ኢሳይያስ 13:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እያንዳንዱ ኮከብና የከዋክብት ክምችቱ ብርሃን መስጠቱን ያቆማል፤ የንጋት ፀሐይ ገና ከመውጣትዋ ትጨልማለች፤ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰማይ ከዋክብትና ሰራዊታቸው፣ ብርሃን አይሰጡም፤ ፀሓይ ገና ከመውጣቷ ትጨልማለች፤ ጨረቃም ብርሃኗን አትሰጥም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰማይ ከዋክብትና ሠራዊታቸው፤ ብርሃን አይሰጡም፤ ፀሓይ ገና ከመውጣቷ ትጨልማለች፤ ጨረቃም ብርሃኗን አትሰጥም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰማይም ከዋክብትና ኦሪዎን፥ የሰማይ ሠራዊትም ሁሉ ብርሃናቸውን አይሰጡም፤ ፀሐይም በወጣች ጊዜ ትጨልማለች፤ ጨረቃም በብርሃኑ አያበራም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰማይም ከዋክብትና ሠራዊቱ ብርሃናቸውን አይሰጡም፥ ፀሐይም በወጣች ጊዜ ትጨልማለች፥ ጨረቃም በብርሃኑ አያበራም። |
የሠራዊት እምላክ ስለሚነግሥ ጨረቃ ትጨልማለች፥ ፀሐይም ብርሃንዋን አትሰጥም፤ እርሱ በኢየሩሳሌም፥ በጽዮን ተራራ ላይ ሆኖ ያስተዳድራል፤ የሕዝቡ መሪዎች ሁሉ ክብሩን ያያሉ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ባቢሎን ሆይ! በጨለማ ውስጥ ጸጥ ብለሽ ተቀመጪ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ‘የመንግሥታት ንግሥት’ ብለው አይጠሩሽም፤
በዚያን ቀን እንደ ባሕር ማዕበል እየተመሙ በእስራኤል ሕዝብ ላይ ይመጡባቸዋል፤ እነሆ ወደ ምድር ቢመለከቱ በጨለማና በመከራ እንደ ተከበቡ ያያሉ፤ ከደመናውም የተነሣ ብርሃኑ ይጨልማል።
“ከነዚያ ከመከራ ቀኖች በኋላ ወዲያውኑ ፀሐይ ትጨልማለች፤ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፤ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፤ የሰማያት ኀይሎችም ይናወጣሉ።
ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “በፀሐይና በጨረቃ፥ በከዋክብትም ላይ ድንቅ ምልክቶች ይታያሉ፤ በምድርም ላይ ሕዝቦች ሁሉ ከባሕርና ከማዕበሉ አስደንጋጭ ድምፅ የተነሣ ፈርተው ይጨነቃሉ።
አራተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ፤ የፀሐይ አንድ ሦስተኛ፥ የጨረቃ አንድ ሦስተኛ፥ የኮከቦች አንድ ሦስተኛ ተመታ፤ ስለዚህ የእነርሱ አንድ ሦስተኛቸው ጨለመ፤ በዚህ ዐይነት የቀን አንድ ሦስተኛና የሌሊት አንድ ሦስተኛ ያለ ብርሃን ሆነ።