Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 13:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ሙሴም ለሕዝቡ እንዲህ አለ፦ “ይህ ቀን በባርነት ስትገዙ የኖራችሁበትን የግብጽን ምድር ለቃችሁ የወጣችሁበት ስለ ሆነ ይህን ቀን አስታውሱ፤ እግዚአብሔር በታላቅ ኀይሉ በመታደግ ያወጣችሁ በዚህ ቀን ነው፤ ስለዚህ በዚህ ቀን እርሾ የነካው እንጀራ አትብሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ከዚያም ሙሴ ሕዝቡን እንዲህ አለ፤ “ከባርነት ምድር ከግብጽ የወጣችሁባትን ይህችን ዕለት አስታውሱ፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር በኀያል ክንዱ አውጥቷችኋል። እርሾ ያለበትን ማንኛውንም ነገር አትብሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ሙሴም ሕዝቡን አለ፦ ከባርነት ቤት ከግብጽ የወጣችሁበትን ይህንን ቀን አስቡ፥ ጌታ ከዚህ ቦታ በብርቱ እጅ አውጥቶአችኋልና ስለዚህ የቦካ እንጀራ አትብሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ሙሴም ሕዝ​ቡን አለ፥ “ከባ​ር​ነት ቤት ከግ​ብፅ የወ​ጣ​ች​ሁ​ባ​ትን ይህ​ችን ቀን ዐስቡ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከዚህ ቦታ በበ​ረ​ታች እጅ አው​ጥ​ቶ​አ​ች​ኋ​ልና። ስለ​ዚህ የቦካ እን​ጀራ አት​ብሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ሙሴም ሕዝቡን አለ፥ “ከባርነት ቤት ከግብፅ የወጣችሁበትን ይህን ቀን አስቡ፤ እግዚአብሔር ከዚህ ቦታ በብርቱ እጅ አውጥቶአችኋልና፤ ስለዚህ የቦካ እንጀራ አትብሉ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 13:3
58 Referencias Cruzadas  

የልጅ ልጆችህ ወደዚህ ተመልሰው የሚመጡት በአራተኛው ትውልድ ነው፤ እስከዚያ የሚቈዩበትም ምክንያት የአሞራውያን ኃጢአት ገና ስላልተፈጸመ ነው።”


አገልጋዮቹ የሆናችሁ የእስራኤል ልጆች ሆይ! የእግዚአብሔር ምርጥ የሆናችሁ የያዕቆብ ልጆች ሆይ! እግዚአብሔር ያደረጋቸውን ድንቅ ነገሮች፥ የሰጠውን ፍርድና ያደረጋቸውን ተአምራት አስታውሱ።


“እግዚአብሔር ሆይ! እነዚህ የአንተ አገልጋዮችና የገዛ ሕዝብህ ናቸው፤ ከዚህ በፊትም በታላቁ ኀይልህና በብርቱ ክንድህ በመታደግ አድነሃቸዋል።


በግብጽ ንጉሥ ላይ በባለሥልጣኖቹና በምድሩ በሚኖሩትም ሕዝብ ሁሉ ላይ ድንቅ ተአምራትን ገልጠህ አሳየህ። ይህንንም ያደረግኸው የቀድሞ አባቶቻችን እንዴት እንደሚጨቈኑ በማየትህ ነው፤ ይህንንም በማድረግህ እስከ ዛሬ ድረስ ዝናህ የገነነ ሆኖአል።


አገልጋዮች የሆናችሁ የእስራኤል ልጆች ሆይ! የእግዚአብሔር ምርጥ የሆናችሁ የያዕቆብ ልጆች ሆይ! እግዚአብሔር ያደረጋቸውን ድንቅ ነገሮች፥ የሰጠውን ፍርድና ያደረጋቸውን ተአምራት አስታውሱ።


የያዕቆብ ዘሮች የሆኑት የእስራኤል ሕዝብ ከግብጽ በመውጣት የባዕድን አገር በለቀቁ ጊዜ


የእስራኤልን ሕዝብ ከግብጽ አገር መርቶ አወጣ፤ ፍቅሩ ዘለዓለማዊ ነው።


በኀያልነቱና በሥልጣኑ ይህን አደረገ፤ ፍቅሩ ዘለዓለማዊ ነው።


ጽድቅና ትክክለኛ ፍርድ የዙፋንህ መሠረቶች ናቸው፤ ፍቅርና ታማኝነት ከአንተ ጋር ናቸው።


እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ “ሰባት ቀን ሙሉ እርሾ ያልነካውና ፈጽሞ ያልቦካ ቂጣ ብቻ ትበላላችሁ፤ በመጀመሪያው ቀን እርሾውን ሁሉ ከየቤታችሁ ታስወግዳላችሁ፤ ማንም ሰው በነዚያ ሰባት ቀኖች እርሾ ያለበትን እንጀራ ቢበላ ከእስራኤል ሕዝብ መካከል ይወገዳል።


