ኤርምያስ 31:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የዋይታና የመራራ ለቅሶ ድምፅ በራማ ተሰማ፤ ራሔል ስለ ልጆችዋ ታለቅሳለች፤ ልጆችዋ በሕይወት ስለሌሉ መጽናናትን እምቢ አለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የልቅሶና የታላቅ ዋይታ ድምፅ ከራማ ተሰማ፤ ራሔል ስለ ልጆቿ አለቀሰች፣ መጽናናትም እንቢ አለች፤ ልጆቿ ዐልቀዋልና።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እንዲህ ይላል፦ “የዋይታና የመራራ ልቅሶ ድምፅ በራማ ተሰማ፤ ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች፤ የሉምና ስለ ልጆችዋ መጽናናትን እንቢ አለች።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “የኀዘን፥ የልቅሶና የጩኸት ድምፅ በራማ ተሰማ፤ ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች፤ የሉምና ስለ ልጆችዋ መጽናናትን እንቢ አለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የዋይታና የመራራ ልቅሶ ድምፅ በራማ ተሰማ፥ ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች፥ የሉምና ስለ ልጆችዋ መጽናናትን እንቢ አለች። |
ወንዶችና ሴቶች ልጆቹ ሁሉ ሊያጽናኑት ወደ እርሱ መጡ፤ እርሱ ግን “ለልጄ እያለቀስሁ ወደ ሙታን ዓለም እወርዳለሁ” በማለት መጽናናትን እምቢ አለ። ስለዚህ ስለ ልጁ ማዘኑን ቀጠለ።
እነርሱም “እኛ አገልጋዮችህ በከነዓን ምድር የሚኖር የአንድ ሰው ልጆች የሆንን ዐሥራ ሁለት ወንድማማቾች ነን፤ አንዱ ወንድማችን ሞቶአል፤ የመጨረሻ ታናሽ ወንድማችን አሁን ከአባታችን ጋር ይገኛል” አሉት።
በዚህ ጊዜ አባታቸው “ልጆቼን ሁሉ እንዳጣ ትፈልጋላችሁን? ዮሴፍ የለም፤ ስምዖንም የለም፤ አሁን ደግሞ ብንያምን ለመውሰድ ትፈልጋላችሁ፤ በዚህ ሁሉ መከራ የምሠቃየው እኔ ነኝ!” አለ።
ከቶ ኃጢአቴን ይቅር አትልልኝምን? የማደርገውንስ በደል አትደመስስልኝምን? ወደ መቃብር መውረጃዬ ደርሶአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ብትፈልገኝ እንኳ አልገኝም።”
በችግር ጊዜ ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ፤ ሌሊቱን ሙሉ ያለ ዕረፍት እጆቼን ዘርግቼ ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ፤ ይሁን እንጂ ለመጽናናት አልቻልኩም።
ድንኳኖቻችን ፈራረሱ፤ መወጠሪያ ገመዶችም ተቈራረጡ፤ ልጆቻችን በሙሉ ተሰደው ስለ ሄዱ፥ ድንኳኖቻችንን መልሶ የሚተክልልንና መጋረጃዎቻችንን የሚሰቅልልን አንድ እንኳ አልቀረም።”
የክብር ዘብ አዛዡ ናቡዛርዳን እኔን በራማ ነጻ ከለቀቀኝ በኋላ እግዚአብሔር ተናገረኝ፤ ከዚያ በፊት እኔ እዚያ የተወሰድኩት አሁን ከኢየሩሳሌምና ከይሁዳ በመማረክ ታስረው ወደ ባቢሎን ከተወሰዱት ሕዝብ ሁሉ ጋር በሰንሰለት ታስሬ ነበር።
ያም እጅ የብራናውን ጥቅል ፈቶ በፊቴ ዘረጋው፤ እርሱም በሁለት በኩል ጽሑፍ ያለበት መሆኑን አየሁ፤ በእርሱም ላይ የለቅሶ፥ የሐዘንና የዋይታ ቃሎች ተጽፈውበት ነበር።
ይህችም ነቢይት በተራራማው በኤፍሬም አገር በራማና በቤትኤል መካከል በሚገኘው የዲቦራ የተምር ዛፍ ሥር ተቀምጣ ትፈርድ ስለ ነበር የእስራኤል ሕዝብ ፍርድ ለማግኘት ወደ እርስዋ ይሄዱ ነበር።