ከዚህ በኋላ አብራም ራእይ አየ፤ እግዚአብሔርም “አብራም፥ አትፍራ፤ እንደ ጋሻ ሆኜ ከአደጋ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፤ ታላቅ በረከትም እሰጥሃለሁ” ሲል ሰማው።
ዘፍጥረት 46:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር፥ ሌሊት በራእይ ተገለጠለትና “ያዕቆብ! ያዕቆብ!” ብሎ ጠራው። እርሱም “አቤት ጌታ ሆይ፥ እነሆ አለሁ” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም ሌሊት በራእይ ለእስራኤል ተገልጦ “ያዕቆብ ያዕቆብ” ብሎ ጠራው። እርሱም፣ “እነሆ፤ አለሁ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርም በሌሊት ራእይ፦ “ያዕቆብ ያዕቆብ” ብሎ ለእስራኤል ጠራው። እርሱም፦ “እነሆኝ” አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም በሌሊት ራእይ፥ “ያዕቆብ ያዕቆብ” ብሎ ለእስራኤል ተናገረው። እርሱም “ምንድን ነው?” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም በሌሊት ራእይ፦ ያዕቆብ ያዕቆብ ብሎ ለእስራኤል ተናገረው። እርሱም፦ እነሆኝ አለ። |
ከዚህ በኋላ አብራም ራእይ አየ፤ እግዚአብሔርም “አብራም፥ አትፍራ፤ እንደ ጋሻ ሆኜ ከአደጋ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፤ ታላቅ በረከትም እሰጥሃለሁ” ሲል ሰማው።
እግዚአብሔር አብራምን እንዲህ አለው፦ “የልጅ ልጆችህ በባዕድ አገር ስደተኞች እንደሚሆኑ ዕወቅ፤ እዚያም በባርነትና በጭቈና ለአራት መቶ ዓመት ያስጨንቁአቸዋል፤
ነገር ግን አንድ ሌሊት እግዚአብሔር በሕልም ተገልጦ አቤሜሌክን “ይህች ሴት ባለባል ስለ ሆነች እርስዋን በመውሰድህ ምክንያት ትሞታለህ” አለው።
ከዚህ ሁሉ ነገር በኋላ እግዚአብሔር አብርሃምን ፈተነው፤ እግዚአብሔርም “አብርሃም!” ብሎ ጠራው፤ አብርሃምም “እነሆ፥ አለሁኝ!” ብሎ መለሰ።
መንፈሳዊ አማካሪው ዘካርያስ በሕይወት እስከ ነበረበት ዘመን ድረስ ዖዝያ እግዚአብሔርን በታማኝነት ያገለግል ነበር፤ እግዚአብሔርም ባረከው።
የእግዚአብሔር መልአክ በቀይ ፈረስ ላይ ተቀምጦ አየሁ። እርሱም በሸለቆው ውስጥ ባሉ በባርሰነት ዛፎች መካከል ቆመ፤ በስተኋላውም ቀይ፥ ሐመርና አምባላይ ፈረሶች ይከተሉት ነበር።
እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፤ “እነሆ፥ እኔ የምነግራችሁን አድምጡ! በመካከላችሁ ነቢያት ቢኖሩ ራሴን የምገልጥላቸው በራእይ ነው፤ በሕልምም አነጋግራቸዋለሁ፤
በዚያን ጊዜ በደማስቆ ሐናንያ የሚባል አንድ ደቀ መዝሙር ነበር፤ ጌታ በራእይ “ሐናንያ!” ብሎ ጠራው፤ እርሱም “እነሆኝ ጌታ ሆይ!” አለ።
እግዚአብሔርም ጌዴዎንን እንዲህ አለው፦ “በምድያማውያን ላይ ድልን አቀዳጃቸው ዘንድ ከአንተ ጋር ያሉ ሰዎች ለእኔ እጅግ ብዙ ሆነዋል፤ በራሳቸው ኀይል የሚያሸንፉ ስለሚመስላቸው ለእኔ ክብር ከመስጠት ይቈጠባሉ፤
በዚያም ሌሊት እግዚአብሔር ጌዴዎንን እንዲህ አለው፥ “በእነርሱ ላይ ድልን እንድትቀዳጅ የማደርግህ ስለ ሆነ ተነሥተህ የእነርሱን ሰፈር አጥቃ።
እግዚአብሔርም መጥቶ በዚያ ቆመ፤ ከዚያም በፊት ያደርግ በነበረው ዐይነት “ሳሙኤል! ሳሙኤል!” ብሎ ጠራው። ሳሙኤልም “ጌታ ሆይ! እነሆ አገልጋይህ እሰማለሁና ተናገር” አለው።