ነህምያ፦ “ሂዱና ምርጡን ምግብ ብሉ፤ ጣፋጩን መጠጥ ጠጡ፤ ምንም ለሌላቸውም ላኩ፤ ይህ ቀን ለአምላካችን የተቀደሰ ቀን ነው፤ የእግዚአብሔር ደስታ ኀይላችሁ ስለ ሆነ አትዘኑ” አላቸው።
ኢሳይያስ 12:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ዘመን እንዲህ ብለህ ትዘምራለህ፦ “ጌታ ሆይ! ቀድሞ ተቈጥተኸኝ ነበር፤ አሁን ግን ቊጣህን መልሰህ ስላጽናናኸኝ አመሰግንሃለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ቀን እንዲህ ትላለህ፤ “እግዚአብሔር ሆይ፤ ቀድሞ ተቈጥተኸኝ ነበር፤ አሁን ግን ከቍጣህ ተመለስህ፤ ደግሞም አጽናንተኸኛልና አወድስሃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ቀን እንዲህ ትላለህ፤ “ጌታ ሆይ፤ ቀድሞ ተቈጥተኸኝ ነበር፤ አሁን ግን ከቁጣህ ተመለስህ፤ ደግሞም አጽናንተኸኛልና እወድስሃለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ቀን እንዲህ ትላለህ፥ “አቤቱ፥ ተቈጥተኸኛልና፥ ቍጣህንም ከእኔ መልሰሃልና፥ ዳግመኛም ይቅር ብለኸኛልና አመሰግንሃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ቀን፦ አቤቱ፥ ተቈጥተኸኛልና፥ ቍጣህንም ከእኔ መልሰሃልና፥ አጽናንተኽኛልምና አመሰግንሃለሁ። |
ነህምያ፦ “ሂዱና ምርጡን ምግብ ብሉ፤ ጣፋጩን መጠጥ ጠጡ፤ ምንም ለሌላቸውም ላኩ፤ ይህ ቀን ለአምላካችን የተቀደሰ ቀን ነው፤ የእግዚአብሔር ደስታ ኀይላችሁ ስለ ሆነ አትዘኑ” አላቸው።
ከመማረክና ከመገደል እንዴት ታመልጣላችሁ? ይህም ሁሉ ሆኖ የእግዚአብሔር ቊጣ ገና አልበረደም፤ ስለዚህ እናንተን ለመቅጣት እጁ እንደ ተሰነዘረ ነው።
እግዚአብሔር የቀድሞ አባቶቻቸው ከግብጽ በወጡ ጊዜ እንዳደረገው ሁሉ አሁንም ከጥፋት የተረፉት የእስራኤል ሕዝብ ከአሦር የሚወጡበትን መንገድ ያዘጋጅላቸዋል።
አምላክ ሆይ! አንተ አምላኬ ነህ፤ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፤ ስምህንም አመሰግናለሁ፤ አንተ እጅግ አስደናቂ የሆኑ ነገሮችን አድርገሃል፤ ከጥንት ጀምሮ ያቀድከውን ሁሉ፥ ፍጹምነት ባለው አስተማማኝ ሁኔታ አከናውነሃል።
ይህም በሚፈጸምበት ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ “እነሆ፥ እርሱ አምላካችን ነው፤ በእርሱ ስለ ታመንን አድኖናል፤ እርሱ እግዚአብሔር ነው፤ እኛም በእርሱ ታምነናል፤ እርሱ ስለ ታደገን በደስታ ተሞልተን ሐሴት እናደርጋለን!” ይላሉ።
