ኢሳይያስ 21:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በባሕር አጠገብ ስለሚገኝ ምድረ በዳ የተነገረ የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው። ከደቡብ በኩል የሚመጣው ዐውሎ ነፋስ ሁሉን ነገር ጠራርጎ እንደሚወስድ አስፈሪ ከሆነች ከአንዲት አገር ከባድ ጥፋት ይመጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በባሕሩ ዳር ባለው ምድረ በዳ ላይ የተነገረ ንግር፤ ዐውሎ ነፋስ ከደቡብ እየጠራረገ እንደሚመጣ፣ ወራሪ ከአሸባሪ ምድር፣ ከምድረ በዳ ይመጣል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በባሕር አጠገብ ስላለው ስለ ምድረ በዳ የተነገረ ትንቢት። ዐውሎ ነፋስ ከደቡብ እንደሚወጣ፥ እንዲሁ ከሚያስፈራ አገር ከምድረበዳ ይወጣል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ ምድረ በዳ የተነገረ ቃል፤ ዐውሎ ነፋስ በምድረ በዳ እንደሚያልፍ፥ እንዲሁ ከሚያስፈራ ሀገር ከምድረ በዳ ይመጣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በባሕር አጠገብ ስላለው ስለ ምድረ በዳ የተነገረ ሸክም። ዐውሎ ነፋስ ከደቡብ እንደሚወጣ፥ እንዲሁ ከሚያስፈራ አገር ከምድረ በዳ ይወጣል። |
እግዚአብሔር ለሕዝቡ ለእስራኤል እንደገና ምሕረትን ያደርጋል፤ የራሱ ወገኖችም አድርጎ ይመርጣቸዋል፤ እንደገናም በአገራቸው እንዲኖሩ ይፈቅድላቸዋል፤ መጻተኞችም እንኳ መጥተው ከእነርሱ ጋር ተስማምተው አብረው ይኖራሉ።
ባቢሎንን ረግረግ ስለማደርጋት የአልቅት መፈልፈያ ትሆናለች፤ ባቢሎንን ሁሉን ነገር ጠራርጎ በሚወስድ መጥረጊያ እጠርጋታለሁ፤ እኔ የሠራዊት አምላክ ይህን ተናግሬአለሁ።”
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “አንቺ በማንም ያልተደፈርሽ የባቢሎን ከተማ ሆይ! ወርደሽ በዐቧራ ላይ ተቀመጪ፤ ወርደሽ በዙፋን ላይ ሳይሆን፤ በመሬት ላይ ተቀመጪ፤ ከእንግዲህ ወዲያ ቅምጥልና ለስላሳ መባልሽ ይቀራል።
ፍላጻቸው የተሳለ፥ ቀስታቸው የተደገነ ነው፤ የፈረሶቻቸው ኮቴ እንደ ባልጩት ነው፤ የሠረገላዎቻቸውም መንኰራኲር እንደ ዐውሎ ነፋስ ይገለባበጣል።
‘ስለ ተሰደብን አፈርን፤ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ ወደ ተቀደሱ ስፍራዎች ባዕዳን ሰዎች ስለ ገቡ ተዋርደን አንገታችንን ደፋን።’ በሉ።
ቀና ብዬ ስመለከት ብርቱ ዐውሎ ነፋስ ከሰሜን በኩል ሲመጣ አየሁ፤ ከግዙፍ ደመና የመብረቅ ብልጭታ ይታይ ነበር፤ በዙሪያው ያለውም ሰማይ ቀላ፤ መብረቁ በሚበርቅበትም ስፍራ አንዳች ነገር እንደ ነሐስ አበራ።
እርሱም ምሕረት የሌለውን ጨካኝ ሠራዊቱን አስከትሎ ምድሪቱን ለመደምሰስ ይመጣል። እነርሱም ግብጽን በሰይፍ ይመታሉ። አገሪቱም በሬሳ የተሞላች ትሆናለች።
ከምድር ሕዝቦች በጣም ጨካኞች የሆኑት ዛፉን ቈርጠው ይጥላሉ። ቀንበጦቹም በተራሮችና በሸለቆዎች ላይ ይወድቃሉ፤ ቅርንጫፎቹ ተሰባብረው በወራጅ ውሃ ላይ ይጋደማሉ። በጥላው ሥር ተጠልለው የነበሩት የምድር ሕዝቦች ሁሉ ትተውት ይሄዳሉ።
“ጊዜው ሲደርስ የግብጽ ንጉሥ በሶርያ ንጉሥ ላይ አደጋ ይጥልበታል፤ ሆኖም የሶርያ ንጉሥ በሠረገሎች፥ በፈረሶችና በመርከቦች በመጠቀም በብርቱ ጦርነት ይቋቋመዋል፤ እንደ ጐርፍ ውሃ በመጠራረግ ብዙ አገሮችን ይወራል።
እግዚአብሔር ከሕዝቡ በላይ ይገለጣል፤ የእርሱም ፍላጻዎች እንደ መብረቅ ይወረወራሉ፤ እግዚአብሔር አምላክ የመለከት ድምፅ ያሰማል፤ ከደቡብ በኩል እንደሚመጣ ዐውሎ ነፋስ ያልፋል።