Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 5:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ፍላጻቸው የተሳለ፥ ቀስታቸው የተደገነ ነው፤ የፈረሶቻቸው ኮቴ እንደ ባልጩት ነው፤ የሠረገላዎቻቸውም መንኰራኲር እንደ ዐውሎ ነፋስ ይገለባበጣል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ፍላጻቸው የተሳለ፣ ቀስታቸውም የተደገነ ነው፤ የሠረገሎቻቸውም መንኰራኵሮች እንደ ዐውሎ ነፋስ ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ፍላጻቸው የተሳለ፤ ቀስታቸውም የተደገነ ነው፤ የሠረገሎቻቸውም መንኮራኩሮች እንደ ዐውሎ ነፋስ ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ፍላ​ጾ​ቻ​ቸው ተስ​ለ​ዋል፤ ቀስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ሁሉ ተለ​ጥ​ጠ​ዋል፤ የፈ​ረ​ሶ​ቻ​ቸ​ውም ኮቴ እንደ ቡላድ፥ የሰ​ረ​ገ​ሎ​ቻ​ቸ​ውም መን​ኰ​ራ​ኵር እንደ ዐውሎ ነፋስ ይቈ​ጠ​ራል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ፍላጾቻቸው ተስለዋል፥ ቀስቶቻቸውም ሁሉ ተለጥጠዋል፥ የፈረሶቻቸውም ኮቴ እንደ ቡላድ የሰረገሎቻቸውም መንኮራኵር እንደ ዐውሎ ነፋስ ይቈጠራል።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 5:28
17 Referencias Cruzadas  

በተሳለ የወታደር ፍላጻ ይወጋችኋል፤ በከሰል ፍምም ያቃጥላችኋል።


ፍላጻዎችህ የተሳሉ ናቸው፤ የጠላቶችህንም ልብ ይወጋሉ፤ መንግሥታትም ተሸንፈው በእግርህ ሥር ይወድቃሉ።


በቀስታቸውና በፍላጻቸው ወጣቶችን ይገድላሉ፤ ሕፃናትን እንኳ አይምሩም፤ ለልጆችም ርኅራኄ የላቸውም።


በባሕር አጠገብ ስለሚገኝ ምድረ በዳ የተነገረ የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው። ከደቡብ በኩል የሚመጣው ዐውሎ ነፋስ ሁሉን ነገር ጠራርጎ እንደሚወስድ አስፈሪ ከሆነች ከአንዲት አገር ከባድ ጥፋት ይመጣል።


እግዚአብሔር በኀይለኛ ቊጣው ለመበቀልና በሚንበለበለው እሳት ለመገሠጽ በእሳት ሆኖ ይመጣል፤ መንኲራኲሮችም እንደ ዐውሎ ነፋስ ናቸው።


“እነሆ የጠላት ሠራዊት እንደ ደመና አንዣቦአል፤ የጦር ሠረገሎቹ እንደ ዐውሎ ነፋስ ፈጣኖች ናቸው፤ ፈረሶቹም ከንስር ይበልጥ ይበራሉ፤ ለእኛ ወዮልን! ጠፍተናል!


ከሚጋልቡ ፈረሶች ኮቴ ድምፅ፥ ከጠላት መንኰራኲር ድምፅ፥ ከሠረገሎቻቸው መትመም የተነሣ አባቶች ኀይላቸው በመድከሙ ምክንያት ልጆቻቸውን እንኳ ለመርዳት ወደ ኋላ አይመለሱም።


ቀስተኞቻቸው ያለ ምሕረት የሚገድሉ ኀይለኞች ጦረኞች ናቸው።


ሠራዊቱ በፈረሶቹ ሰኰናዎች መንገዶችሽን ይረጋግጣል፤ ሕዝብሽን በሰይፍ ይገድላል፤ ጠንካራ ዐምዶችሽም ወደ መሬት ይወድቃሉ።


እርሱና ሠራዊቱ፥ እንዲሁም ከእርሱ ጋር ያሉ ብዙ ሕዝብ እንደ ማዕበል ሞገድ ሆነው ይመጣሉ፤ እንደ ደመናም ሆነው ምድሪቱን ይሸፍናሉ።”


“ጊዜው ሲደርስ የግብጽ ንጉሥ በሶርያ ንጉሥ ላይ አደጋ ይጥልበታል፤ ሆኖም የሶርያ ንጉሥ በሠረገሎች፥ በፈረሶችና በመርከቦች በመጠቀም በብርቱ ጦርነት ይቋቋመዋል፤ እንደ ጐርፍ ውሃ በመጠራረግ ብዙ አገሮችን ይወራል።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እናንተ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ሆይ! ሂዱና ጠላቶቻችሁን እንደ እህል አበራዩ! ቀንዱ ብረት፥ ሰኮናው ነሐስ እንደ ሆነ በሬ ብርቱ አደርጋችኋለሁ፤ ብዙ መንግሥታትን ትደመስሳላችሁ፤ እነርሱ በግፍ የሰበሰቡትን ሀብትና ንብረት ሁሉ ለመላው ዓለም ጌታ ለእኔ ለእግዚአብሔር አምጥታችሁ ታቀርባላችሁ።”


የአለንጋና የመንኰራኲሮች ድምፅ፥ የፈረስ ግልቢያና የሠረገላ መንጓጓት ይሰማል።


ፈረሰኞች እየጋለቡ ሲመጡ የፈረሶቹ ኮቴዎች የነጐድጓድ ድምፅ አሰሙ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos