ንጉሥ ኢኮንያን ከእናቱ፥ ከልዑላን መሳፍንቱ፥ ከጦር አዛዦቹና ባለሟሎቹ ከሆኑት ባለሥልጣኖች ጋር ቀርቦ ለባቢሎናውያን እጁን ሰጠ፤ ናቡከደነፆር በነገሠ በስምንተኛው ዓመት ኢኮንያንን እስረኛ አድርጎ ያዘው፤
ኤርምያስ 37:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር የኢዮስያስን ልጅ ሴዴቅያስን የኢዮአቄም ልጅ በነበረው በኢኮንያን ምትክ በይሁዳ ላይ አነገሠው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር የኢዮስያስን ልጅ ሴዴቅያስን በይሁዳ ላይ አነገሠው፤ እርሱም በኢዮአቄም ልጅ በኢኮንያን ፈንታ ነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የባቢሎንም ንጉሥ ናቡከደነፆር በይሁዳ ምድር ላይ ያነገሠው የኢዮስያስ ልጅ ሴዴቅያስ በኢዮአቄም ልጅ በኢኮንያን ፋንታ ነገሠ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በይሁዳ ያነገሠው የኢዮስያስ ልጅ ሴዴቅያስ በኢዮአቄም ልጅ በኢኮንያን ፋንታ ነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የባቢሎንም ንጉሥ ናቡከደነፆር በይሁዳ ያነገሠው የኢዮስያስ ልጅ ሴዴቅያስ በኢዮአቄም ልጅ በኢኮንያን ፋንታ ነገሠ። |
ንጉሥ ኢኮንያን ከእናቱ፥ ከልዑላን መሳፍንቱ፥ ከጦር አዛዦቹና ባለሟሎቹ ከሆኑት ባለሥልጣኖች ጋር ቀርቦ ለባቢሎናውያን እጁን ሰጠ፤ ናቡከደነፆር በነገሠ በስምንተኛው ዓመት ኢኮንያንን እስረኛ አድርጎ ያዘው፤
ለኢዮአቄም ልጅ ለኢኮንያን እግዚአብሔር እንዲህ አለው፦ “እኔ ሕያው አምላክ አንተ በቀኝ እጄ እንደሚገኝ የማኅተም ቀለበት ብትሆን እንኳ አውልቄ እጥልሃለሁ፤
እኔም እንዲህ አልኩ፦ “ንጉሥ ኢኮንያን ከተጣለ በኋላ ማንም እንደማይፈልገው ሰባራ ገንቦ መሆኑ ነውን? እርሱና ልጆቹ ተማርከው ወደማያውቁት አገር የተወሰዱት ለምንድን ነው?”
እግዚአብሔር በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት የተቀመጡ ሁለት የበለስ ፍሬ ቅርጫቶችን አሳየኝ፤ ይህም የሆነው የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር የኢዮአቄም ልጅ የሆነውን የይሁዳ ንጉሥ ኢኮንያንን ከይሁዳ መሪዎች፥ ከእጅ ጥበብ ባለሞያዎችና ከሌሎችም ብልኀተኞች ሠራተኞች ጋር ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን አስሮ ከወሰደ በኋላ ነው።
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ወደ ይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ ዘንድ ሄጄ እንዲህ ብዬ እንድነግረው አዘዘኝ፤ “እኔ እግዚአብሔር ይህችን ከተማ ለባቢሎን ንጉሥ አሳልፌ እሰጣታለሁ፤ እርሱም በእሳት ያቃጥላታል።
የይሁዳ ንጉሥ ኢኮንያን በተማረከ በሠላሳ ሰባተኛው ዓመት በዐሥራ ሁለተኛው ወር ከወሩም በሃያ አምስተኛው ቀን የባቢሎን ንጉሥ ኤዌል መሮዳክ በነገሠበት ዓመት የይሁዳን ንጉሥ ኢኮንያንን ከእስር ፈታው።