Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 26:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 መንፈሳዊ አማካሪው ዘካርያስ በሕይወት እስከ ነበረበት ዘመን ድረስ ዖዝያ እግዚአብሔርን በታማኝነት ያገለግል ነበር፤ እግዚአብሔርም ባረከው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 እግዚአብሔርን መፍራት ባስተማረው በዘካርያስ ዘመን እግዚአብሔርን ፈለገ፤ እግዚአብሔርን በፈለገ መጠንም አምላክ ነገሮችን አከናወነለት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ጌታንም መፍራት ባስተማረው ዘካርያስ በእርሱም ዘመን ጌታን ለመፈለግ ልቡን አቀና፤ ጌታንም በፈለገ ጊዜ ጌታ ነገሩን አከናወነለት።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም መፍ​ራት ባስ​ተ​ማረ በዘ​ካ​ር​ያስ ዘመን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ይፈ​ልግ ዘንድ ልብ አደ​ረገ፤ በዘ​መ​ኑም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈለገ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ነገ​ሩን አከ​ና​ወ​ነ​ለት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 እግዚአብሔርንም መፍራት ባስተማረ በዘካርያስ ዘመን እግዚአብሔርን ይፈልግ ዘንድ ልብ አደረገ፤ እግዚአብሔርንም በፈለገ ጊዜ እግዚአብሔር ነገሩን አከናወነለት።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 26:5
24 Referencias Cruzadas  

ንጉሡም ዮሴፍን “ሕልም አይቼ ነበር፤ ነገር ግን ማንም ሊተረጒመው አልቻለም፤ አንተ ሕልም የመተርጐም ችሎታ እንዳለህ ሰምቼአለሁ” አለው።


ንጉሡም “የእግዚአብሔር መንፈስ ካደረበት ከዮሴፍ የተሻለ ሰው ከቶ አናገኝም” አላቸው።


የአባቱንም የዖዝያን መልካም አርአያነት በመከተል እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሥራ ሠራ፤


ዳዊት ንግግሩን በመቀጠል እንዲህ አለ፦ “አሁንም ልጄ ሆይ፥ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሁን፤ ለእርሱ ቤተ መቅደስ ትሠራለት ዘንድ የሰጠውን የተስፋ ቃል በመጠበቅ ሁሉን ነገር ያከናውንልህ፤


እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት ለእስራኤል የሰጠውን ሕጎችንና ሥርዓቶችን ሁሉ ብትፈጽም፥ ሁሉ ነገር ይሳካልሃል፤ በርታ፤ ቈራጥ ሁን፤ አትፍራ፤ ተስፋም አትቊረጥ።


ለይሁዳ ከተሞች ምሽጎችን ሠራ፤ እግዚአብሔር ሰላም ስለ ሰጠውም ለብዙ ዘመን በአገሪቱ ጦርነት አልነበረም፤


ዐዛርያስም ከንጉሥ አሳ ጋር ለመገናኘት ሄዶ እንዲህ አለው፤ “ንጉሥ አሳ ሆይ! አድምጠኝ! እናንተም የይሁዳና የብንያም ሰዎች ሁሉ ስሙኝ! እናንተ ከእግዚአብሔር ጋር እስከ ሆናችሁ ድረስ እርሱም ከእናንተ ጋር ይሆናል፤ ከፈለጋችሁትም ታገኙታላችሁ፤ ብትተዉት ግን ይተዋችኋል፤


ካህኑ ዮዳሄ በሕይወት በነበረበት ዘመን ሁሉ ኢዮአስ፥ እግዚአብሔርን ደስ የሚያስኝ ነገር ያደርግ ነበር፤


“አንተ በዚህ በምታደርገው ጦርነት የእስራኤል ወታደሮች ድጋፍ ይሆኑኛል ብለህ ታስብ ይሆናል፤ ነገር ግን አሸናፊም ሆነ ተሸናፊ እንድትሆን የሚያደርግህ እግዚአብሔር ብቻ ነው፤ እነሆ አሁንም እርሱ በጠላቶችህ ድል እንድትሆን ያደርግሃል።”


ዖዝያ የአባቱን መልካም አርአያነት በመከተል እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ነገር አደረገ፤


