ኤርምያስ 20:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በማግስቱም ከሰንሰለት እስራት ከፈታኝ በኋላ እንዲህ አልኩት፥ “ከእንግዲህ ወዲህ እግዚአብሔር ስምህን ፓሽሑር ብሎ አይጠራህም፤ ለአንተ ያወጣልህ ስም ‘ሽብር በየስፍራው’ የሚል ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በማግስቱም ጳስኮር ኤርምያስን ከተጠረቀበት ግንድ አወጣው፤ ኤርምያስም እንዲህ አለው፤ “እግዚአብሔር ከእንግዲህ ማጎርሚሳቢብ ብሎ ይጠራሃል እንጂ ጳስኮር አይልህም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በነጋውም ጳስኮር ኤርምያስን ከመንቈር ውስጥ ፈታው። ኤርምያስም እንዲህ አለው፦ “ጌታ ስምህን፦ ማጎርሚሳቢብ እንጂ ጳስኮር ብሎ አይጠራህም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በነጋውም ጳስኮር ኤርምያስን ከአዘቅት ውስጥ አወጣው። ኤርምያስም እንዲህ አለው፥ “እግዚአብሔር ስምህን፦ ዘዋሪ ስደተኛ እንጂ ጳስኮር ብሎ አይጠራህም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በነጋውም ጳስኮር ኤርምያስን ከግንድ ውስጥ አወጣው። ኤርምያስም እንዲህ አለው፦ እግዚአብሔር ስምህን፦ ማጎርሚሳቢብ እንጂ ጳስኮር ብሎ አይጠራህም። |
ሰውየውም፥ “ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ ያዕቆብ አይባልም፤ ከእግዚአብሔርም ከሰውም ጋር ታግለህ አሸንፈሃል፤ ስለዚህ ስምህ ‘እስራኤል’ ይባላል” አለው።
ከጥቂት ጊዜ በኋላ ከነቢይቱ ሚስቴ ጋር ተገናኘሁ፤ እርስዋም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች፤ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “ስሙን ‘ለማጥፋትና ለምርኮ ፍጠን!’ ብለህ ጥራው
ብዙ ሰዎች ፈርተው በሹክሹክታ እንዲህ ሲሉ ሰማሁ፤ “አሁን ኤርምያስን ለመክሰስ መልካም አጋጣሚ ነው!” ወዳጆቼ ናቸው የሚባሉት እንኳ ስሕተት እንዳደርግ ይጠባበቃሉ፤ “ኤርምያስ ሊታለል ይችል ይሆናል፤ ይህም ከሆነ እርሱን ይዘን እንበቀለዋለን፤” ይላሉ።
“ነገር ግን ይህ የማየው ነገር ምንድን ነው? ከፍርሃት የተነሣ ወደ ኋላ በመመለስ ላይ ናቸው፤ ወታደሮቻቸው ድል ሆኑ፤ በየአቅጣጫው ፍርሀትና ሽብር ስላለ ወደ ኋላ መለስ ብለው ሳያዩም ወደ ፊት ሸሹ።
ስለዚህ የዚያ ቦታ ስም የቤን ሂኖም ሸለቆ ወይም ቶፌት መባሉ ቀርቶ የዕርድ ሸለቆ ተብሎ የሚጠራበት ጊዜ ይመጣል፤ ሌላ የመቃብር ስፍራ ስለማይገኝ ያ ሸለቆ ራሱ የሕዝቡ መቃብር ይሆናል።
የበዓል ቀን ይመስል ጠላቶቼን ከየቦታው ጋብዘሃል፤ በቊጣህ ቀን አንድም ያመለጠ ወይም በሕይወት የተረፈ የለም፤ ወልጄ ያሳደግኋቸውን ጠላቴ ፈጃቸው።
ሐሰተኛ ራእይ በሚያዩና ሟርትን በሚያሟርቱ ነቢያት ላይ እጄን አነሣለሁ፤ እነርሱ በሕዝቤ ማኅበር ውስጥ አይገኙም፤ እንዲያውም በእስራኤል ሕዝብ መዝገብ ውስጥ አይመዘገቡም፤ ወደ እስራኤል ምድርም አይገቡም፤ በዚያን ጊዜ እኔ ልዑል እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።