መላውን የእስራኤል ሕዝብ ከግብጽ ምድር መርቼ ያወጣሁት በዚህ ቀን ስለ ሆነ ይህን የቂጣ በዓል ትጠብቃላችሁ፤ በሚመጡትም ዘመናት ሁሉ ይህን በዓል ማክበር ቋሚ ሥርዓት ይሁንላችሁ።


እስከ ሰባት ቀን ምንም እርሾ በቤታችሁ መገኘት የለበትም፤ የአገር ተወላጅም ሆነ ወይም መጻተኛ ማንኛውም ሰው የቦካ እንጀራ ቢበላ፥ ከእስራኤል ሕዝብ መካከል ይወገዳል፤


“ይህ ወር ለእናንተ የዓመቱ መጀመሪያ ወር ይሁንላችሁ፤


አራት መቶ ሠላሳው ዓመት በተፈጸመበትም ቀን የእግዚአብሔር ሕዝብ ሁሉ የግብጽን ምድር ለቆ ወጣ።


እግዚአብሔር ሕዝቡን እየጠበቀ ከግብጽ ምድር ባወጣቸው ዕለት ጊዜው ሌሊት ነበር፤ ያም ሌሊት እስራኤላውያን በመጠባበቅ ተግተው የሚያድሩበት ለሚመጣው ትውልድ ሁሉ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ሌሊት ነው።


ሥጋውንም በዚያኑ ሌሊት እየጠበሱ ከመራር ቅጠልና ካልቦካ ቂጣ ጋር ይብሉት።


በሚመጡት ዘመናት ልጆችህ የዚህን ሥርዓት ትርጒም ቢጠይቁህ፥ እንዲህ በማለት ታስረዳቸዋለህ፦ ‘በባርነት ከተገዛንበት ከግብጽ ምድር እግዚአብሔር በታላቅ ኀይል አወጣን፤


ይህም በዓል በእጃችሁ እንደ ታሰረ ምልክትና በግንባራችሁ እንዳለ ማስታወሻ ይሆንላችኋል፤ እግዚአብሔር በታላቅ ኀይሉ ከግብጽ ስላወጣችሁም የእግዚአብሔር ሕግ ዘወትር ከአንደበታችሁ ሳይለይ በቃላችሁ እንድትደግሙትና እንድታጠኑት ያስታውሳችኋል።


“የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! በባርነት ከምትኖርባት ከግብጽ ምድር ያወጣሁህ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ነኝ፤


“የሰንበትን ቀን አክብር፤ ቀድሰውም፤


ከግብጽ በወጣችሁበት በአቢብ ወር፥ እኔ ባዘዝኳችሁ አኳኋን የቂጣን በዓል አክብሩ፤ ይህ በዓል በሚከበርባቸው በሰባቱ ቀኖች ውስጥ እርሾ የነካው እንጀራ አትብሉ፤ ለእኔ ልትሰግዱ በምትመጡበት ጊዜ መባ ሳትይዙ አትምጡ።


ስለዚህም እጅግ አስፈሪ የሆኑ ድንቅ ተአምራትን በማድረግ የኀይል ክንዴን ዘርግቼ ግብጻውያንን እቀጣለሁ፤ ከዚያም በኋላ እንድትወጡ ይፈቅድላችኋል።


“ከግብጽ የወጣችሁት በአቢብ ወር ስለ ሆነ የቂጣን በዓል በመጠበቅ በየዓመቱ አክብሩ፤ እንዳዘዝኳችሁ በአቢብ ወር እስከ ሰባት ቀን ቂጣ ብሉ።


እግዚአብሔርም ሙሴን “በንጉሡ በፈርዖን ላይ የማደርገውን አሁን ታያለህ፤ በኀይሌ ተገዶ ሕዝቤን ይለቃል፤ በኀያል ክንዴም ተሸንፎ ያባርራቸዋል።”


ስለዚህም ለእስራኤላውያን የምለውን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ ‘እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ግብጻውያን ከሚያደርሱባችሁ የባርነት ጭቈና በማዳን ነጻ አወጣችኋለሁ፤ አሠቃቂ ቅጣት አመጣባቸው ዘንድ የኀይል ክንዴን በእነርሱ ላይ አነሣለሁ፤ እናንተንም እታደጋችኋለሁ፤


የእኔ ሕዝብ አደርጋችኋለሁ፤ እኔም አምላካችሁ እሆናለሁ፤ ከግብጽ ባርነትም ነጻ በማወጣችሁ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ መሆኔን ታውቃላችሁ፤


