ሆሴዕ 4:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ ካህናት እንደ ሕዝቡ ሆናችኋል፤ ስለዚህ በሕዝቡ ላይ የሚደርሰው ቅጣት በእናንተም በካህናት ላይ ይደርሳል፤ የክፉ ሥራችሁንም ብድራት ትከፍላላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካህናትም ከሕዝቡ የተለዩ አይደሉም፤ ሁሉንም እንደ መንገዳቸው እቀጣቸዋለሁ፤ እንደ ሥራቸውም እከፍላቸዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደ ሕዝቡም እንዲሁ ካህኑ ይሆናል፤ ስለ መንገዳቸውም እበቀላቸዋለሁ፥ እንደ ሥራቸውም ብድራትን እከፍላቸዋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደ ሕዝቡም እንዲሁ ካህኑ ይሆናል፤ በመንገዳቸውም እበቀላቸዋለሁ፤ እንደ ሥራቸውም እከፍላቸዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደ ሕዝቡም እንዲሁ ካህኑ ይሆናል፥ በመንገዳቸውም እበቀላቸዋለሁ፥ ሥራቸውንም እመልስባቸዋለሁ። |
የሰው ሁሉ ዕድል አንድ ዐይነት ይሆናል፤ ካህናትና ሕዝቡ፥ አገልጋዮችና አሳዳሪዎቻቸው፥ እመቤቲቱና አገልጋይቱ፥ ገዢዎችና ሻጮች፥ አበዳሪዎችና ተበዳሪዎች፥ ዕዳ ከፋይና ዕዳ አስከፋይ በአንድነት ይጠፋሉ።
ነቢያት ነን የሚሉት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፤ ካህናቱ በነቢያት ምክር ያስተዳድራሉ፤ ሕዝቡም ይህን ሁሉ አይቃወሙም፤ ታዲያ የዚህ ሁሉ ፍጻሜ በሚደርስበት ጊዜ ምን ይበጃችሁ ይሆን?”
ነገር ግን እነርሱ ራሳቸው የጣዖት አምልኮ ሥርዓት መሪዎች በመሆን ሕዝቡን ወደ ኃጢአት ስለ መሩ መቀጣት እንደሚገባቸው በራሴ ምዬአለሁ” ይላል ልዑል እግዚአብሔር።
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ሆሴዕን እንዲህ አለው፦ “ኢዩና ዘሮቹ በኢይዝራኤል በገደሉአቸው ሰዎች ምክንያት የኢዩን ቤተሰብ የምቀጣበት ጊዜ ሩቅ አይደለም፤ የእስራኤልም መንግሥት እንዲያከትም አደርጋለሁ፤
እግዚአብሔር በይሁዳ ሕዝብ ላይ የሚያቀርበው ወቀሳ አለው፤ የያዕቆብንም ልጆች እንደ አካሄዳቸው ይቀጣቸዋል፤ ባደረጉትም ክፉ ሥራ መጠን ዋጋቸውን ይከፍላቸዋል።
ነገር ግን እኔ ይህን ሁሉ ክፋታቸውን እንደማስታውስ ከቶ አይገነዘቡም፤ ከዚህ የተነሣ በገዛ ኃጢአታቸው ተከበዋል፤ ክፉ ሥራቸው ሁሉ ከእኔ የተሰወረ አይደለም።”
እነርሱ ለእኔ ምርጥ መሥዋዕት ቢያቀርቡ፥ የመሥዋዕቱንም ሥጋ ቢበሉ እኔ እግዚአብሔር አልቀበላቸውም። አሁን በደላቸውን አስቤ በኃጢአታቸው እቀጣቸዋለሁ፤ ወደ ግብጽም ይመለሳሉ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ገና በጌልገላ ሳሉ ክፉ ሥራቸው ተገለጠ፤ እኔም በዚያ የእነርሱን ሥራ መጥላት ጀመርኩ፤ ስለ ሠሩትም ክፉ ሥራ ከሰጠኋቸው ምድር አስወጣቸዋለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲያ ለእነርሱ ፍቅር አላሳያቸውም፤ መሪዎቻቸው ሁሉ ዐመፀኞች ሆነዋል።
ነገር ግን አገልጋዮቼ በሆኑት በነቢያት አማካይነት ለቀድሞ አባቶቻችሁ ያስተላለፍኩትን ሕግና ትእዛዝ ባለመጠበቃቸው ተቀጥተው የለምን? ስለዚህ በበደላቸው ተጸጸተው ‘የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ባቀደው መሠረት እንደ ሥራችንና እንደ አካሄዳችን በእኛ ላይ ቅጣትን ማምጣቱ ትክክለኛ ነው’ አሉ።”