ንጉሥ ኢዮስያስ በሒኖም ሸለቆ የነበረው “ቶፌት” ተብሎ የሚጠራው የአሕዛብ ማምለኪያ ቦታ የረከሰ መሆኑን አስገነዘበ፤ ከዚህም የተነሣ “ሞሌክ” ተብሎ ለሚጠራው አምላክ ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን መሥዋዕት አድርጎ የሚያቀርብ ማንም እንዳይኖር ተከለከለ፤
ኤርምያስ 19:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሸክላ ስባሪ በር በኩል አድርገህ ወደ ሂኖም ሸለቆ ሂድ፤ በእዚያም እኔ የምነግርህን ቃል እንዲህ ብለህ ዐውጅ፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በገል በር መግቢያ አጠገብ ወዳለው ወደ ሄኖም ልጅ ሸለቆ ውጣ። በዚያም የምነግርህን ቃል ተናገር፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በካርሲት በር መግቢያ አጠገብ ወዳለው ወደ ሄኖም ልጅ ሸለቆ ሂድ፥ በዚያም የምነግርህን ቃላት ተናገር፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በከርሲት በር መግቢያ አጠገብ ወዳለው ወደ ሄኖም ልጅ ሸለቆ ሂድ፥ በዚያም የምነግርህን ቃል አንብብ፤ እንዲህም በል፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በካርሲት በር መግቢያ አጠገብ ወዳለው ወደ ሄኖም ልጅ ሸለቆ ሂድ፥ በዚያም የምነግርህን ቃል ተናገር፥ |
ንጉሥ ኢዮስያስ በሒኖም ሸለቆ የነበረው “ቶፌት” ተብሎ የሚጠራው የአሕዛብ ማምለኪያ ቦታ የረከሰ መሆኑን አስገነዘበ፤ ከዚህም የተነሣ “ሞሌክ” ተብሎ ለሚጠራው አምላክ ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን መሥዋዕት አድርጎ የሚያቀርብ ማንም እንዳይኖር ተከለከለ፤
በሂኖም ሸለቆም ዕጣን አጠነ፤ እስራኤላውያን ወደ ምድሪቱ በገቡ ጊዜ እግዚአብሔር ከዚያ ያባረራቸውን ሕዝቦች አጸያፊ ልማድ በመከተል፥ የራሱን ወንዶች ልጆች እንኳ ሳይቀር የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ ለጣዖቶች አቀረበ።
የገዛ ወንዶች ልጆቹንም በሂኖም ሸለቆ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ፤ እርሱም ራሱ ሟርተኛና አስማተኛ ሆኖ፥ ከጠንቋዮችና ከሙታን ጠሪዎች ምክርን ይጠይቅ ነበር፤ በዚህም ሁሉ አድራጎቱ ታላቅ ኃጢአት ስለ ሠራ፥ እግዚአብሔርን አስቈጣ።
እግዚአብሔር ግን እንዲህ አለኝ፦ “ ‘ገና ልጅ ነኝ’ አትበል፤ የምትሄደው እኔ ወደምልክህ ቦታ ነው፤ የምትናገረውም እኔ የማዝህን ሁሉ ነው፤
ከዚያን በኋላም እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “ወደ ይሁዳ ከተሞችና ወደ ኢየሩሳሌም መንገዶች ሄደህ ቃል ኪዳኔን እንዲያዳምጡና ትእዛዞቼን እንዲፈጽሙ በማሳሰብ ቃሌን ዐውጅላቸው፤
ስለዚህም እግዚአብሔር ወደ ሰሜን ሄጄ ለእስራኤል እንድነግራት ያዘዘኝ ይህ ነው፤ “እምነት የማይጣልብሽ እስራኤል ሆይ! ወደ እኔ ተመለሺ፤ እኔ ምሕረቴ የበዛ ስለ ሆነ አልቈጣም፤ በአንቺ ላይ የምቈጣውም ለዘለዓለም አይደለም።
ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ሞሌክ ለተባለው ጣዖት መሥዋዕት አድርገው ለማቅረብ በሄኖም ሸለቆ ውስጥ ለበዓል ጣዖት መሠዊያ ሠርተዋል፤ እኔ ይህን እንዲያደርጉ አላዘዝኳቸውም የይሁዳንም ሕዝብ ወደ ኃጢአት ለመምራት ይህን ያደርጋሉ ብዬ አልጠበቅሁም ነበር።”
ድንበሩ በሔኖም ልጅ ሸለቆ ከደቡብ ዝቅተኛ ቦታ የኢያቡሳውያን ከተማ በሆነችው በኢየሩሳሌም በኩል ከሔኖም ሸለቆ ፊት ለፊት እስካለው ተራራ ጫፍ ድረስ በመዝለቅ በሰሜን በኩል ወደ ሬፋይም ሸለቆ ይደርሳል።