ዘፍጥረት 48:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደግሞም ‘ዘርህን አበዛለሁ፤ ተወላጆችህም ብዙ ሕዝቦች ይሆናሉ፤ ይህችንም ምድር ከአንተ በኋላ ለሚመጡት ዘሮችህ ለዘለዓለም ርስት አድርጌ እሰጣቸዋለሁ’ አለኝ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህም አለኝ፤ ‘ፍሬያማ አደርግሃለሁ፣ አበዛሃለሁ፣ ለብዙ ሕዝብም ጉባኤ አደርግሃለሁ፤ ይህችንም ምድር ከአንተ በኋላ ለሚነሡ ዘሮችህ የዘላለም ርስት አድርጌ እሰጣቸዋለሁ።’ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደግሞም፦ ‘እነሆ ፍሬያማ አደርግሃለሁ፥ አበዛሃለሁም፥ ለብዙም ሕዝብ ጉባኤ አደርግሃለሁ፥ ይህችንም ምድር ከአንተ በኋላ ለዘለዓለም ርስት ለዘርህ እሰጣታለሁ።’” አለኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም አለኝ፦ እነሆ፥ አበዛሃለሁ፤ አባዛሃለሁም፤ ለብዙም ሕዝብ ጉባኤ አደርግሃለሁ፤ ይህችንም ምድር ለአንተ፥ ከአንተም በኋላ ለዘለዓለም ርስት ለዘርህ እሰጣታለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ ፍሬያማ አደርግሃለሁ አበዛሃልሁም ለብዙም ሕዝብ ጉባኤ አደርግሃለው ይህችንም ምድር ከአንተ በኍላ ለዘላለም ርስት ለዘርህ እሰጣታለሁ። |
አሁን በእንግድነት የምትኖርባትን ይህችን ምድር ለአንተና ለዘርህ እሰጣችኋለሁ፤ መላውን የከነዓን ምድር ለዘለዓለም እንዲወርሱት ለዘርህ እሰጣለሁ፤ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ።”
ደግሞም እግዚአብሔር ያዕቆብን እንዲህ አለው፦ “ሁሉን ቻይ አምላክ እኔ ነኝ፤ ብዙ ልጆች ይኑርህ፤ ዘርህም ይብዛ፤ የብዙ ሕዝብ አባት ሁን፤ ነገሥታትም ከአንተ ይወለዱ።
እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፤ “እኔ የአባትህ አምላክ፥ እግዚአብሔር ነኝ፤ ወደ ግብጽ ለመሄድ አትፍራ፤ እኔ ዘርህን በግብጽ አገር ታላቅ ሕዝብ አደርገዋለሁ፤
ከዚህ በኋላ በብርቱ ሥራ ይጨቊኑአቸው ዘንድ ጨካኞች የሆኑ አሠሪዎችን ሾሙባቸው፤ በዚህም ሁኔታ ዕቃ ማከማቻ የሆኑትን ፊቶምና ራምሴ የተባሉትን ከተሞች ለፈርዖን ሠሩ።
ለአገልጋዬ ለያዕቆብ በሰጠሁትና የቀድሞ አባቶቻቸውም በኖሩባት ምድር ይኖራሉ፤ በዚያችም ምድር እነርሱና ልጆቻቸው ዘሮቻቸውም ሳይቀሩ ለዘለዓለም ይኖራሉ፤ እንደ አገልጋዬ እንደ ዳዊት ያለ ንጉሥ በእነርሱ ላይ ለዘለዓለም ይነግሣል።
ልዑል እግዚአብሔር ለሕዝቡ ርስታቸውን ባከፋፈለ ጊዜ፥ የሰውን ዘር በለያየ ጊዜ፥ እንደ እስራኤል ልጆች ቊጥር ብዛት፥ ለሕዝቡ ድንበርን ሠራላቸው።