ኤርምያስ 21:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዳዊት ዘሮች ለሆኑት ለይሁዳ ንጉሣዊ ቤተሰብ እንድነግራቸው እግዚአብሔር የሰጠኝ ቃል ይህ ነው፦ “እኔ እግዚአብሔር የምነግራችሁን አድምጡ፤ በየማለዳው ፍትሕ እንዳይጓደል አድርጉ፤ አንዱ ሌላውን በመቀማት ግፍ እንዳይሠራበት ጠብቁ፤ ይህን ባታደርጉ ግን ከምትሠሩት ክፋት የተነሣ ቊጣዬ እንደ እሳት ይነዳል፤ ሊያጠፋውም የሚችል አይኖርም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ለይሁዳ ንጉሥ ቤትም እንዲህ በል፤ ‘የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የይሁዳ ንጉሥ ቤት ሆይ! የጌታን ቃል ስሙ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የይሁዳ ንጉሥ ቤት ሆይ! የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የይሁዳ ንጉሥ ቤት ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ። |
እኔ የምነግርህንም ቃል እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘የይሁዳ ነገሥታትና ሕዝብ! እንዲሁም በእነዚህ ቅጽር በሮች የምትገቡ የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ሆይ! የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ!
እግዚአብሔር የዳዊት ዘር ወደ ሆነው ወደ ይሁዳ ቤተ መንግሥት እንድወርድና በዚያም ለንጉሡ፥ ለመኳንንቱና ለኢየሩሳሌም ሕዝብ እኔ የምነግራቸውን ቃል እንዲያዳምጡ እንዲህ ብለህ ንገራቸው አለኝ፦
ስለዚህ እግዚአብሔር ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮስያስ ልጅ ስለ ኢዮአቄም የሚለው ይህ ነው፥ “እርሱ በሚሞትበት ጊዜ ‘ዋይ! ወዮ! ወንድሜ ሆይ!’ እያሉ በማልቀስ አያዝኑለትም፤ እንዲሁም ‘ጌታዬ ሆይ! ንጉሤ ሆይ! ወዮ!’ እያለ የሚያለቅስለት አይኖርም።
ከዚህም በኋላ እንዲህ አልኳቸው፦ “የእስራኤል ሕዝብ ልጆች መሪዎችና የእስራኤል ሕዝብ ገዢዎች! አድምጡ! ትክክለኛ ፍርድን ማወቅ ይገባችሁ አልነበረምን?