ኤርምያስ 39:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ናቡከደነፆር የክብር ዘብ አዛዡን ናቡዛርዳንን እንዲህ ሲል አዘዘው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በክብር ዘበኞቹ አዛዥ በናቡዘረዳን በኩል ስለ ኤርምያስ እንዲህ የሚል ትእዛዝ ሰጠ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የባቢሎንም ንጉሥ ናቡከደነፆር ስለ ኤርምያስ በዘበኞቹ አለቃ በናቡዘረዳን በኩል እንዲህ ሲል ትእዛዝን ሰጠ፦ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የባቢሎንም ንጉሥ ናቡከደነፆር የአዛዦች አለቃ ናቡዛርዳንን ስለ ኤርምያስ እንዲህ ሲል አዘዘው፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የባቢሎንም ንጉሥ ናቡከደነፆር ስለ ኤርምያስ፦ ውሰደውና በመልካም ተመልከተው፥ የሚሻውንም ነገር አድርግለት እንጂ ክፉን ነገር አታድርግበት ብሎ የዘበኞቹን አለቃ ናቡዘረዳንን አዘዘ። |
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “በእርግጥ ለመልካም ዓላማ እታደግሃለሁ፤ በችግርና በመከራ ጊዜ ጠላቶችህ አንተን እንዲለማመጡ አደርጋለሁ።
እነርሱን መቋቋም እንድትችል እንደ ነሐስ ግንብ አበረታሃለሁ፤ አንተን ለማዳንና ለመታደግ ከአንተ ጋር ስለ ሆንኩ አደጋ ቢጥሉብህም እንኳ አያሸንፉህም።
የክብር ዘብ አዛዡ ናቡዛርዳን እኔን በራማ ነጻ ከለቀቀኝ በኋላ እግዚአብሔር ተናገረኝ፤ ከዚያ በፊት እኔ እዚያ የተወሰድኩት አሁን ከኢየሩሳሌምና ከይሁዳ በመማረክ ታስረው ወደ ባቢሎን ከተወሰዱት ሕዝብ ሁሉ ጋር በሰንሰለት ታስሬ ነበር።
እነሆ እኔ በእጅህ ላይ ያለውን ሰንሰለት ፈትቼ ነጻ አደርግሃለሁ፤ ከእኔ ጋር ወደ ባቢሎን ለመውረድ ብትፈልግ እንደ ወደድክ አድርግ፤ እኔም ለአንተ እንክብካቤ አደርግልሃለሁ፤ ወደዚያ ለመሄድ ካልፈለግህ ግን መቅረት ትችላለህ፤ እነሆ አገሪቱ በሞላ በፊትህ ስለ ሆነች ወደ መረጥከው ቦታ መሄድ ትችላለህ።”
ናቡከደነፆር በባቢሎን በነገሠ በዐሥራ ዘጠነኛው ዓመት በአምስተኛው ወር በዐሥረኛው ቀን የንጉሡ የክብር ዘብ አዛዥ የሆነው ናቡዛርዳን ኢየሩሳሌም ገባ፤
ጳውሎስን ይጠብቅ የነበረውንም መቶ አለቃ “እምብዛም ነጻነት ሳትከለክለው በጥንቃቄ ጠብቀው፤ ወዳጆቹም የሚያስፈልገውን ሁሉ ይዘውለት ሲመጡ አትከልክልበት” አለው።