“ይህን ሁሉ በምትነግራቸው ጊዜ ‘እግዚአብሔር በእኛ ላይ ይህን የሚያኽል ከባድ ጥፋት ለምን ወሰነብን? ምን በደልን? በአምላካችን በእግዚአብሔር ፊትስ የሠራነው ኃጢአት ምንድን ነው?’ ብለው ይጠይቁሃል።
ኤርምያስ 22:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከዚያን በኋላ በዚያ በኩል የሚያልፉ ብዙ የውጪ አገር ሰዎች ‘በዚህች በታላቅ ከተማ ላይ እግዚአብሔር ይህን ጥፋት ያመጣው ለምን ይሆን?’ በማለት እርስ በርሳቸው ይጠያየቃሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከተለያየ አገር የመጡ ሕዝቦች በዚህች ከተማ በኩል ሲያልፉ፣ ‘እግዚአብሔር በዚህች ታላቅ ከተማ ላይ ለምን እንዲህ አደረገ?’ እያሉ እርስ በርስ ይነጋገራሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብዙ አሕዛብም በዚህች ከተማ አጠገብ ያልፋሉ፥ ሁሉም ባልንጀሮቻቸውን፦ ጌታ በዚህች ታላቅ ከተማ ለምን እንዲህ አደርገ?” ይላሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብዙ አሕዛብም በዚች ከተማ ላይ ያልፋሉ፤ ሁሉም ባልንጀሮቻቸውን፦ እግዚአብሔር በዚች ታላቅ ከተማ ለምን እንዲህ አደረገ? ይላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብዙ አሕዛብም በዚህች ከተማ አጠገብ ያልፋሉ፥ ሁሉም ባልንጀሮቻቸውን፦ እግዚአብሔር በዚህች ታላቅ ከተማ ለምን እንዲህ አደርገ? ይላሉ። |
“ይህን ሁሉ በምትነግራቸው ጊዜ ‘እግዚአብሔር በእኛ ላይ ይህን የሚያኽል ከባድ ጥፋት ለምን ወሰነብን? ምን በደልን? በአምላካችን በእግዚአብሔር ፊትስ የሠራነው ኃጢአት ምንድን ነው?’ ብለው ይጠይቁሃል።
የክብር ዘብ አዛዡ እኔን ገለል አድርጎ ለብቻ እንዲህ አለኝ፦ “አምላክህ እግዚአብሔር ይህችን ምድር እንደሚያጠፋት አስቀድሞ ተናግሮ ነበር፤
አደርጋለሁ ብሎ ያቀደውን ሁሉ እነሆ አሁን ፈጽሞታል፤ ይህም ሁሉ የሆነው እናንተ ኃጢአት በመሥራታችሁና ለእግዚአብሔር ባለመታዘዛችሁ ምክንያት ነው።
ነገር ግን ከእነርሱ ጥቂቶቹን ከጦርነት፥ ከራብና ከቸነፈር እንዲተርፉ አደርጋለሁ፤ በዚህም ዐይነት በሕዝቦች መካከል ሲኖሩ ሥራቸው ምን ያኽል አጸያፊ እንደ ነበር ይገነዘባሉ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ያውቃሉ።”
እስራኤላውያን ተማርከው የሄዱትም እኔን በመበደላቸው ምክንያት መሆኑን ሕዝቦች ሁሉ ያውቃሉ፤ እኔ ችላ ስላልኳቸው ጠላቶቻቸው በጦርነት ድል አድርገው ሁላቸውንም ገድለዋቸዋል።
“በኀይለኛ ቊጣዬ በእናንተ ላይ ፍርዴን ተግባራዊ አድርጌ በምቀጣችሁ ጊዜ በአካባቢአችሁ ለሚኖሩ ሕዝቦች የመሳለቂያ፥ የሽሙጥ፥ የማስጠንቀቂያ የድንጋጤ ምክንያት ትሆናላችሁ፤ ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።
ጌታ ሆይ! አንተ እውነተኛ ነህ፤ ነገር ግን ለአንተ ታማኞች ባለመሆናችን፥ እኛ በምድር ሁሉ ላይ የበተንከን በቅርብና በሩቅ ያለን የይሁዳ ሕዝብ የኢየሩሳሌም ነዋሪዎችና መላዋ የእስራኤል ሕዝብ በአሁኑ ጊዜ ኀፍረት ደርሶብናል።