ስለ እርሱ እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ይህ ነው፦ የጽዮን ድንግል ትንቅሃለች፤ ታፌዝብሃለች፤ አንተ እየሸሸህ ሳለህ፥ የኢየሩሳሌም ልጃገረዶች ከኋላህ ሆነው ራሳቸውን ይነቀንቁብሃል።
ኤርምያስ 31:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቤ እስራኤል ሆይ፥ እንደገና ትገነባላችሁ፤ ትገነቢአለሽም፥ እንደገና ከበሮ ትይዢአለሽ፤ ከሚደሰቱት ጋር አብረሽ በመውጣት ትጨፍሪአለሽ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእስራኤል ድንግል ሆይ፤ እንደ ገና ዐንጽሻለሁ፤ አንቺም ትታነጺአለሽ፤ ከበሮችሽንም እንደ ገና አንሥተሽ፣ ከሚፈነጥዙት ጋራ ትፈነድቂአለሽ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤል ድንግል ሆይ! እንደገና እሠራሻለሁ አንቺም ትሠሪያለሽ፤ እንደገናም ከበሮሽን አንሥተሽ ሐሤት በሚያደርጉ ዘፋኞች ሽብሸባ እያሸበሸብሽ ትወጫለሽ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤል ድንግል ሆይ እንደ ገና እሠራሻለሁ፤ አንቺም ትሠሪያለሽ፤ እንደ ገናም ከበሮሽን አንሥተሽ ከዘፋኞች ጋር ትወጫለሽ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤል ድንግል ሆይ፥ እንደ ገና እሠራሻለሁ አንቺም ትሠሪያለሽ፥ እንደ ገናም ከበሮሽን አንሥተሽ ከዘፋኞች ጋር ወደ ዘፈን ትወጫለሽ። |
ስለ እርሱ እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ይህ ነው፦ የጽዮን ድንግል ትንቅሃለች፤ ታፌዝብሃለች፤ አንተ እየሸሸህ ሳለህ፥ የኢየሩሳሌም ልጃገረዶች ከኋላህ ሆነው ራሳቸውን ይነቀንቁብሃል።
እግዚአብሔር ለሕዝቡ ለእስራኤል እንደገና ምሕረትን ያደርጋል፤ የራሱ ወገኖችም አድርጎ ይመርጣቸዋል፤ እንደገናም በአገራቸው እንዲኖሩ ይፈቅድላቸዋል፤ መጻተኞችም እንኳ መጥተው ከእነርሱ ጋር ተስማምተው አብረው ይኖራሉ።
ስለ እርሱም እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ይህ ነው፥ ‘ሰናክሬም ሆይ! የኢየሩሳሌም ሕዝብ አንተን በመናቅ ያፌዙብሃል፤ በምትሸሽበትም ጊዜ ከበስተኋላህ ሆነው ራሳቸውን ይነቀንቁብሃል።
ስለዚህ ጉዳይ እግዚአብሔር ለሕዝቡ እንዲህ ብዬ እንድናገር አዘዘኝ። “ሕዝቤ እጅግ ቈስሎአል፤ በብርቱም ተጐድቶአል፤ ስለዚህ ዐይኖቼ ቀንና ሌሊት እንባ ያፈሳሉ፤ ባለማቋረጥም አለቅሳለሁ።
ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ይህን የመሰለ ነገር በሕዝቦች መካከል ተሰምቶ እንደ ሆነ ጠይቁ፤ የተለዩ የእስራኤል ሕዝብ በጣም አጸያፊ የሆነ ነገር አድርገዋል።
ልጃገረዶቻቸውም በደስታ ይጨፍራሉ፤ ወንዶች ወጣቶችና ሽማግሌዎችም ደስ ይላቸዋል፤ አጽናናቸዋለሁ፤ ለቅሶአቸውን ወደ ደስታ፥ ሐዘናቸውንም ወደ ሐሴት እለውጣለሁ፤
ለራሳችሁ የመንገድ ምልክቶችን አድርጉ፤ መንገድንም የሚመሩ ዐምዶችን ትከሉ፤ የሄዳችሁበትን ዐውራ ጐዳና አተኲራችሁ ተመልከቱ፤ ሕዝቤ እስራኤል ሆይ! ወደ እነዚህ ከተሞቻችሁ ተመለሱ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ከሐናንኤል መጠበቂያ ግንብ ጀምሮ እስከ ማእዘኑ የቅጽር በር ድረስ ኢየሩሳሌም የእኔ ከተማ ሆና የምትታነጽበት ጊዜ ይመጣል።
እንደ ድንግል የምትታዪ ግብጽ ሆይ! ወደ ገለዓድ ሄደሽ የሚቀባ መድኃኒት ፈልጊ፤ የአንቺ መድኃኒት ሁሉ ከንቱ ነው፤ ሊፈውስሽ የሚችል ነገር ከቶ የለም።
“እግዚአብሔር ወታደሮቻችንን ከእኛ አስወገደ፤ የጐልማሶቻችንን ኀይል ለማድቀቅ የጦር ሠራዊት ላከብን፤ እግዚአብሔር ባልተደፈረችው ከተማ የሚኖረውን ሕዝባችንን በወይን መጭመቂያ እንደሚረገጥ የወይን ዘለላ ረገጣቸው።
ምን ልበላችሁ? ከምንስ ጋር ላነጻጽራችሁ? የተወደደችው ከተማ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ሆይ! እንዳጽናናችሁ ከምን ጋር ላመሳስላችሁ? በተለይ የኢየሩሳሌም ከተማ ሕዝብ ሆይ! የሚደርስባችሁ ጥፋት እንደ ባሕር መጠኑ ሰፊ ስለ ሆነ፥ ማን ሊፈውሳችሁ ይችላል?
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ፈራርሶ እንደ ወደቀ ቤት የነበረውን የዳዊትን ሥርወ መንግሥት መልሼ የማቋቊምበት ጊዜ ይመጣል፤ ቅጽሩን እጠግናለሁ፤ ፍርስራሹንም አድሳለሁ፤ በቀድሞ ዘመን እንደ ነበረውም አድርጌ እሠራዋለሁ፤
ዮፍታሔ በምጽጳ ወዳለው ቤቱ በተመለሰ ጊዜ ሴት ልጁ አታሞ ይዛ እየጨፈረች ልትቀበለው ወጣች፤ ያለ እርስዋም ሌላ ወንድ ወይም ሴት ልጅ አልነበረውም።