ኤርምያስ 2:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሰማያት ሆይ! ከዚህ የተነሣ ደንግጡ፤ በታላቅ ፍርሀትም ተንቀጥቀጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰማያት ሆይ፤ በዚህ ተገረሙ፤ በታላቅ ድንጋጤም ተንቀጥቀጡ፤” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰማያት ሆይ! በዚህ ተሣቀቁ፥ እጅግም ደንግጡና ተንቀጥቀጡ ይላል ጌታ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰማይ በዚህ ደነገጠ፤ እጅግም ተንቀጠቀጠ” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰማያት ሆይ፥ በዚህ ተደነቁ፥ እጅግም ደንግጡና ተንቀጥቀጡ ይላል እግዚአብሔር። |
ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ይህን የመሰለ ነገር በሕዝቦች መካከል ተሰምቶ እንደ ሆነ ጠይቁ፤ የተለዩ የእስራኤል ሕዝብ በጣም አጸያፊ የሆነ ነገር አድርገዋል።
ምድር ሆይ! ስሚ! እነርሱ ያስተማርኳቸውን ሥርዓት ስለ ተቃወሙ፤ ለሕጌም ስላልታዘዙ ስለ ክፉ ሐሳባቸው ሁሉ እቀጣቸው ዘንድ በሕዝቡ ላይ ጥፋትን አመጣለሁ።
እናንተ ተራራዎች! እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ የሚያቀርበውን ወቀሳ ስሙ! እናንተም ጠንካራ የሆናችሁ የምድር መሠረቶች! አድምጡ! እግዚአብሔር ሕዝቡን እስራኤልን ይወቅሳል ይገሥጻልም።