እናንተን አይሰማችሁም፤ ከዚያን በኋላ በግብጽ ላይ በታላቅ ፍርድ ብርቱ ቅጣት በማምጣት ሠራዊቴን፥ ሕዝቤን የእስራኤልን ልጆች ከምድረ ግብጽ አስወጣቸዋለሁ።


የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እኔ ራሴ የቀድሞ አባቶቻችሁን ከግብጽ ምድር፥ ከባርነት ቤት ነጻ ባወጣኋቸው ጊዜ ከእነርሱ ጋር እንዲህ ስል ቃል ኪዳን ገብቼ ነበር።


“እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ! ከዚህ በፊት በብርቱ ኀይልህ ሕዝብህን ከግብጽ በማውጣት ስምህ እስከ ዛሬ ድረስ እንዲታወቅ አድርገሃል፥ እኛ ግን ኃጢአተኞችና በደለኞች ሆንን።


ወደ ሰው ቤት ስትገቡ ሰላምታ ስጡ፤


ቀጥሎም ኢየሱስ ኅብስት አንሥቶ ከአመሰገነ በኋላ፤ ቈርሶ ለደቀ መዛሙርቱ “እንካችሁ፤ ይህ ለእናንተ የሚሰጥ ሥጋዬ ነው፤ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት” ብሎ ሰጣቸው።


የምስጋናም ጸሎት አድርጎ ቈረሰውና “[እንካችሁ ብሉ፤] ይህ ለእናንተ የሚሆን ሥጋዬ ነው፤ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት” አለ።


ስለዚህ ተንኰልና ክፋት በሞላበት በአሮጌ እርሾ ሳይሆን እርሾ በሌለበት የቅንነትና የእውነት ቂጣ በዓላችንን እናክብር።


የማይለካው ታላቅ ኀይሉ ለእኛ ለምናምነው ምን ያኽል ታላቅ መሆኑን ታውቁ ዘንድ እጸልያለሁ፤ ይህንንም ታላቅ ኀይሉን በተግባር ያሳየው ከሞት አስነሥቶ በሰማይ በቀኙ ባስቀመጠው በክርስቶስ አማካይነት ነው።


በባርነት ከኖርክበት ከግብጽ ምድር ነጻ ካወጣህ ከአምላክህ ከእግዚአብሔር ሊያርቅህ ስለ ሞከረ እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ውገረው፤


ከዚህም በኋላ የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ የሆነውን ነገር ሰምተው ይፈራሉ፤ ስለዚህም ያንን ዐይነት ክፉ ነገር እንደገና የሚያደርግ አይኖርም።


በባርነት ከኖራችሁባት ከግብጽ ምድር ነጻ በማውጣት በአዳናችሁ በእግዚአብሔር ላይ እንድታምፁ የሚያደርጋችሁን ሕልም አላሚ ወይም ነቢይ ነኝ ባዩን ሁሉ ግደሉ፤ እንደዚህ ያለው ሰው ጸንታችሁ እንድትኖሩበት እግዚአብሔር አምላካችሁ ካዘዛችሁ መንገድ ሊለያችሁ ያቀደ ነው፤ ስለዚህ እናንተ ይህን ክፉ ነገር ከመካከላችሁ አስወግዱ።


“በቅርብም ሆነ በሩቅ ካሉት፥ ከአንዱ የምድር ዳርቻ በአካባቢህ ካሉ ከአሕዛብ አማልክት አንተ ወይም አባቶችህ የማታውቁትን አንዱን እናምልክ በማለት ሌላ እንኳ ቀርቶ የአባትህ፥ ወይም የእናትህ ልጅ ወንድምህ፥ ወንድ ልጅህ፥ ወይም ሴት ልጅህ ወይም የምትወዳት ሚስትህ ወይም የቅርብ ወዳጅህ በምሥጢር ይገፋፋህ ይሆናል።


አንተም በግብጽ ምድር ባሪያ እንደ ነበርክና እግዚአብሔር አምላክህ ነጻ ያወጣህ መሆኑን አስታውስ፤ እኔም ዛሬ ይህን ትእዛዝ የማዝህ በዚህ ምክንያት ነው።


“አንተን ከግብጽ ምድር ያወጣህ ከአቢብ ወር ውስጥ በአንዱ ሌሊት ስለ ሆነ በዚህ ወር የፋሲካን በዓል በማድረግ እግዚአብሔር አምላክህን አክብር።


እነዚህን ድንጋጌዎች በጥንቃቄ ጠብቅ፤ አንተም ቀድሞ በግብጽ ባሪያ እንደ ነበርክ አስታውስ።


ያንንም ራት በምትመገብበት ጊዜ እርሾ የነካው እንጀራ አትብላ፤ በዚያ ዐይነት አስቸኳይ ሁኔታ ግብጽን ለቀህ በወጣህበት ጊዜ እንዳደረግኸው ሰባት ቀን ሙሉ እርሾ ያልነካው ቂጣ ትበላለህ፤ ይህን ቂጣ ብላ፤ እርሱም የሥቃይ እንጀራ ተብሎ ይጠራል፤ ይኸውም በምትኖርበት ዘመን ሁሉ ብዙ ሥቃይ ከተቀበልክበት ከግብጽ ምድር የወጣህበትን ቀን ታስታውሳለህ።


