ዘፍጥረት 47:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፈርዖንም “ዕድሜህ ስንት ነው?” በማለት ያዕቆብን ጠየቀው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፈርዖን፣ “ለመሆኑ ዕድሜህ ምን ያህል ነው?” ሲል ያዕቆብን ጠየቀው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈርዖንም ያዕቆብን፦ “የዕድሜህ ዘመን ስንት ዓመት ነው?” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈርዖንም ያዕቆብን፥ “የኖርኸው ዘመን ስንት ነው?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈርዖንም ያዕቆብን፦ የዕድሜህ ዘመን ስንት ዓመት ነው? አለው |
ያዕቆብም “በመንከራተት ያሳለፍኳቸው ዘመናት መቶ ሠላሳ ናቸው። እነርሱም የቀድሞ አባቶቼ በመንከራተት ካሳለፉአቸው ዘመናት እጅግ ያነሡና ችግር የበዛባቸው ናቸው” አለ።
ባርዚላይ ግን እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ንጉሥ ሆይ! ከእንግዲህ ወዲያ ብዙ ዘመን አልኖርም፤ ታዲያ፥ ከአንተ ጋር ወደ ኢየሩሳሌም መሄድ ምን ያስፈልገኛል?