁሉ ገደለ፤ ከተማይቱን አፈራረሰ፤ በምድሪቱም ላይ ጨው ዘራባት።


ነገር ግን ረግረጉና እቋሪው ውሃ የጨው መከማቻ እንደ ሆነ ይቀራል እንጂ የጠራ ውሃ አይሆንም።


በመጨረሻም ቅጠሉ እንደ ረገፈ የወርካ ዛፍና ውሃ እንደሌለው የአትክልት ቦታ ትሆናላችሁ።


ክፉዎች እንደ ሣር ቶሎ ቢያድጉም፥ ክፉ አድራጊዎች ቢበለጽጉም፥ እነርሱ ለዘለዓለሙ ይጠፋሉ።


በዚህ ጊዜ የንጉሡ የቅርብ ባለሟል የሆነ አገልጋዩ ኤልሳዕን፥ “እግዚአብሔር ራሱ የሰማይ መስኮቶችን ከፍቶ እህልን እንደ ዝናብ ቢያዘንብ እንኳ ይህ ሊሆን ከቶ አይችልም!” ሲል በመጠራጠር ተናገረ። ኤልሳዕም “ያን እህል በዐይንህ ታያለህ፤ ነገር ግን ከእርሱ ምንም ነገር አትቀምስም!” አለው።


እዚያ ከሚኖሩት ሰዎች ክፋት የተነሣ ፍሬያማዋን አገር እንደ ጨው ምድር የማታፈራ አደረጋት።


ስለዚህም እኔ እግዚአብሔር እርሱንና ዘሮቹን ሁሉ እቀጣለሁ፤ ከእንግዲህ ይህ ሰው በእናንተ መካከል የሚተርፍ ዘር አይኖረውም፤ እርሱ ራሱም ለሕዝቤ የማደርገውን መልካም ነገር ሁሉ ለማየት የመኖር ተስፋ የለውም፤ ምክንያቱም እርሱ እናንተን በእኔ ላይ እንድታምፁ አድርጓችኋል፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።’ ”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios