ኤርምያስ 35:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ ግን እንዲህ ሲሉ መለሱልኝ፦ “እኛ የወይን ጠጅ አንጠጣም፤ የሬካብ ልጅ የነበረው አባታችን ኢዮናዳብ እኛም ሆንን ዘሮቻችን ሁሉ ምንም ዐይነት የወይን ጠጅ እንዳንጠጣ አዞናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱ ግን እንዲህ አሉ፤ “የወይን ጠጅ አንጠጣም፤ አባታችን የሬካብ ልጅ ኢዮናዳብ እንዲህ ብሎ አዝዞናል፤ ‘እናንተና ዘራችሁ ከቶ የወይን ጠጅ አትጠጡ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱ ግን እንዲህ አሉ፦ “የወይኑን ጠጅ አንጠጣም፥ አባታችን የሬካብ ልጅ ኢዮናዳብ እንዲህ ብሎ አዝዞናልና፦ ‘እናንተና ልጆቻችሁ ለዘለዓለም የወይን ጠጅ አትጠጡ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱ ግን እንዲህ አሉ፥ “የወይኑን ጠጅ አንጠጣም፤ አባታችን የሬካብ ልጅ ኢዮናዳብ እናንተና ልጆቻችሁ ለዘለዓለም የወይን ጠጅ አትጠጡ ብሎ አዝዞናልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱ ግን እንዲህ አሉ፦ የወይኑን ጠጅ አንጠጣም፥ አባታችን የሬካብ ልጅ ኢዮናዳብ እንዲህ ብሎ አዝዞናልና፦ እናንተና ልጆቻችሁ ለዘላለም የወይን ጠጅ አትጠጡ። |
ይህንንም ያደረገበት ምክንያት እርሱና ያዕቆብ ብዙ ንብረት ስለ ነበራቸው፥ የሚሰፍሩበት ምድር ለሁለት ስላልበቃ ነው፤ ሁለቱም ብዙ እንስሶች ስለ ነበሩአቸው አብረው ለመኖር አልቻሉም።
ኢዩ ተነሥቶ እንደገና ጒዞ ቀጠለ፤ በመንገድ ሳለም የሬካብን ልጅ ኢዮናዳብን አገኘ፤ ኢዩም ሰላምታ ከሰጠው በኋላ “እኔና አንተ በሐሳብ አንድ ነን፤ ታዲያ ከእኔ ጋር ትተባበራለህን?” ሲል ጠየቀው። ኢዮናዳብም “አዎ እተባበርሃለሁ” ሲል መለሰ። ኢዩም “እንግዲያውስ ጨብጠኝ” ሲል መለሰለት፤ እጅ ለእጅ ተያይዘው ኢዩ ደግፎት በሠረገላው ላይ አስቀመጠውና፥
ከዚህም በኋላ ኢዩ ራሱ የሬካብ ልጅ ከሆነው ከኢዮናዳብ ጋር አብሮ ወደ ቤተ መቅደሱ ገባ፤ በዚያም ለሕዝቡ “እንግዲህ በዚህ የሚገኙት የባዓል አምላኪዎች ብቻ መሆናቸውንና እግዚአብሔርን የሚያመልክ አንድም አለመኖሩን በሚገባ አረጋግጡ” ሲል ተናገረ፤
ቲርዓውያን፥ ሺምዓውያንና ሱካውያን የተባሉት ታሪክ በመጻፍና በመገልበጥ ጥበበኞች የነበሩት ጐሣዎች ያዕቤጽ ተብላ በምትጠራ ትንሽ ከተማ ይኖሩ ነበር፤ እነርሱም ከሬካባውያን አባት ከሐሜት የወጡ ቄናውያን ነበሩ።
የኢዮናዳብ ዘሮች እንኳ የወይን ጠጅ እንዳይጠጡ አባታቸው ያዘዛቸውን ቃል በመጠበቅ እነሆ እስከ አሁን ድረስ ምንም ዐይነት የወይን ጠጅ አይቀምሱም፤ እኔ ግን ሁልጊዜ በመደጋገም እነግራችኋለሁ፤ እናንተ ልትታዘዙኝ አልፈለጋችሁም፤
“አንተና ልጆችህ የወይን ጠጅ ወይም ሌላ የሚያሰክር መጠጥ ጠጥታችሁ ወደ መገናኛው ድንኳን እንዳትገቡ ተጠንቀቁ፤ ይህን ብታደርጉ ትሞታላችሁ፤ ይህም ሕግ ከእናንተ በኋላ በሚነሣውም ትውልድ ዘንድ ሁሉ ተጠብቆ መኖር አለበት።
እርሱ በጌታ ፊት ታላቅ ይሆናል፤ የወይን ጠጅና ሌላም የሚያሰክር መጠጥ አይጠጣም፤ ገና በእናቱ ማሕፀን ሳለ በመንፈስ ቅዱስ የተሞላ ይሆናል።
ከወይን ተክል የሚገኝ ምንም ነገር መመገብ አይኖርባትም፤ የወይን ጠጅም ሆነ ማንኛውንም የሚያሰክር መጠጥ አትጠጣ፤ ማንኛውንም ርኩስ ምግብ አትበላም፤ በአጠቃላይ እኔ ያዘዝኳትን ሁሉ መፈጸም አለባት።”
ነገር ግን እርሱ ‘እነሆ ትፀንሺአለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ’ ብሎ ነገረኝ፤ እንዲሁም የሚወለደው ልጅ ከተወለደበት ቀን ጀምሮ እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ በናዝራዊነት ለእግዚአብሔር የተለየ ስለሚሆን፥ የወይን ጠጅም ሆነ ማንኛውንም የሚያሰክር መጠጥ ከመጠጣትና ማንኛውንም ርኩስ ምግብ ከመብላት እንድጠነቀቅ ነግሮኛል።”