እግዚአብሔር የታደጋቸው ሰዎች ተመልሰው ይመጣሉ፤ እየዘመሩም ወደ ጽዮን ይገባሉ፤ ዘወትር የደስታን ዘውድ ይቀዳጃሉ፤ ተድላና ደስታንም ያገኛሉ፤ ማዘንና መቃተት ከእነርሱ ይርቃል።
“እኔ እግዚአብሔር ጽዮንንና ባድማ የሆኑባትን ቦታዎችዋን ሁሉ አጽናናለሁ፤ ምድረ በዳዋን እንደ ዔደን፥ በረሓዋንም እንደ ገነት አደርጋለሁ፤ በእርስዋም ተድላና ደስታ ይገኛል፤ እንዲሁም የምስጋና መዝሙር ድምፅ ይሰማል።
“በኖኅ ዘመን ‘ምድርን በውሃ መጥለቅለቅ እንደገና አላጠፋትም’ ብዬ ቃል እንደ ገባሁ እነሆ አሁንም ‘በአንቺ ላይ እንደገና አልቈጣም’ ብዬ ቃል እገባልሻለሁ፤ ከእንግዲህም ወዲህ ተግሣጽ አላደርስብሽም።
እኔ በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፤ ሁለንተናዬም በአምላኬ ሐሴትን ያደርጋል፤ የአበባ አክሊል በራሱ ላይ እንደሚያደርግ ሙሽራ፥ በጌጣጌጥም እንዳሸበረቀች ሙሽሪት አድርጎ፥ የመዳንን ልብስ አልብሶኛል፤ የጽድቅንም መጐናጸፊያ ደርቦልኛል።
የአንተን መንገድ አስታውሰው ፈቃድህን በደስታ የሚፈጽሙትን ትረዳቸዋለህ፤ ፈቃድህን መተላለፍን በቀጠልን ጊዜ ግን አንተ ተቈጣኸን፤ ታዲያ እንዴት ልንድን እንችላለን?
በዚያም የሚኖሩ ሕዝብ ሁሉ፥ የምስጋና መዝሙር ይዘምራሉ፤ በደስታም እልል ይላሉ፤ አበዛቸዋለሁ እንጂ ቊጥራቸው አይቀንስም፤ ክብር እንዲኖራቸው አደርጋለሁ፤ ከዚያም በኋላ አይናቁም።
ልጃገረዶቻቸውም በደስታ ይጨፍራሉ፤ ወንዶች ወጣቶችና ሽማግሌዎችም ደስ ይላቸዋል፤ አጽናናቸዋለሁ፤ ለቅሶአቸውን ወደ ደስታ፥ ሐዘናቸውንም ወደ ሐሴት እለውጣለሁ፤
“እስራኤል ሆይ! እንዴት እተውሃለሁ? እንዴትስ አሳልፌ እሰጥሃለሁ? በአዳማና በጸቦይም ያደረግኹትንስ፥ እንዴት አደርግብሃለሁ? ለአንተ ያለኝ ፍቅር ታላቅ ስለ ሆነ፥ ይህን ሁሉ ላደርግብህ አልፈቅድም!
በዚያን ጊዜ በፈረሶች አንገት ላይ በሚንጠለጠል ቃጭል ሁሉ ላይ “ለእግዚአብሔር የተለየ” የሚል የጽሕፈት ምልክት ይቀረጽበታል፤ በቤተ መቅደሱ ውስጥ ያለው የማብሰያ ማሰሮ በመሠዊያው ላይ እንደሚገኘው ሳሕን የተቀደሰ ይሆናል።
“በአራተኛው፥ በአምስተኛው፥ በሰባተኛውና በዐሥረኛው ወር ትጠብቁት የነበረው ጾም ሁሉ ለይሁዳ ሕዝብ የተድላና የደስታ በዓል ይሆንላቸዋል፤ እናንተ ግን እውነትንና ሰላምን ውደዱ።”
እግዚአብሔር እነርሱን በጣላቸው ጊዜ ሌላው የዓለም ሕዝብ ከእግዚአብሔር ጋር ከታረቀ እግዚአብሔር እነርሱን በሚቀበላቸው ጊዜ ምን የሚሆን ይመስላችኋል? ይህማ ከሞት እንደ መነሣት ያኽል ነው!