ለኢሳይያስም እንዲነግሩት የላከው መልእክት ከዚህ የሚከተለው ነው፦ “ዛሬ የታላቅ መከራ ቀን ነው፤ የሚያሳፍር ቅጣትና ውርደት እየደረሰብን ነው፤ የምትወልድበት ጊዜ ደርሶ ለማማጥ አቅም እንዳነሣት ሴት ሆነናል፤
ኢሳይያስ 26:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዳረገዙ ሴቶች ሆንን፤ ምጥም ይዞን ነበር፤ ነገር ግን ምንም ልጅ አልወለድንም፤ ለምድራችንም ድል አላስገኘንላትም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አረገዝን በምጥም ተጨነቅን፤ ነገር ግን ነፋስን ወለድን፤ ለምድርም ድነትን አላመጣንም፤ የዓለምን ሕዝብ አልወለድንም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኛ ፀንሰናል ምጥም ይዞናል፥ ነፋስንም እንደምንወልድ ሆነናል፤ በምድርም ደኅንነት አላመጣንም፤ በዓለም እንዲኖሩም ሕዝብ አልወለድንም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተን በመፍራት አቤቱ፥ እኛ ፀንሰናል፤ ምጥም ይዞናል፤ በምድርም የማዳንህን መንፈስ ወለድን፤ በዓለምም የሚኖሩ ይወድቃሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኛ ፀንሰናል ምጥም ይዞናል፥ ነፋስንም እንደምንወልድ ሆነናል፥ በምድርም ደኅንነት አላደረግነም፥ በዓለምም የሚኖሩ ይወድቃሉ። |
ለኢሳይያስም እንዲነግሩት የላከው መልእክት ከዚህ የሚከተለው ነው፦ “ዛሬ የታላቅ መከራ ቀን ነው፤ የሚያሳፍር ቅጣትና ውርደት እየደረሰብን ነው፤ የምትወልድበት ጊዜ ደርሶ ለማማጥ አቅም እንዳነሣት ሴት ሆነናል፤
እግዚአብሔር ሆይ! የሕይወታቸው ድርሻ የዚህ ዓለም ነገር ብቻ ከሆነ ሰዎች በእጅህ አድነኝ፤ ለምትወዳቸው ምግብን ስጣቸው፤ ልጆቻቸው ብዙ ይኑራቸው፤ የልጅ ልጆቻቸውም የተትረፈረፈ ምግብ እንዲኖራቸው አድርግ።
እነርሱም ከሕዝቅያስ ተቀብለው ለኢሳይያስ የነገሩት መልእክት ይህ ነበር፦ “ዛሬ የታላቅ መከራ ቀን ነው፤ የሚያሳፍር ቅጣትና ውርደት እየደረሰብን ነው፤ የምትወልድበት ጊዜ ደርሶ ለማማጥ አቅም እንዳነሣት ሴት ሆነናል፤
ማንም ሰው ክስ ሲመሠርት ትክክለኛውን ጉዳይ ይዞ አይመጣም ወደ ፍርድ ሸንጎም ሲቀርብ ለሕግ ታማኝ ሆኖ አይደለም፤ እነርሱ ከንቱ በሆነ አቤቱታ ላይ ተመሥርተው ውሸትን ይናገራሉ፤ ተንኰልን አስበው በደልን ይፈጽማሉ።
ሕዝቡ ግን ሳኦልን “ይህን ታላቅ ድል ለእስራኤል ያስገኘ ዮናታን ይሞታልን? ከቶ አይደረግም! መሞቱ ይቅርና ከራስ ጠጒሩ አንዲቱ እንደማትወድቅ በሕያው እግዚአብሔር ስም እንምላለን፤ ዛሬ እርሱ ያደረገው ነገር ሁሉ በእግዚአብሔር ረዳትነት የተፈጸመ ነው” አሉ፤ በዚህም ዐይነት ሕዝቡ ዮናታንን ከሞት ቅጣት አዳኑት።