በጠላቶችህ ላይ ድልን ያቀዳጀህ፥ ልዑል እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን።” አብራምም በምርኮ ካገኘው ሀብት ሁሉ አንድ ዐሥረኛውን ለመልከ ጼዴቅ ሰጠው።
ዘፍጥረት 47:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን በመከር ጊዜ ከምታመርቱት ከአምስት አንዱን እጅ ለፈርዖን መስጠት አለባችሁ፤ የቀረው አራት አምስተኛው እጅ ግን ለመሬታችሁ ዘር፥ ለራሳችሁና ለልጆቻችሁ ለቤተሰባችሁም ሁሉ ምግብ ይሁናችሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም መከሩ በሚሰበሰብበት ጊዜ ግን ከዐምስት እጅ አንዱን ለፈርዖን ታስገባላችሁ፤ ከዐምስት እጅ አራቱን ደግሞ ለመሬታችሁ ዘር፣ እንዲሁም ለራሳችሁ፣ ለቤተ ሰቦቻችሁና ለልጆቻችሁ ምግብ ታደርጉታላችሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመከርም ጊዜ ፍሬውን ከአምስት እጅ አንዱን እጅ ለፈርዖን ስጡ፥ አራቱም እጅ ለእናንተ ለራሳችሁ፥ ለእርሻው ዘርና ለእናንተ ምግብ፥ ለቤተ ሰዋችሁና ለሕፃናቶቻችሁም ምግብ ይሁን።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመከርም ጊዜ ፍሬውን ከአምስት እጅ አንዱን እጅ ለፈርዖን ስጡ፤ አራቱም እጅ ለእናንተ ለራሳችሁ፥ ለእርሻው ዘርና ለእናንተ ምግብ፥ ለቤተ ሰባችሁም ሁሉ ሲሳይ ይሁን።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምድሪቱን ዝሩ በመከርም ጊዜ ፍሬውን ከአምስት እጅ አንዱን እጅ ለፈርዖን ስጡ አራቱም እጅ ለእናንተ ለራሳችሁ ለእርሻው ዘርና ለእናንተ ምግብ ለቤተ ሰዋችሁና ለሕፃናቶቻችሁም ሲሳይ ይሁን። |
በጠላቶችህ ላይ ድልን ያቀዳጀህ፥ ልዑል እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን።” አብራምም በምርኮ ካገኘው ሀብት ሁሉ አንድ ዐሥረኛውን ለመልከ ጼዴቅ ሰጠው።
እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ “የእስራኤል ሕዝብ ለእኔ የሚያመጡትን ዐሥራት ሁሉ የሌዋውያን ድርሻ እንዲሆን ሰጥቻቸዋለሁ፤ ይህም በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ለሚሰጡት አገልግሎት ደመወዝ ይሆንላቸዋል።
“በሦስተኛው ዓመት ማለት ዐሥራት በምታወጣት ዓመት ዐሥራትህን ሁሉ አጠናቅቀህ ከሰበሰብክ በኋላ በከተማህ ለሚገኙ ለሌዋውያን፥ ለመጻተኞች፥ ለሙት ልጆችና ባሎቻቸው ለሞቱባቸው ሴቶች ሰጥተህ ጠግበው እንዲበሉ አድርግ።