ምድሪቱ ሁሉ በፊትህ አይደለችምን? ከእኔ ተለይተህ ሂድ፤ አንተ ወደ ግራ ብትሄድ እኔ ወደ ቀኝ እሄዳለሁ፤ ወይም አንተ ወደ ቀኝ ብትሄድ እኔ ወደ ግራ እሄዳለሁ።”
ኤርምያስ 40:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነሆ እኔ በእጅህ ላይ ያለውን ሰንሰለት ፈትቼ ነጻ አደርግሃለሁ፤ ከእኔ ጋር ወደ ባቢሎን ለመውረድ ብትፈልግ እንደ ወደድክ አድርግ፤ እኔም ለአንተ እንክብካቤ አደርግልሃለሁ፤ ወደዚያ ለመሄድ ካልፈለግህ ግን መቅረት ትችላለህ፤ እነሆ አገሪቱ በሞላ በፊትህ ስለ ሆነች ወደ መረጥከው ቦታ መሄድ ትችላለህ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነሆ፤ ዛሬ የእጅህን ሰንሰለት ፈታሁልህ። ከፈለግህ ከእኔ ጋራ ወደ ባቢሎን ና፤ እኔም እንከባ ከብሃለሁ፤ ካልፈለግህ ግን አትምጣ። እነሆ፤ አገሪቱ ሁሉ በፊትህ ናት፤ ወደ ቀናህ ሂድ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁን ደግሞ፥ እነሆ፥ በእጅህ ካለው ሰንሰለት ዛሬ ፈታሁህ። ከእኔ ጋር ወደ ባቢሎን መምጣት መልካም መስሎ ቢታይህ፥ ና፥ እኔም በበጎ ዐይን እመለከትሀለው፤ ከእኔ ጋር ወደ ባቢሎን መምጣት መልካም መስሎ ባይታይህ ግን፥ ቅር፤ እነሆ ተመልከት፥ አገሪቱ ሁሉ በፊትህ ናት፤ ለመሄድ መልካም መስሎ ወደሚታይህ ትክክልም ነው ብለህ ወደምታስበው ስፍራ ወደዚያ ሂድ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም እነሆ በእጅህ ካለችው ሰንሰለት ዛሬ ፈታሁህ። ከእኔ ጋር ወደ ባቢሎን መምጣት መልካም መስሎ ቢታይህ፥ ና፤ እኔም በመልካም አይሃለሁ፤ ከእኔ ጋር ወደ ባቢሎን መምጣት መልካም መስሎ ባይታይህ ግን፥ ተቀመጥ፤ ተመልከት፥ እነሆ፥ ሀገሪቱ ሁሉ በፊትህ ናት፤ ትሄድ ዘንድ መልካም መስሎ በሚታይህና ደስ በሚያሰኝህም ስፍራ ተቀመጥ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንም፥ እነሆ፥ በእጅህ ካለችው ሰንሰለት ዛሬ ፈታሁህ። ከእኔ ጋር ወደ ባቢሎን መምጣት መልካም መስሎ ቢታይህ፥ ና፥ እኔም በመልካም አይሃለሁ፥ ከእኔ ጋር ወደ ባቢሎን መምጣት መልካም መስሎ ባይታይህ ግን፥ ተቀመጥ፥ እነሆ፥ አገሪቱ ሁሉ በፊትህ ናት፥ ትሄድ ዘንድ መልካም መስሎ ወደሚታይህ ደስ ወደሚያሰኝህም ስፍራ ሂድ። |
ምድሪቱ ሁሉ በፊትህ አይደለችምን? ከእኔ ተለይተህ ሂድ፤ አንተ ወደ ግራ ብትሄድ እኔ ወደ ቀኝ እሄዳለሁ፤ ወይም አንተ ወደ ቀኝ ብትሄድ እኔ ወደ ግራ እሄዳለሁ።”
እነሆ፥ መላው የግብጽ ምድር የአንተ ነው፤ ስለዚህ አባትህና ወንድሞችህ ምርጥ በሆነችው በጌሴም ምድር እንዲኖሩ አድርግ። ከእነርሱ መካከል ልዩ ችሎታ ያላቸው ሰዎች ካሉ፥ በእኔ እንስሶች ላይ የበላይ ኀላፊዎች አድርገህ ሹማቸው።”
እኔም “አንተ እንደምትለው እኔ ከድቼ የምሄድ ሰው አይደለሁም!” ብዬ መለስኩለት፤ ዪሪያ ግን ሊያዳምጠኝ አልፈለገም፤ ይልቁንም አስሮ ወደ ባለ ሥልጣኖች ወሰደኝ፤