እኔን ከጒዳት ሁሉ ያዳነኝ መልአክ እነርሱንም ይጠብቃቸው። የእኔ ስም፥ የአባቶቼም የአብርሃምና የይስሐቅ ስም በነዚህ ልጆች ሲታወስ ይኑር፤ ዘራቸውም በምድር ላይ ይብዛ።”
ኤርምያስ 15:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከክፉዎች አድንሃለሁ፤ ከጨካኞችም እጅ እታደግሃለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከክፉዎች እጅ እቤዥሃለሁ፤ ከጨካኞችም ጭምደዳ እታደግሃለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከክፉ ሰዎችም እጅ እታደግሃለሁ፥ ከጨካኞችም እጅ እቤዥሃለሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከክፉ ሰዎችም እጅ እታደግሃለሁ፤ ከጨካኞችም ጡጫ እቤዥሃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከክፉ ሰዎችም እጅ እታደግሃለሁ፥ ከጨካኞችም ጡጫ እቤዥሃለሁ። |
እኔን ከጒዳት ሁሉ ያዳነኝ መልአክ እነርሱንም ይጠብቃቸው። የእኔ ስም፥ የአባቶቼም የአብርሃምና የይስሐቅ ስም በነዚህ ልጆች ሲታወስ ይኑር፤ ዘራቸውም በምድር ላይ ይብዛ።”
ኢየሩሳሌም ሆይ! በአንቺ ላይ በጠላትነት የሚነሡ የጠላት ሠራዊት ሁሉ እንደ ትቢያ በነው ይጠፋሉ፤ እጅግ የሚያስፈሩ ሠራዊቶቻቸውም ሳይታሰቡ በድንገት በነፋስ እንደሚወሰድ ገለባ ይሆናሉ።
ጨቋኞችሽ የገዛ ሥጋቸውን እንዲበሉ አደርጋለሁ፤ በወይን ጠጅ እንደሚሰክሩ የገዛ ደማቸውን ጠጥተው እንዲሰክሩ አደርጋለሁ። ከዚህም የተነሣ እኔ እግዚአብሔር አዳኝሽና ታዳጊሽ የእስራኤል ኀያል አምላክ መሆኔን የዓለም ሕዝብ ሁሉ ያውቃል።”
አንቺን ለማጥፋት የሚሠራ መሣሪያ ዘላቂነት አይኖረውም፤ ለሚከሱሽ ሁሉ በቂ መልስ ይኖርሻል፤ የእኔ አገልጋዮች ርስትና ከእኔ የሚፈረድላቸው ፍርድ ይህ ነው፤” ይላል እግዚአብሔር።
ልጆች የእናታቸውን ጡት እንደሚጠቡ የአንቺም ልጆች የሕዝቦችንና የነገሥታትን ሀብት በመውሰድ ይጠቀሙበታል፤ አንቺም እኔ እግዚአብሔር አዳኝሽና ታዳጊሽ ኀያሉ የያዕቆብ አምላክ መሆኔን ታውቂአለሽ።
ነገር ግን ታዳጊያቸው ብርቱ ነው፤ ስሙም የሠራዊት አምላክ ነው፤ እርሱ ራሱ ይረዳቸዋል፤ ሰላምን በምድር ላይ ያወርድላቸዋል፤ በባቢሎን ሕዝብ ላይ ገና መከራን ያመጣባቸዋል።”
ንጉሡም “እነሆ፥ እኔ እሳቱ ምንም ሳይጐዳቸው ከእስራት ተፈተው በነበልባሉ ውስጥ የሚመላለሱ አራት ሰዎች አያለሁ፤ አራተኛውም የአማልክትን ልጅ ይመስላል” አለ።