ኢዮአታም በአምላኩ በእግዚአብሔር ፊት መንገዱን ስለ አቀና ገናና እየሆነ ሄደ።


ሕዝቅያስ ዕድሜው ኻያ አምስት ዓመት ሲሆነው ነገሠ፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ኻያ ዘጠኝ ዓመት ገዛ፤ እናቱ አቢያ ተብላ የምትጠራ የዘካርያስ ልጅ ነበረች።


በላይ በኩል ያለውን የግዮንን ምንጭ መውጫ ገድቦ ውሃውን ወደ ምዕራብ፥ ወደ ዳዊት ከተማ፥ በቦይ እንዲወርድ ያደረገ ራሱ ሕዝቅያስ ነው፤ ይህ ሕዝቅያስ ሊሠራ ባቀደው ነገር ሁሉ የተሳካለት ሰው ነበር፤


እርሱም፦ ፍሬዋን በየወቅቱ እንደምትሰጥ፥ ቅጠሏም እንደማይረግፍ፥ በፈሳሽ ውሃ ዳር እንደ ተተከለች ዛፍ ይሆናል፤ የሚሠራውም ሥራ ሁሉ ይሳካለታል።


እግዚአብሔርም ለእነዚህ ለአራት ወጣቶች በማናቸውም ጥበብና ሥነ ጽሑፍ ዕውቀትና ማስተዋል ሰጣቸው፤ ዳንኤል ግን በተጨማሪ ራእይንና ሕልምን የመተርጐም ችሎታ ነበረው።


የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ በነገሠ በሦስተኛው ዓመት ብልጣሶር ለተባለው ለዳንኤል ሌላ ራእይ ተገለጠለት፤ በራእዩም የተነገረው ቃል እውነት ነው፤ ነገር ግን ለማስተዋል እጅግ ከባድ ከመሆኑ የተነሣ ትርጒሙ በራእይ ተገለጠለት።


በዚያኑ ሌሊት ምሥጢሩ ለዳንኤል በራእይ ተገለጠለት፤ ስለዚህ የሰማይን አምላክ እንዲህ ሲል አመሰገነ፦


አንተ ግን የተሰወረውን ነገር የመተርጐምና አስቸጋሪ የሆነውን ነገር ሁሉ የመፍታት ችሎታ እንዳለህ ሰምቻለሁ፤ ስለዚህ ይህን ጽሕፈት አንብበህ ትርጒሙን ብትነግረኝ፥ ሐምራዊ መጐናጸፊያ እንድትለብስ፤ የወርቅ ኒሻን በአንገትህ እንድታደርግና በመንግሥቴም ሥልጣን ሦስተኛውን ማዕርግ እንድትይዝ አደርጋለሁ።”


እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ “የእስራኤልና የይሁዳ ሕዝብ ሆይ! እናንተን ምን ላድርጋችሁ? እናንተ ለእኔ ያላችሁ ፍቅር እንደ ማለዳ ጉምና እንደ ጠዋት ጤዛ ፈጥኖ ይጠፋል።


እንዲሁም አንዳንድ ሰዎች ከመካከላችሁ ተነሥተው ጠማማ ትምህርት በማስተማር ብዙ አማኞችን ወደ እነርሱ ይስባሉ።


አንተ ብቻ አይዞህ፤ በርታ፤ አገልጋዬ ሙሴ ለሰጠህም ሕግ ሁሉ እውነተኛ ታዛዥ ሁን፤ በምትሄድበት ስፍራ ሁሉ ማናቸውም ነገር እንዲሳካልህ ከዚህ ሕግ ከቶ ዝንፍ አትበል፤


ይህን የሕግ መጽሐፍ ምን ጊዜም ከማንበብ አትቈጠብ፤ በእርሱ የተጻፈውን ሁሉ መፈጸም ትችል ዘንድ እርሱን ሌሊትና ቀን አሰላስለው፤ ይህንን ብታደርግ፥ ሁሉ ነገር በተቃና ሁኔታ ይሳካልሃል።


በኢያሱ ዘመንና በኋላ እግዚአብሔር ለእስራኤል ሕዝብ ያደረገውን ታላቅ ሥራ ባዩት ሽማግሌዎች የሕይወት ዘመን ሁሉ ሕዝቡ እግዚአብሔርን አመለከ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos