ኤርምያስ 40:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከይሁዳ የጦር መኰንኖችና ወታደሮች ጥቂቶቹ ገና እጃቸውን አልሰጡም ነበር፤ እነርሱም የባቢሎን ንጉሥ ገዳልያን በሀገሪቱ ላይ ገዢ አድርጎ እንደ ሾመውና ወደ ባቢሎን ሳይወሰዱ በሀገሪቱ ለቀሩት ድኾች ኀላፊ ያደረገው መሆኑን ሰሙ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በየሜዳው የነበሩት የጦር መኰንኖችና ሰዎቻቸው ሁሉ የባቢሎን ንጉሥ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በምድሪቱ ላይ ገዥ አድርጎ እንደ ሾመውና ወደ ባቢሎን በምርኮ ባልተወሰዱት በምድሪቱ ድኾች ወንዶች፣ ሴቶችና ልጆች ላይ ሥልጣን እንደ ሰጠው በሰሙ ጊዜ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በየሜዳውም የነበሩት የጭፍራ አለቆችና ሰዎቻቸው ሁሉ የባቢሎን ንጉሥ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በምድሪቱ ላይ እንደ ሾመ፥ ወንዶችንና ሴቶችን ሕፃናትንም፥ ወደ ባቢሎን ያልተማረኩትን በምድሪቱ ያሉትን ድሆች፥ እንዲገዛ ኀላፊነት እንደሰጠው በሰሙ ጊዜ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በየሜዳው የነበሩት የጭፍራ አለቆችና ሰዎቻቸው ሁሉ የባቢሎን ንጉሥ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በሀገሩ ላይ እንደ ሾመ፥ ወንዶችንና ሴቶችን ልጆችንም፥ ወደ ባቢሎን ያልተማረኩትንም የምድርን ድሆች እንዳስጠበቀ በሰሙ ጊዜ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በየሜዳውም የነበሩት የጭፍራ አለቆችና ሰዎቻቸው ሁሉ የባቢሎን ንጉሥ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በምድር ላይ እንደ ሾመ፥ ወንዶችንና ሴቶችን ልጆችንም፥ ወደ ባቢሎን ያልተማረኩትን የምድርን ድሆች፥ እንዳስጠበቀ በሰሙ ጊዜ፥ የናታንያ ልጅ እስማኤል፥ |
የከተማይቱ ቅጽሮች ተጣሱ፤ የባቢሎን ወታደሮች ከተማይቱን ዙሪያውን ከበው በመያዝ ቢጠብቁም እንኳ የይሁዳ ንጉሥ ወታደሮች በሌሊት አምልጠው ወጡ፤ ወደ ንጉሡ የአትክልት ቦታ ከሚያስገባው መንገድ ተነሥተው ሁለቱን ቅጽሮች በሚያያይዘው የቅጽር በር በኩል በማለፍ ወደ ዮርዳኖስ ሸለቆ አቅጣጫ ሸሹ።
ታስሬበት ከነበረው በቤተ መንግሥቱ ግቢ ከሚገኘው ዘብ ጠባቂዎች ክፍል እንድወጣ አስደረገ፤ እኔም የሳፋን የልጅ ልጅ በሆነው በአሒቃም ልጅ በገዳልያ እጅ ወደ ቤቴ ተወሰድኩ፤ እኔም ከሕዝቤ ጋር በዚያ ኖርኩ።
ንጉሥ ሴዴቅያስና ወታደሮቹ ሁሉ የሆነውን ነገር ባዩ ጊዜ በሌሊት ከከተማይቱ ወጥተው ለማምለጥ ሞከሩ፤ በቤተ መንግሥቱ የአትክልት ቦታ በኩል አድርገው ሁለቱን ቅጽሮች በሚያገናኘው መውጫ በር አቋርጠው ወደ ዮርዳኖስ ሸለቆ አቅጣጫ አመለጡ።
በመጨረሻም የባቢሎን ንጉሥ የክብር ዘቡ አዛዥ ናቡዛርዳን በከተማ የቀሩትን ሕዝብና ቀደም ብለው ወደ እርሱ ከድተው የገቡትንም ሁሉ በአንድነት ሰብስቦ በእስረኛነት ወደ ባቢሎን ወሰዳቸው፤
በዚሁ ዓመት በሰባተኛው ወር ከንጉሡ ታላላቅ ባለ ሥልጣኖች አንዱ፥ የንጉሣውያን ቤተሰብ አባል የሆነውና የኤሊሻማዕ የልጅ ልጅ የነታንያ ልጅ እስማኤል ከዐሥር ሰዎች ጋር ሆኖ አገረ ገዢውን ገዳልያን ለመጐብኘት ወደ ምጽጳ ሄደ፤ ሁሉም በማዕድ ተቀምጠው አብረው ምግብ እየተመገቡ ሳሉ፥
ከዚያም በኋላ የንጉሡን ሴቶች ልጆችና የቀሩትንም ሕዝብ በምጽጳ አሰረ፤ እነዚህም ሁሉ የባቢሎን ንጉሥ ጦር አዛዥ ናቡዛርዳን በገዳልያ ሥር እንዲጠበቁ ዐደራ የተሰጡ ነበሩ፤ እስማኤል ግን እነዚህን ሁሉ ማርኮ ወደ ዐሞን ግዛት አቅጣጫ ተሻገረ።
ወንዶችንም ሴቶችንም፥ ሕፃናትንና የንጉሡን ሴቶች ልጆች ጭምር ወሰዱአቸው፤ የባቢሎን ጦር አዛዥ ናቡዛርዳን በገዳልያ ሥልጣን ሥር እንዲጠበቁ የተዋቸውን ሁሉ፥ እንዲሁም እኔንና ባሮክን ወሰዱ።