እናንተም በግብጽ ባርያዎች እንደ ነበራችሁና አምላካችሁ እግዚአብሔር ነጻ እንዳወጣችሁ አስታውሱ፤ እኔም ይህን ትእዛዝ የምሰጣችሁ በዚህ ምክንያት ነው።


አንተም በግብጽ ባሪያ እንደ ነበርክ አትርሳ፤ እኔም ይህን ትእዛዝ የሰጠሁህ በዚህ ምክንያት ነው።


እግዚአብሔርም በታላቅ ኀይሉና ሥልጣኑ ታላቅ ፍርሀትን በማሳደር፥ ሥራዎችን ተአምራትንና ድንቅ ሥራዎችን በማሳየት ከግብጽ አወጣን።


ወይስ በፈተና፥ በተአምራትና በድንቅ ነገሮች፥ በጦርነት፥ በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ፥ በሚያስፈራ ኀይል፥ በዐይናችሁ እያያችሁት እግዚአብሔር አምላካችሁ እናንተን ከግብጽ ምድር እንዳወጣችሁ ያለ አንድን ሕዝብ ከሌላ ሕዝብ መካከል ወስዶ የራሱ ሕዝብ ለማድረግ የሞከረ ሌላ አምላክ አለን?


በግብጽ ምድር ባሪያ የነበርክ መሆንህን አስታውስ፤ አምላክህ እግዚአብሔር በታላቅ ኀይልና በብርቱ ሥልጣን ከዚያ አወጣህ፤ አምላክህ እግዚአብሔር የሰንበትን ቀን ታከብር ዘንድ ያዘዘህ ስለዚህ ነው።


‘በባርነት ተገዢ ሆነህ ከኖርክበት ከግብጽ ምድር ያወጣሁህ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ነኝ፤


ባሪያ ሆነህ ትኖርባት ከነበረችው ከግብጽ ምድር ያወጣህን እግዚአብሔርን እንዳትረሳ ጥንቃቄ አድርግ።


በዚያን ጊዜ አንተ እንዲህ ብለህ ንገረው፤ ‘ቀድሞ እኛ ለግብጽ ንጉሥ ባርያዎች ነበርን፤ እግዚአብሔር ግን በታላቅ ኀይሉ አወጣን፤


ነገር ግን እግዚአብሔር እናንተን ስለ ወደደ ለቀድሞ አባቶቻችሁ የሰጠውን የተስፋ ቃል መጠበቅ ፈለገ፤ በታላቅ ኀይሉ ያዳናችሁና የግብጽ ንጉሥ ባርያዎች ከመሆን ነጻ ያወጣችሁም በዚህ ምክንያት ነበር።


ልብህ እንዳይታበይና በባርነት ከኖርክባት ከግብጽ ምድር ያወጣህን አምላክህን እግዚአብሔርን እንዳትረሳ ተጠንቀቅ።


“ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ ‘ፈጥነህ ከተራራው ራስ ላይ ውረድ፤ ከግብጽ ምድር መርተህ ያወጣኸው ሕዝብህ፥ ክፉ ነገር በማድረግ ረክሶአል፤ እኔ ከሰጠኋቸው ትእዛዝ ሁሉ ወዲያውኑ ርቀው፥ የሚያመልኩትን ጣዖት ለራሳቸው ሠርተዋል።’


አምላካችን እግዚአብሔር አባቶቻችንንና እኛን ከግብጽ ባርነት አውጥቶናል፤ ያደረገውን ተአምራት ሁሉ አይተናል፤ ሕዝቦችን ሁሉ አልፈን በመጣንበት ጊዜ በሰላም ጠብቆናል፤


ከግብጽ ያወጣቸውን የቀድሞ አባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ማገልገል ተዉ፤ በዚህም ፈንታ በዙሪያቸው ያሉ ሕዝቦች የሚያመልኩአቸውን የውሸት አማልክትን ማገልገል ጀመሩ፤ ለእነርሱም በመስገድ እግዚአብሔርን አስቈጡት።


እግዚአብሔር ወደ እስራኤል ሕዝብ አንድ ነቢይ ላከ፤ ያም ነቢይ ከእስራኤል አምላክ ከእግዚአብሔር ዘንድ ያመጣው መልእክት ይህ ነው፦ “እኔ በባርነት ከኖራችሁባት ከግብጽ ምድር አወጣኋችሁ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos