Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 26:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 እኛ ፀንሰናል ምጥም ይዞናል፥ ነፋስንም እንደምንወልድ ሆነናል፤ በምድርም ደኅንነት አላመጣንም፤ በዓለም እንዲኖሩም ሕዝብ አልወለድንም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 አረገዝን በምጥም ተጨነቅን፤ ነገር ግን ነፋስን ወለድን፤ ለምድርም ድነትን አላመጣንም፤ የዓለምን ሕዝብ አልወለድንም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 እንዳረገዙ ሴቶች ሆንን፤ ምጥም ይዞን ነበር፤ ነገር ግን ምንም ልጅ አልወለድንም፤ ለምድራችንም ድል አላስገኘንላትም፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 አን​ተን በመ​ፍ​ራት አቤቱ፥ እኛ ፀን​ሰ​ናል፤ ምጥም ይዞ​ናል፤ በም​ድ​ርም የማ​ዳ​ን​ህን መን​ፈስ ወለ​ድን፤ በዓ​ለ​ምም የሚ​ኖሩ ይወ​ድ​ቃሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 እኛ ፀንሰናል ምጥም ይዞናል፥ ነፋስንም እንደምንወልድ ሆነናል፥ በምድርም ደኅንነት አላደረግነም፥ በዓለምም የሚኖሩ ይወድቃሉ።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 26:18
12 Referencias Cruzadas  

ምጥ እንደ ያዛት ሴት ጭንቅ ይመጣበታል፤ በሚወለድበት ጊዜ ወደ ማኅፀን አፍ ራሱን አያቀርብምና ማስተዋል የጎደለው ልጅ ነው።


አቤቱ፥ ከሰዎች፥ እድል ፈንታቸው በሕይወታቸው ከሆነች ከዚህ ዓለም ሰዎች በእጅህ አድነኝ፥ ከሰወርኸው መዝገብህ ሆዳቸውን አጠገብህ፥ ልጆቻቸው ተትረፍርፎላቸዋል የተረፋቸውንም ለሕፃናቶቻቸው ያተርፋሉ።


በጽድቅ የሚጠራ በእውነትም የሚፈርድ የለም፤ በእርባና ቢስ ነገር ታምነዋል ሐሰትንም ተናግረዋል፤ ጉዳትን ፀንሰዋል በደልንም ወልደዋል።


እነርሱም፦ “ሕዝቅያስ እንዲህ ይላል፦ ይህ ቀን የመከራና የተግሣጽ የዘለፋም ቀን ነው፤ ልጆች የሚወለዱበት ጊዜ ደርሶአል ለመውለድም ብርታቱ የለም።


ለኢሳይያስም እንዲነግሩት የላከው መልእክት ከዚህ የሚከተለው ነው፦ “ዛሬ የታላቅ መከራ ቀን ነው፤ የሚያሳፍር ቅጣትና ውርደት እየደረሰብን ነው፤ የምትወልድበት ጊዜ ደርሶ ለማማጥ አቅም እንዳነሣት ሴት ሆነናል፤


ገለባን ትጸንሳላችሁ፥ ዕብቅንም ትወልዳላችሁ፤ እስትንፋሳችሁ የምትበላችሁ እሳት ናት።


ሕዝቡ ግን ሳኦልን፥ “ለእስራኤል ይህን ታላቅ ድል ያስገኘ ዮናታን መሞት ይገባዋልን? ይህ አይሆንም! ዛሬ ይህን ያደረገው በእግዚአብሔር ርዳታ ስለ ሆነ፥ ሕያው ጌታን! ከራስ ጠጉሩ አንዲቱ እንኳ መሬት ላይ አትወድቅም” አሉት። ስለዚህ ሰዎቹ ዮናታንን ታደጉት፤ እርሱም ከመሞት ዳነ።


ሳኦል ግን፥ “ይህ ዕለት ጌታ እስራኤልን የታደገበት ቀን ሰለሆነ፥ በዛሬው ዕለት ማንም ሰው አይገደልም” አለ።


እኛ ከእግዚአብሔር እንደ ሆንን፥ መላው ዓለምም በክፉው እንደ ተያዘ እናውቃለን።


ዓለም እናንተን ሊጠላ አይቻለውም፤ እኔ ግን ይጠላኛል፤ ሥራው ክፉ መሆኑን እመሰክርበታለሁና ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios