ግመሎቹ ጠጥተው ካበቁ በኋላ ሰውየው አምስት ግራም ያኽል የሚመዝን የወርቅ ጒትቻ አውጥቶ በጆሮዋ ላይ አደረገላት፤ መቶ ዐሥር ግራም ያኽል የሚመዝን ሁለት የወርቅ አምባሮችንም አውጥቶ በእጆችዋ ላይ አደረገላትና፥
ኤርምያስ 2:32 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለመሆኑ ኰረዳ ጌጣጌጥዋን፥ ሙሽራም የሙሽርነት ልብስዋን ትረሳለችን? ሕዝቤ ግን ሊቈጠሩ ለማይችሉ ለብዙ ዘመናት ረስተውኛል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለመሆኑ ቈንጆ ጌጣጌጧን፣ ሙሽራ የሰርግ ልብሷን ትረሳለችን? ሕዝቤ ግን፣ እጅግ ብዙ ቀን ረስቶኛል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በውኑ ኰረዳ ጌጥዋን ወይስ ሙሽራ ዝርግፍ ጌጣጌጥዋን ትረሳለችን? ሕዝቤ ግን በቍጥር ለማይቆጠሩ ቀናቶች ረስተውኛል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በውኑ ሙሽራ ጌጥዋን ወይስ ድንግል ዝርግፍ ጌጥዋን ትረሳለችን? ሕዝቤ ግን ለማይቈጠር ወራት ረስቶኛል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በውኑ ቆንጆ ጌጥዋን ወይስ ሙሽራ ዝርግፍ ጌጥዋን ትረሳለችን? ሕዝቤ ግን የማይቈጠር ወራት ረስቶኛል። |
ግመሎቹ ጠጥተው ካበቁ በኋላ ሰውየው አምስት ግራም ያኽል የሚመዝን የወርቅ ጒትቻ አውጥቶ በጆሮዋ ላይ አደረገላት፤ መቶ ዐሥር ግራም ያኽል የሚመዝን ሁለት የወርቅ አምባሮችንም አውጥቶ በእጆችዋ ላይ አደረገላትና፥
ላባ ወደ ሰውየው የሄደው እኅቱ በጆሮዋ ላይ ያደረገችውን ጒትቻና በእጆችዋ ላይ ያደረገቻቸውን አንባሮች ስላየና ርብቃ ሰውየው ያላትን ስትናገር ስለ ሰማም ነው። እርሱንም በውሃው ጒድጓድ አጠገብ ከግመሎቹ ጋር ቆሞ አገኘው።
ከወርቅና ከብር የተሠሩ ጌጣጌጦችን፥ እንዲሁም ልብስ አውጥቶ ለርብቃ ሰጣት፤ ለወንድምዋና ለእናትዋም በጣም ውድ የሆኑ ስጦታዎችን አውጥቶ ሰጣቸው።
እስራኤል ሆይ እናንተ እንደ ጽኑ አለት መከላከያ ሆኖ የተቤዣችሁን እግዚአብሔርን ረስታችኋል፤ ስለዚህ ከፍ ያለ ዋጋ ያለው ድንቅና ብርቅ የሆነ ተክል ብትተክሉና
“እኔን ባለማስታወስና ስለ እኔ ባለማሰብ ውሸት የተናገራችሁት ማንን ፈርታችሁ ነው? እኔን ያልፈራችሁኝ ለብዙ ጊዜ ዝም ስለልኩና እንዳላየ ስለሆንኩ ነውን?
እኔ በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፤ ሁለንተናዬም በአምላኬ ሐሴትን ያደርጋል፤ የአበባ አክሊል በራሱ ላይ እንደሚያደርግ ሙሽራ፥ በጌጣጌጥም እንዳሸበረቀች ሙሽሪት አድርጎ፥ የመዳንን ልብስ አልብሶኛል፤ የጽድቅንም መጐናጸፊያ ደርቦልኛል።
እነዚህ በክፋት የተሞሉ ሕዝብ ለእኔ መታዘዝን እምቢ ብለዋል፤ ከምንጊዜውም ይልቅ እልኸኞች ሆነዋል፤ ባዕዳን አማልክትን በማምለክ ያገለግላሉ፤ ከዚህም የተነሣ እነርሱ ዋጋቢስ ሆኖ እንደ ቀረው እንደዚያ መታጠቂያ ይሆናሉ።
ዕድል ፈንታችሁም ይህ እንደሚሆን እግዚአብሔር ተናግሮአል። እርሱን ረስታችሁ በሐሰተኞች አማልክት ስለ ታመናችሁ በእናንተ ላይ ይህን ለማድረግ ወስኖአል።
ሕዝቤ ግን እኔን ረስተዋል፤ ከንቱ ለሆኑ ጣዖቶችም ዕጣን ያጥናሉ፤ እነርሱም ባልታወቀ መንገድ እንዲሄዱ አድርገዋቸዋል፤ ተሰናክለውም የቀድሞውን መንገድ ትተዋል።
ሐሰተኞች አማልክት ቢሆኑም እንኳ አማልክቱን የሚቀያይር ሕዝብ የለም፤ ሕዝቤ ግን ክብር ያጐናጸፍኳቸውን እኔን አምላካቸውን ምንም ሊያደርጉላቸው በማይችሉ ከንቱ አማልክት ለውጠውኛል።”
ልምላሜ በሌለባቸው ኰረብቶች ራስ ላይ ድምፅ ይሰማል፤ ይህም ድምፅ፥ የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔር አምላካቸውን በመርሳት ኃጢአት ሲሠሩ ኖረው፥ አሁን በመጸጸት የሚያሰሙት የለቅሶና የልመና ድምፅ ነው።
ከሕዝብሽ አንዳንዶቹ ገንዘብ ተቀብለው ሰው ይገድላሉ፤ አንዳንዶቹ ለገዛ ወገኖቻቸው ለእስራኤላውያን ሳይቀር በአራጣ ያበድራሉ፤ እነርሱንም በመበዝበዝ ያለ አግባብ ይበለጽጋሉ፤ እኔንም ፈጽሞ ረስተዋል፤” ልዑል እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአል።
“የእስራኤል ሕዝብ ለራሳቸው ታላላቅ ቤተ መንግሥቶች ሠርተዋል፤ እኔን ፈጣሪአቸውን ግን ረስተዋል፤ የይሁዳም ሕዝብ ብዙ የተመሸጉ ከተሞችን ሠርተዋል፤ ስለዚህ ከተሞቻቸውንና ምሽጎቻቸውን የሚያቃጥል እሳት እልክባቸዋለሁ።”