እግዚአብሔርም ኤልያስን “ካለህበት ወጥተህ በተራራው ጫፍ ላይ በፊቴ ቁም” አለው፤ ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር በአጠገቡ አለፈ፤ ብርቱ ነፋስም በፊቱ በመላክ ኰረቶችን ሰነጣጠቀ፤ አለቶችንም ሰባበረ፤ እግዚአብሔር ግን በነፋሱ ውስጥ አልነበረም፤ ነፋሱም ከቆመ በኋላ ምድሪቱ ተናወጠች፤ እግዚአብሔር ግን በምድሪቱ ነውጥ ውስጥ አልነበረም፤
ኤርምያስ 4:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ተራራዎችን ተመለከትኩ፤ እነርሱም በመንቀጥቀጥ ላይ ናቸው፤ ኰረብቶችንም አየሁ፤ እነሆ ወዲያና ወዲህ በመናጥ ላይ ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ተራሮችን ተመለከትሁ፣ እነሆ ይንቀጠቀጡ ነበር፤ ኰረብቶችም ሁሉ ተናጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተራሮችን አየሁ፥ እነሆም፥ ተንቀጠቀጡ፥ ኮረብቶችም ሁሉ ተናወጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተራሮችን ተመለከትሁ፤ እነሆም ይንቀጠቀጡ ነበር፤ ኮረብቶችም ሁሉ ይናወጡ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ተራሮችን አየሁ፥ እነሆም፥ ተንቀጠቀጡ፥ ኮረብቶችም ሁሉ ተናወጡ። |
እግዚአብሔርም ኤልያስን “ካለህበት ወጥተህ በተራራው ጫፍ ላይ በፊቴ ቁም” አለው፤ ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር በአጠገቡ አለፈ፤ ብርቱ ነፋስም በፊቱ በመላክ ኰረቶችን ሰነጣጠቀ፤ አለቶችንም ሰባበረ፤ እግዚአብሔር ግን በነፋሱ ውስጥ አልነበረም፤ ነፋሱም ከቆመ በኋላ ምድሪቱ ተናወጠች፤ እግዚአብሔር ግን በምድሪቱ ነውጥ ውስጥ አልነበረም፤
እግዚአብሔር በእሳት ስለ ወረደበት መላው የሲና ተራራ በጢስ ተሞላ። ጢሱም ከእሳት ምድጃ እንደሚወጣ ዐይነት ሆኖ ወደ አየር ተትጐለጐለ፤ ሰዎቹም እጅግ ፈርተው ተንቀጠቀጡ።
ምድር እንደ ሰከረ ሰው ትንገዳገዳለች፤ በዐውሎ ነፋስ እንደ ተገፋ ጎጆም ትናወጣለች፤ እርስዋም የኃጢአትዋ ሸክም ስለሚጫናት ትወድቃለች፤ መነሣትም አትችልም።
እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ በጣም ተቈጥቶአል፤ በኀያልነቱም ይቀጣቸዋል፤ ተራራዎች ይናወጣሉ፤ የሞቱ ሰዎችም አስከሬን እንደ ጥራጊ በየመንገዱ ዳር ይወድቃል፤ ይህም ሁሉ ሆኖ የእግዚአብሔር ቊጣ አይበርድም፤ እንደገናም ሊቀጣቸው ተዘጋጅቶአል።
እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ግን እውነተኛ አምላክ ነህ፤ አንተ ሕያው አምላክ፥ ዘለዓለማዊ ንጉሥ ነህ፤ አንተ በምትቈጣበት ጊዜ ዓለም ይናወጣል፤ የአሕዛብ መንግሥታትም የአንተን ቊጣ ችለው አይቆሙም።
ጠላቶቻችን እስከ ዳን ከተማ ደርሰዋል፤ ፈረሶቻቸው ሲያንኮራፉ ድምፃቸው ይሰማል፤ ሰንጋ ፈረሶቻቸውም ሲያሽካኩ ምድር ትናወጣለች፤ ጠላቶቻችን የመጡት ምንም ሳያስቀሩ ሕዝባችንንና ከተሞቻችንን እንዲሁም በውስጡ ያለውን ነገር ሁሉ ለማጥፋት ነው።”
እኔም እንዲህ አልኩ፦ “ሁሉም ወና ስለ ሆኑና በእነርሱም ላይ የሚዘዋወርባቸው ስለሌለ፥ ስለ ተራራዎች አዝናለሁ፤ ስለ ሜዳዎችም አለቅሳለሁ፤ የከብቶች ድምፅ ዳግመኛ አይሰማም፤ የሰማይ ወፎችና የምድር አራዊት ሁሉ ሸሽተው ጠፍተዋል።”
እያንዳንዱ የዓሣና የወፍ ዐይነት፥ እያንዳንዱም አውሬና እንስሳ በምድር የሚኖር እያንዳንዱ ሰው እኔን በመፍራቱ ይንቀጠቀጣል፤ ተራራዎች ይወድቃሉ፤ ገደሎች ተፈረካክሰው ይናዳሉ፤ እያንዳንዱም የቅጽር ግንብ ይደረመሳል።
በዚያን ጊዜ ሰም በእሳት እንደሚቀልጥና፥ ውሃም ከከፍተኛ ቦታ ወደ ታች እንደሚወርድ እንዲሁም ተራራዎች ከእርሱ ሥር ይቀልጣሉ፤ ሸለቆዎችም ይከፈታሉ።
ተራራዎች አንተን አይተው በፍርሃት ተንቀጠቀጡ፤ የዝናብም ጐርፍ ምድርን እየጠራረገ አለፈ፤ ውቅያኖስ ከፍተኛ ድምፅ አሰማ፤ ማዕበሉም ወደ ላይ ከፍ ከፍ አለ።
እርሱ ሲቆም ምድር ትናወጣለች፤ እርሱ ሲመለከታቸው ሕዝቦች ይንቀጠቀጣሉ፤ የጥንቱ ተራራዎች ይናዳሉ፤ ከጥንት ጀምሮ የእርሱ መረማመጃ የነበሩት ኰረብቶች ወደ ታች ይሰጥማሉ።