La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሆሴዕ 12:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔር በላከው ነቢይ አማካይነት የእስራኤልን ሕዝብ ከግብጽ መርቶ አወጣቸው፤ በዚያም ነቢይ አማካይነት ተንከባከባቸው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔር በነቢይ አማካይነት እስራኤልን ከግብጽ አወጣ፤ በነቢይም በኩል ተንከባከበው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ያዕቆብ ወደ አራም ምድር ሸሸ፥ እስራኤልም ስለ ሚስት አገለገለ፥ ስለ ሚስትም በጎችን ያሰማራ ነበረ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ያዕ​ቆብ ወደ ሶርያ ሀገር ሸሸ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ስለ ሚስት አገ​ለ​ገለ፤ ስለ ሚስ​ትም ጠበቀ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ያዕቆብ ወደ ሶርያ አገር ሸሸ፥ እስራኤልም ስለ ሚስት አገለገለ፥ ስለ ሚስትም ጠባቂ ነበረ።

Ver Capítulo



ሆሴዕ 12:13
17 Referencias Cruzadas  

ይልቅስ ተነሥተህ በመስጴጦምያ ወዳለው ወደ እናትህ አባት ወደ ባቱኤል ቤት ሂድ፤ እዚያም ከአጐትህ ከላባ ሴቶች ልጆች አንዷን አግባ፤


ያዕቆብ ራሔልን ለማግባት ሰባት ዓመት አገለገለ፤ ይሁን እንጂ ራሔልን በጣም ይወዳት ስለ ነበር የቈየበት ጊዜ ጥቂት ቀን ብቻ መስሎ ታየው።


እረኛ የበጎችን መንጋ እንደሚመራ፥ አንተም በሙሴና በአሮን አማካይነት ሕዝብህን መራህ።


ሙሴም ለሕዝቡ እንዲህ አለ፦ “ይህ ቀን በባርነት ስትገዙ የኖራችሁበትን የግብጽን ምድር ለቃችሁ የወጣችሁበት ስለ ሆነ ይህን ቀን አስታውሱ፤ እግዚአብሔር በታላቅ ኀይሉ በመታደግ ያወጣችሁ በዚህ ቀን ነው፤ ስለዚህ በዚህ ቀን እርሾ የነካው እንጀራ አትብሉ።


የእስራኤልን ሠራዊት ፊት ፊት ይመራ የነበረው የእግዚአብሔር መልአክ ወደ ኋላ ተመልሶ ደጀን ሆነ፤ የደመናውም ዐምድ አልፎ በኋላ በኩል ቆመ፤


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቤን እስራኤልን ገና በሕፃንነቱ ወደድኩት፤ ልጄን ከግብጽ ጠራሁት።


የቀድሞውን የወይን ተክል እመልስላታለሁ፤ የመከራንም ሸለቆ የተስፋ በር እንዲሆናት አደርጋለሁ፤ እዚያም ከግብጽ ስትወጣ በወጣትነትዋ ወራት በነበራት ሁኔታ በደስታ ትዘምራለች።


ከግብጽ አወጣሁህ፤ ከባርነት ምድርም ታደግኹህ፤ ሙሴን፥ አሮንንና ማርያምን በፊትህ መሪዎች አድርጌ ሰጠሁህ።


ስለዚህም እኔ ከእርሱ ጋር ቃል ለቃል በግልጥ እነጋገራለሁ እንጂ ስውር በሆነ አነጋገር አልናገረውም፤ የእኔን የእግዚአብሔርን መልክ ያያል፤ ታዲያ፥ እናንተ በአገልጋዬ በሙሴ ላይ ትናገሩ ዘንድ እንዴት ደፈራችሁ?”


ከዚያ በኋላ በእግዚአብሔር አምላክህ ፊት ይህን መግለጫ ስጥ፦ ‘አባቴ ከቦታ ወደ ቦታ በመዞር የሚኖር ሶርያዊ ነበር፤ ጥቂት ቤተሰብ ይዞ ወደ ግብጽ በመውረድ መጻተኛ ሆኖ ኖረ፤ ጥቂት የነበረው ታላቅ፥ ኀያል፥ ብዙ ሕዝብ ሆነ።


ያዕቆብና ቤተሰቡ ወደ ግብጽ ወርደው በዚያ ሲኖሩ ግብጻውያን የጭቈና ቀንበር ጫኑባቸው፤ የቀድሞ አባቶቻቸውም ርዳታ ለማግኘት ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን ላከላቸው፤ እነርሱም ከግብጽ መርተው በማውጣት በዚህች ምድር እንዲሰፍሩ አደረጉአቸው፤