በዚህ ሁሉ ነገር ታዛዥ ብትሆንለት፥ ‘ዘሮችህ በጥንቃቄ ተጠብቀው ቢኖሩ፥ በፍጹም ልባቸውና በፍጹም ነፍሳቸው በፊቴ በቅንነት ቢመላለሱ፥ በእስራኤል ዙፋን ላይ ነግሦ የሚገዛ ዘር አላሳጣህም’ ብሎ የነገረኝን የተስፋ ቃል ይፈጽማል።
ኤርምያስ 29:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ትፈልጉኛላችሁ፤ የምትፈልጉኝም በሙሉ ልባችሁ ከሆነ ታገኙኛላችሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ ትፈልጉኛላችሁ፤ በፍጹም ልባችሁም ከፈለጋችሁኝ ታገኙኛላችሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ ትሹኛላችሁ፥ በፍጹም ልባችሁም ከሻችሁኝ ታገኙኛላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተ ትሹኛላችሁ፤ በፍጹም ልባችሁም ከሻችሁኝ ታገኙኛላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ ትሹኛላችሁ፥ በፍጹም ልባችሁም ከሻችሁኝ ታገኙኛላችሁ። |
በዚህ ሁሉ ነገር ታዛዥ ብትሆንለት፥ ‘ዘሮችህ በጥንቃቄ ተጠብቀው ቢኖሩ፥ በፍጹም ልባቸውና በፍጹም ነፍሳቸው በፊቴ በቅንነት ቢመላለሱ፥ በእስራኤል ዙፋን ላይ ነግሦ የሚገዛ ዘር አላሳጣህም’ ብሎ የነገረኝን የተስፋ ቃል ይፈጽማል።
ንጉሡ በዐምዱ አጠገብ ቆሞ በሙሉ ልቡና ሓሳቡ እግዚአብሔርን ለመከተልና ትእዛዞቹን፥ ደንቦቹንና ድንጋጌዎቹን ለመጠበቅ በእርሱ ፊት ቃል ኪዳኑን አደሰ፤ ስለዚህም በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን ቃል ኪዳን አረጋገጠ፤ ሕዝቡም በቃል ኪዳኑ ተባበረ።
እንግዲህ አምላካችሁን እግዚአብሔርን በፍጹም ልባችሁና በፍጹም ነፍሳችሁ አገልግሉ፤ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦትና እግዚአብሔርን ለማምለክ መገልገያ የሆኑትን ንዋያተ ቅድሳት ሁሉ አምጥታችሁ በውስጡ ማኖር ትችሉ ዘንድ ቤተ መቅደሱን ለክብሩ መሥራት ጀምሩ።”
ዳዊት ሰሎሞንንም እንዲህ አለው፤ “ልጄ ሆይ፥ የአባትህን አምላክ እንድታውቅ፥ በሙሉ ልብና በፈቃደኛ አእምሮ እንድታገለግለው ዐደራ እልሃለሁ፤ እርሱ ሐሳባችንንና ምኞታችንን ሁሉ ያውቃል፤ ወደ እርሱ ብትቀርብ እርሱም ወደ አንተ ይቀርባል፤ ብትተወው ግን እርሱም ለዘለዓለም ይተውሃል፤
አካዝያስንም ፈልገው በሰማርያ ተሸሽጎ አገኙት፤ ወደ ኢዩም አምጥተው ገደሉት፤ ነገር ግን የተቻለውን ያኽል እግዚአብሔርን ያገለግል ስለ ነበረው ስለ አያቱ ስለ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ ክብር ሲሉ ሬሳውን ቀበሩት። ከአካዝያስ ቤተሰብ አባላት መካከል መንግሥቱን ሊመራ የሚችል አንድም ሰው አልተረፈም።
ለቤተ መቅደሱ አገልግሎት ወይም ሕጉንና ትእዛዞቹን ለመጠበቅ ያከናወነው ሥራ ሁሉ ለአምላኩ ለእግዚአብሔር በፍጹም ታማኝነትና በመንፈሳዊ ቅናት ስለ ነበር ሁሉም ነገር ተሳካለት።
ጨለማ በሆነ አገር በድብቅ አልተናገርኩም፤ የያዕቆብን ልጆች፦ ‘ቅርጽ በሌለው ቦታ ፈልጉኝ’ አላልኳቸውም፤ እኔ እግዚአብሔር እውነቱን እናገራለሁ፤ ትክክል የሆነውንም ነገር እገልጣለሁ።
እኔ እግዚአብሔር መሆኔን እንዲያውቁ አደርጋቸዋለሁ። ከዚያ በኋላም በሙሉ ልባቸው ወደ እኔ ስለሚመለሱ፥ እነርሱ ሕዝቤ ይሆናሉ፤ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ።
ይህን ሁሉ ከፈጸመች በኋላ እምነት የማይጣልባት የእስራኤል እኅት የሆነችው ይሁዳ፥ እንደገና ወደ እኔ ለመመለስ የምትሞክር መስላ የታየችው ከልብዋ ሳይሆን ከአንገት በላይ ነበር፤ ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ዘመኑና ጊዜው ሲደርስ የእስራኤልና የይሁዳ ሕዝብ በአንድነት ሆነው እኔን አምላካቸውን ፍለጋ እያለቀሱ ይመጣሉ፤